Skip to main content

ፖለቲካዊ ጽንፈኝነት እና ሐገር

ፖለቲካ (Politics) ለእሚለው ቃል ምንጩ ፤ ከተማ ወይንም መንደር የእሚል ትርጉም የአለው ፤ ፖሊስ (Polis) የእሚለው የግሪክ ቃል ነው ። በእርግጥ ፥ ይኽ የግሪክ ቃል ፤ ፖለቲካ ከእሚለው ቃል በአሻገርም ፤ በእንግሊዘኛ  ፦

    Police ብለን የእምናውቀውን ፤ የከተማ ፀጥታ አስከባሪ  

    Policy ብለን የእምናውቀውን ፤ በሐገር ደረጃ የፖለቲካ እና ኢከነሚ ጉዳዮች መመሪያ 

    Polity ብለን የእምናውቀውን ፤ ሐገር ፣ ብሔር ፣ ራስ ገዝ  

እና መሰል ቃላቶችም የመጡበት ነው።


ይኽንን ፥ ከተማ ወይንም መንደር የእሚል ትርጉም የነበረውን ፖሊስ የእሚባል ቃል ፤ ፖለቲካ   (politics በእንግሊዘኛ ወይንም በመጀመሪያ የግሪክ ስያሜው Politeia ) በእሚል ርዕስ መጽሐፍ በመጻፍ ፤ ቃሉን ታዋቂ የአደረገው ፤  አርስታትል እንደ ኾነ ብዙዎች ይስማማሉ ። 


የአርስታትል መጽሐፍ ፤ ምንም እንኳን ከ2,300 ዓመታት በላይ ቀደም ብሎ ቢጻፍም ፤ በመጽሐፉ ውስጥ የተነፀባረቁት ኃሳቦች ፤ በሐገር ጉዳይ ፤ ከአንድ መንደር የውስጥ ጉዳዮች አንስቶ እስከ ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ያሉትን ጉዳዮች በመዳሰስ ፤ የመጀመሪያው ሳይንሳዊ ሊባል የእሚችል ጽሑፍ በመኾኑ እና በዘመነ ዳግማዊ ስልጣኔ (Renaissance) ፤ በስፋት ከተጠኑ እና ለአኹኑ ዘመናዊ ፖለቲካዊ ሳይንስ እርሾ ከኾኑ መጽሐፍት መካከል አንዱ እና ዋነኛው በመኾኑ ፤ በሐገር ጉዳይ ላይ የእሚነሱ ርዕሶች በሙሉ ፤ ፖለቲካ በእሚል እንዲጠሩ ምክንያት ኾኗል ። 


በእርግጥ ከአርስታትል ቀደም ብሎ ፤ የአርስታትል አስተማሪ የነበረው ፕሌቶ ጽፎት ፤ ሪፐብሊክ (Republic) ተብሎ  የተተሮጎመው እና በስነ መንግሥት ጉዳይ ተመራጭ የእሚለውን አንድ ዓይነት የመንግሥት አወቃቀር የእሚተነትን መጽሐፍ  ቢኖርም ፤ የአርስታትል “ፖለቲካ” የእሚለው መጽሐፍ ፤ ከስነ-መንግሥት በአሻገር ማሕበረሰብን የእሚያስተሳስሩ እና የእሚያንቀሳቅሱ መርኾች (Dynamics) ላይ በማተኮር ፤ አንድ ሐኪም የሰውን አካል እንደ እሚያጠና ፤ ማሕበረሰብን ለማጥናት የእሚሞክር በመኾኑ ፤ ከስነ-መንግሥት ፍልስፍናዎች በአሻገር ፤ ፖለቲካዊ ማሕበረሰብን እንደ ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ የጥናት ማዕከል በማድረጉ ፥ ወይንም አርስታትል በመጽሐፉ ከእርሱ ቀደም ከነበሩት ፈላስፎች ይልቅ ፤ አካታች ሊባል በእሚቻል መልኩ የሐገርን እና ዓለም ዓቀፋዊ ግንኙነት ጉዳዮችን በመዳሰሱ ፤ ይኽንንም ጥናቱን ፥ ሐገር ( Politeia ) ወይንም ፖለቲካ ብሎ ስለ ሰየመው ፤ መሰል ጥናቶች አርስታትልን ተከትለው ራሳቸውን ፖለቲካዊ ጥናት ብለው በመሰየም ፤ ቃሉ ዛሬ የያዘውን ትርጉም እና ታዋቂነት እንዲይዝ ሳያደርጉት አልቀረም ።


ይኽ የቃሉ አጀማመር ታሪክ ሲሆን ፤ አኹን በዓለም ላይ በአለው እንደምታ ፤ ፖለቲካ የእሚለውን ቃል ፦ ቃል በቃል ወደ አማርኛ መልሰን እንተርጉመው ከአልን ፤ ሲጠብ ሐገርኛ ሲሰፋ ደግሞ ዓለም-ዓቀፍኛ የእሚል ነው የእሚኾነው ። 


ሐገርኛ ፦ በአንድ ሐገር ፤ ኢከነሚያዊ ፣ መንግሥታዊ ፣ ባሕላዊ ፣ ወዘተ ፤ ጉዳዮች ላይ መርህዎችን ፣ መላምቶችን ፣ ሕጎችን ፣ ወዘተ ፤ የእሚመለከት ሲኾን ፤ ዓለም-ዓቀፍኛ ሲኾን በተመሳሳይ በሐገራት መካከል ያሉ ኢከነሚያዊ ፣ መንግሥታዊ/አስተዳደራዊ ፣ ባሕላዊ ፣ ወዘተ ፤ ግንኙነቶች የእሚመሩባቸው መርኾች ፣ መላምቶች ፣ ሕግጋት ፣ ወዘተ ፤ የእሚመለከት ይኾናል ። 


የፖለቲካ ፅንፈኝነትም ፤ በፖለቲካው ረገድ ወይንም በሐገር እና በዓለም ዓቀፍ ጉዳይ ፤ የእኔ አስተሳሰብ ብቻ ልክ ነው ከማለት አልፎ ፤  የእኔ ከእሚለው ውጭ ያሉ ፖለቲካዊ አስተሳሰቦችን ለማስተናገድ አለመፈለግ እና ይኽንንም አቋም በተግባር ለመተርጎም መንቀሳቀስ ነው ። 


በዓለማችን ላይ ይኽን መሰል የተለያዩ ፅንፈኛ ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች በተለያየ ግዜ እና ኹኔታ ተነስተው የነበሩ ሲኾን ፤ በዘመናችን ግን ፤ ምንም እንኳን አብረው ሊጠቀሱ የእሚችሉ ሌሎች ቢኖሩም ፤ በእዚኽ ጎራ ብቸኛ ተመዳቢ ወይንም ብቻውን ይኽን ጎራ ወክሎ በአትኩሮት ሊቃኝ የእሚገባው ማርክሲዝም ነው። 


ለእዚኽም ደግሞ ምክንያቱ ፤ ማርክሲዝም በፖለቲካዊ አምባገነንነት ጎራ ውስጥ ሆኖ ፤ የአለው ልዩነት ከተጽኖው ጋር ገኖ ፤ በእንግሊዘኛው “one of a kind” ወይንም በፈርጁ ብቸኛው በእሚባል አጋኖ ሊገለጥ የእሚችል ከመሆኑ በአሻገር ፤ ምንም እንኳን እንደ ፖለቲካዊ ርዕዮት በአብዛኛው የዓለም ሕዝብ ዘንድ በአደባባይ የተወገዘ እና የተተወ ቢሆንም ፤ ያስተዋወቃቸው የፖለቲካዊ አምባገነናዊ ዜዴዎች እና አደራረጎች ፥ በቅሪትነት በተለያዩ ዘመናዊ አምባገነናዊ ስረዓቶች ውስጥ በተለያየ መልኩ የእሚታዩ በመሆኑ ፤ ማርክሲዝም እና ፖለቲካዊ አምባገነናዊ ስረዓቱን መረዳት ፤ በእዚኽ ዘመን ፖለቲካዊ አምባገነንነትን ከእነ ሙሉ ገጽታው እና አስቀያሚነቱ መረዳት የእሚያስችል በመሆኑ ነው። 


ማርክሲዝም ወደ ዓለም ዓቀፉ ፖለቲካዊ መድረክ ከመምጣቱ በፊት እና ከማርክሲዝም ውጭ ፦


    በዴሞክራሲያዊ ሕገመንግሥት ያልተገደቡ ዘውዳዊ ስረዓቶች (Monarchies without democratic constitution)

    በደም ተወራራሽ መሳፍንታዊ እና መኳንንታዊ ስረዓቶች ( Oligarchies  & Aristocracies)

    በሳይንሳዊ መርህ የተደራጁ የተለያዩ አምባገነናዊ ስረዓቶች (All forms of modern dictatorships)


በዓለም ላይ ገነው የነበሩ አምባገነናዊ ስረዓት በመኾን ፤ ከእነርሱ ውጭ ያሉ ፤ ማናቸውንም የፖለቲካ አስተሳሰቦች እና አሰላለፎች በኃይል ለማስወገድ የእሚንቀሳቀሱ የነበሩ ስለ ኾኑ ወይንም በስሪታቸው ምክንያት ብቸኛ ግዢነታቸውን የእማይቀበለውን ኹሉ እንደ ሕገወጥ ስለ እሚያዩ ፤ ፅንፈኛ የፖለቲካ ስረዓቶች ስር ተካተው መጠናት የእሚችሉ ናቸው ።  


በዘመናችን ግን ፤ እነዚኽን ኹሉ አምባገነናዊ ስረዓቶች ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ፤ ከፖለቲካዊው ምህዳር በማስወገድ ፥ የተወሰኑ ቢቀሩም እንኳን ለመወያየት በእማይበቁ መልኩ እንዲ ከስሙ በማድረግ ፤ እነ እዚኽን ሦሥቱንም አምባገነናዊ እና ፅንፈኛ ፖለቲካዊ ስረዓቶች ፤ በአንድነት አዋህዶ እና ተክቶ ወይንም ወርሶ ፤ ብቸኛ ፖለቲካዊ ፅንፈኛ ስረዓት ኾኖ ስለ ቆየ እና የስረዓቱ የአስተሳሰብ ቅሪቶች ዛሬም በተለያየ መልኩ በዘመናዊ ፖለቲካዊ ሰረዓቶች ውስጥ ስለ እሚንጸባረቁ ፤ በእዚኽ ፈርጅ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በእሚችል ደረጃ አትኩሮታችንን ከሚንዝም  ላይ  አድርገን  እንኼዳለን ።


ሚሎቨን ዲለስ (Milovan Djilas) የእሚባል በዓለም ዓቀፍ የከምኒዝም እንቅስቃሴ ከፈተኛ ደረጃ ደርሶ የነበረ እና በኋላም ከከምኒዝም ራሱን ያገለለ ሰው ፤ ስለ ከምኒዝም እንደ እዚኽ ይላል ፦

 

“በእኛ ዘመን የተከሰተው ከምኒዝም  የራሱ የኾነ ልዩ ባሕሪ የአለው እና ከሌላ ከምንም ጋር ሊምታታ የእማይገባው ነው ። ከምኒዝም  ፦ ፊውዳሊዝምን ፣ ካፒታሊዝምን እና የባሪያ ስረዓትን ራሱ በውስጡ አካቶ ፤ በተመሳሳይ ደግሞ ራሱን የቻለ ልዩ ስረዓት ነው ።”


 “Contemporary communism has its own essence which doesn’t permit it to be confused with any other. Communism, while absorbing into itself all knds of other elements – feudal, capitalist, and even slave-owning – remains individual and independent at the same time. [11]“


ከምኒዝም  ይኽን መሰል መልከ ብዙ እና አምታች የፖለቲካ ርዕዮት ነው።


እንደ አልነው ፤ ማርክሲዝምን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በእሚችል ደረጃ የእዚኽ ንዑስ ክፍል ዋነኛ አጀንዳ የእምናደርገው ቢሆንም ፤ በራሱ ልዩ ምክንያት ወደ መጨረሻ አከባቢ የፋሺዝምን አንኳር ነጥብ አንስተን ፤ ውይይታችንን ሙሉ ለማድረግ ፤ ከማርክሲዝም ጋር በተለይ ሐገርን ከእሚረዱበት እና ከእሚገልጹበት አግባብ አንጻር በማነጻጸር የተወሰኑ ነጥቦችን እንመለከታለን ። 


በእኔ እምነት ፤ ማርክሲዝም ፥ ሳይንሳዊ ለመኾን ወይንም ለመምሰል ቢጥርም ፤ እውነታው ፦ ራሱ በሳይንሳዊ መመዘኛ ሚዛን የእማይደፋ ኾኖ ሳለ ፤ በስሪቱ ሳይንሳዊነት ለሌለው ፤ ተጨባጫዊነት (Realism) ለእሚባለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ፤ ሳይንሳዊ ለምድ ለማልበስ የእሚሞክር የፖለቲካ ርዕዮት ነው ።


ተጨባጫዊነት የእሚለው ቃል እንደ እሚያሳየው ፤ የተጨባጫዊያን ፍልስፍና ፤ መኾን የእሚገባውን ወይንም መኾን የአለበትን ጉዳይ ሆን ብሎ በመዘንጋት (Purposefully disregarding the ought to be) ፤  እየኾነ በአለው ወይንም በተጨባጭ የአለውን ጉዳይ የትኩረት ማዕከሉ በማድረግ ፤ የነበረው እና የአለው ልምድ እርሱ (ተጨባጩ  ኹኔታ) ብቸኛ እውነት ነው የእሚል ነው ። 


ከላይ ሲታይ ፤ ይኽን መሰሉ የተጨባጫዊነት አስተሳሰብ ፤ ከምኞታዊው ምናብ አውጥቶ ወደ ተግባራዊ እና ገኃዱ ዓለም የእሚመልስ በመምሰል ተገቢ ሊመስል ይችላል ። በእርግጥም ፤ ነገሮችን በአሉበት ኹኔታ መረዳት እና መቀበል ተገቢ መሆኑ ብዙም የእሚያከራክር አይደለም ።


ሆኖም ግን ፤ ነገሮችን በእሚገኙበት ኹኔታ መረዳት እና መቀበል ተገቢ ነው ማለት ፤ ሌላ የተሻለ መሆን የእሚችሉበት ኹኔታ እንደ አለ መረዳት እና መቀበል የለብንም ማለት ግን አይደለም ። 


ተጨባጫዊያን በተለይ ፤ በህሊና ወይንም በሞራል ጉዳይ ፤ ነገሮችን በነበሩበት እና በአሉበት ኹኔታ ብቻ ነው የእምንረዳቸው እና የእምንቀበላቸው በማለት ፤ መኾን የእሚገባቸውን (Ought to be’s) እየደፈጠጡ ለመኖር መፈለጋቸው ፤ ከፍተኛ የሞራል ወይንም የስነምግባር ዝቅጠት በማስከተል ፤ ተጨባጫዊያን የነገሡበት የፖለቲካ ምሕዳር በሙሉ ፤ ወደ ፖለቲካዊ ፣ ኢከነሚያዊ እና ማሕበራዊ ቀውስ እና ውድቀት እንዲያመራ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ በታሪክ የእሚታይ ነው።


ለምሳሌ ፦ በአንድ የታሪክ ዘመን ላይ ፤ የፖለቲካ ስልጣን ፥ በሴራ ፣ በሸፍጥ እና በአመፅ ሊያዝ ይችላል ወይንም በየትኛውም ዘመን ላይ የፖለቲካ ስልጣንን በሴራ ፣ በሸፍጥ እና በአመፅ ከመያዝ ወደ ኋላ የእማይሉ ሰዎች እና ኃይላት ይኖራሉ ፤ አሉም ። 


ይኽን እንደ ተጨባጭ እውነታ ማስቀመጥ እና ይኽንን መረዳት በራሱ ችግር የለበትም ብቻ ሰአይሆን ተገቢም ነው ፤ ነገር ግን ፥ ይኽን ገኃዳዊ ኃቅ በመንተራስ  ፤ የፖለቲካ ስልጣን ሊያዝ እና ሊጠበቅ የእሚገባው ወይንም ብቸኛው አዋጭው የፖለቲካ ስልጣን መያዣ መንገድ ፤ ሴራ ፣ ሸፍጥ እና አመፅ ነው ማለት ወይንም የፖለቲካ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ለምሳሌ ፦ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሊያዝ አይችልም ብሎ መደምደም ፤ ከመላምታዊ ስሁቱነቱ  (its theoretical erroneousness) በአሻገር  ፖለቲካዊ ምህዳሩን እንዴት በወንጀል የወየበ ሊያድርገው እንደ እሚችል ግልፅ ነው ። ተጨባጫዊያን የእሚባሉት የፖለቲካ መስመሮች ግን ይኽ አካኼድ መገለጫቸው ነው ።


ልምድን እውነታ ማድረግ (asserting experience as truth)  ተጨባጫዊያንን የእሚገልፃቸው እና የማሕበራዊ ደህንነት አደጋ የእሚያደርጋቸው ምክንያት ነው ።


የዘመናዊ ፖለቲካ ቆርቋሪ የእሚባለው ፤ የመካከለኛው ዘመን የፖለቲካ ተመራማሪ እና ጸሐፊ ፤ ኒኮል ማክያቬሊ ፤ የተጨባጫዊያን ተወዳጅ እና ተመራጭ ጸሐፊ ነው ። ማክያቬሊ Discourse on Livy ( በሊቪ መጽሐፍ ላይ የቀረበ ሐተታ ) መሰል በሳል የፖለቲካ መጽሐፍት ቢጽፍም ፤ ተጨባጫዊያን በጣም የእሚያደንቁት እና አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ‘ተጨባጭ’ ኹኔታን መሠረት የአደረገ ስልቶቻቸውን የእሚመሰርቱት ፤ ልዑሉ (The Prince [12]) በመባል በእሚታወቀው መጽሐፉ ላይ በአስቀመጣቸው ‘ምክሮች’  ነው ። 


በእዚኽ ፦ ልዑሉ በእሚለው መጽሐፍ ውስጥ ከእሚገኙ እና ልምድን እውነታ ለማድረግ ተጨባጫዊያን ከእሚጠቀሙባቸው ማጣቀሻዎች አንዱ ፤ የእሚከተለው የማክያቬሊ ምክረ ኃሳብ ነው ፦ 


“ኹሉም ሰው እንደ እሚስማማው ፤ አንድ ልዑል በቃሉ መኖር  እና ሕይወቱን በታማኝነት ከሽንገላ ውጭ መኖር አለበት ። በልምድ እንደ እምናውቀው ግን ትልልቅ ሥራ የሰሩ ልዑላን ለቃላቸው ቦታ የሌላቸው እና የእሚፈልጉትን ለማግኘት ከመሸንገል ወደ ኋላ የእማይሉት ናቸው ። አታላዮቹ ቃላቸውን የእሚጠብቁትን አሸንፈዋል ። ማሸነፊያ መንገዶች ኹሌም ፤ ኹለት እንደ ኾኑ ማወቅ ይጠበቅብኃል ፤ አንዱ በመርህ ሌላው በኃይል ። የመጀመሪያው የሰው መንገድ ሲኾን ኹለተኛው የአውሬ መንገድ ነው ። ብዙ ግዜ ግን ፤ የመጀመሪያው መንገድ ውጤት ስለ እማያስገኝ ኹለተኛውን መጠቀም ግድ ይላል ። ስለ እዚኽ ፦ ልዑሉ የሰውንም የአውሬውንም መንገድ መጠቀም ማወቅ አለበት ። ጥንታዊ ትርክቶች  ፤ አኪሌስ እና ሌሎች ሉዕላን ቺሮን ለተባለው ፤ ከፊል ሰው ከፊል ፈረስ ለኾነው ፍጥረት ፤ ለስለጠና እንደ ተሰጡ ይነግሩናል ። ይኽም ማለት ፤ ከፊል ሰው ከፊል አውሬ የኾነ አስተማሪ ነበራቸው ማለት ነው ። ስለ እዚኽ ፦ አንድ ልዑል ኹለቱንም መንገድ መጠቀም ማወቅ አለበት ፤ አንዱ ብቻውን በቂ አይደለም ። እዚኽ አስገዳጅ ኹኔታ ውስጥ የገባው ልዑሉ ፤ አንበሳን እና ቀበሮን ምሳሌ አድርጎ መውሰድ አለበት ፤ አውሬዋዊውን አደራረግ ለመማር ። ምክንያቱም ፦ ቀበሮው ራሱን ከተኩላዎች መከላከል አይችልም ፤ አንበሳውም ከወጥመድ ማምለጥ አይችልም ። ስለ እዚኽ ፦ ወጥመዱ የተደበቀበትን ለማየት ቀበሮ መኾን ፤ ተኩላውን ለማስፈራራት ደግሞ አንበሳ መኾን አለበት ። በአንበሳነታቸው ላይ ብቻ የእሚደገፉ ምን እያደረጉ እንደ ኾነ አያውቁም ።”


“Everyone admits how good it is in a prince to keep faith, and to live with integrity and not with trickery. Nevertheless our experience has been that those princes who have done great things have held good faith of little account, and have known how to get their way through cheating. In the end they have overcome those who have relied on their word. You must know there are two ways of winning, one by the rules, and  the other by force. The first method is suited to men, the second to beasts. But because the first is frequently not sufficient, it is necessary to use the second. Therefore it is necessary for a prince to understand how to use the ways of both the beast and the man. This has been taught by example to princes by ancient writers, who describe how Achilles and many other princes of old were given to Chiron, who was half horse and half man, to nurse who brought them up in his discipline. This means that they had for a teacher one who was half beast and half human. So, it is necessary for a prince to know how to make use of both natures, and that one without the other is not sufficient. A prince, therefore, being forced knowingly to adopt the beast, ought to choose the fox and the lion; because the lion cannot defend himself against traps and the fox cannot defend himself against wolves. Therefore, it is necessary to be a fox to discover the traps and a lion to frighten the wolves. Those who rely simply on the lion do not understand what they are doing. [12]“


ይኽን መሰሉ የማክያቬሊ ምክር ፤ በዋናነት ፥ የፖለቲካ ሳይንሳዊ መርኾችን ችላ በማለት ፤ ይልቁንም በህቡ በመደራጀት ፣ በሴራ እና በውጭ ኃይል እገዛ ፣ በግልፅ ወታደራዊ ኃይል ወይንም በስውር ማስገደድ ፣ ወዘተ ፤ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ ፣ ከሰብዓዊ እና ስነምግባራዊ ግዴታ ራሳቸውን ማላቀቅ ለእሚፈልጉ ጨካኞች ወይንም ፖለቲካዊ መኃይማን ፤ ለእነርሱ እና ለሕዝባቸው ጥፋት የሚኾን ትልቅ ወጥመድ ነው ። 


ይኽ የተጨባጫዊያን የሸፍጥ ፖለቲካ ፤ ለተጨባጫዊያኑ ወጥመድ የእሚኾነው አብሮ ይዞ የእሚመጣቸው መዘዞች በመኖራቸው ነው ። 


የመጀመሪያው መዘዝ ፤ እነ እዚኽ ኃይላት ፤ በእዚኽ መልኩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ፤ በተጨባጫዊያን ሴራ እና ሸፍጥ ያገኙት ስልጣናቸው ሕጋዊ ተቀባይነት ስለ እማይኖረው ፤ ብቸኛው ይኽን ሕገ ወጥ ስልጣናቸውን ማቆያው መንገድ ያው የመጡበት የተጨባጫዊነት ሴራ እና ሸፍጥ በመሆኑ ፤ በስልጣን ለመቆየት በቋሚነት ወንጀል የእሚፈጽሙ መንግሥታት ያደርጋቸዋል ። 


ሌላው ዳፋ ፤ ይኽ ፍፁም አምባገነንነታቸው ፤ ሌላውን ተመሳሳይ ነገር ግን ተፎካካሪ ቡድን ልክ እንደ እነርሱው ፤ በሴራ ፣ በሸፍጥ እና ‘በተጨባጫዊያን’ መንገድ ተመሳሳይ የስልጣን ንጥቂያ ከአልአደረገ በስተቀር ይኽን የተጨባጫዊያንን መንግሥት አደብ የእሚያስገዛበት ወይንም ከስልጣን የእሚያወርድበት መንገድ በአለመኖሩ ፤ ሴራን ፣ ሸፍጥን ወይንም ወታደራዊ አመጽን ብቸኛው የፖለቲካ አመራር መቀየሪያ መንገድ ስለ እሚያድርገው ድምር ውጤቱ ማሕበራዊ አለመረጋጋት ነው ።


ስንጠቀልለው ፤ ፖለቲካዊ ተጨባጫዊነት ወይንም ኃይል የተቀላቀለበት ሴራ ፤ የፖለቲካ ስልጣን መያዢያ መንገድ በእሚኾንበት ግዜ ፤ በእዚኽ መንገድ ተሳክቶለት ስልጣን የያዘው ኃይል ስልጣኑን ማስጠበቅ የእሚችለው በመጣበት ኃይል በተቀላቀለበት ሴራ ስለ እሚኾን እና ይኽንንም በስልጣን ላይ የተቀመጠ ተጨባጫዊ ከስልጣን ለማውረድ የአለው ብቸኛ አማራጭ ኃይል የተቀላቀለበት ሴራ ስለ እሚያደርገው ፤ ተጨባጫዊያን የነገሡበት ፖለቲካዊ ምህዳር በሸፍጥ እና በአለመረጋጋት የተሞላ ይኾናል ።


ስልጣን የእሚያዝበት መንገድ እና ከስልጣን መወገጃውም መንገድ ኃይል የተቀላቀለበት ሴራ በሆነበት ሐገር ውስጥ ፤ ከማሕበራዊ አለመረጋጋት እና ሰቆቃ ውጭ ሌላ የእሚጠበቅ ነገር ሊኖር አይችልም ።


በእርግጥም ደግሞ ፤ የእነ ማክያቬሊን ፍሎረንስ ከተማ ፤ ምንም እንኳን የጥንታዊቷ ታላቋ ሮም ኹለተኛ ከተማ እና የዳግማዊ ስልጣኔ ወይንም የሕዳሴ (Renaissance) መፍለቂያ የነበረች ትልቅ ታሪካዊ ከተማ ብትኾንም ፤ የማክያቬሊ ዓይነቱ ተጨባጫዊ ፖለቲካ ፤ ለብዙ ዓመታት የቆየ ከልብ ወለድ የእማይተናነስ የፖለቲካዊ ሴራ ድራማ ስታስተናግድ እንድ እትቆይ በማድረግ ፤ የታሪክ ሚውዚየም ሆና እንድትቀር ከአደረጓት ምክንያቶች አንዱ ኾኖ ፤ የታሪኳ መጥፎ ገጽታ አካል ሆኗል።


ማክያቬሊ ራሱም የእዚኽ የፍሎረንስ ከተማ ተጨባጫዊ ፖለቲካ ሰለባ ኾኖ ፤ ከእነ ችሎታው እና እውቀቱ ከእሚወደው የፖለቲካ ሥራ ተባሮ ፤ በገጠራማ አከባቢ ኑሮውን በአባቱ እርሻ ላይ እንዲያደርግ የተገደደ ፣ ከአንዱ ተቃራኒ አንጃ ጋር አብረኃል ተብሎ ወፌ ላላ የተገረፈ ፤ በአጠቃላይ ፤ የፍሎረንስ ከተማ ተጨባጭ ፖለቲካዊ ባህል እንደ ከተማው ኑሮውን የአመሰቃቀለበት ሰው ነው ።


ማርክሲዝምም ፤ ፍሎረንስን ብሎም ጣልያንን በማውደም ፤ የስልጣኔ ማጀት እንደ አልነበረች ኹሉ ፤ ወደ ህያው የታሪክ ሚውዝየምነት ከቀየሯት ምክንያቶች አንዱ የሆነውን የማክያቬሊያዊ የተጨባጭ ፖለቲካ ድክመት ፤ በማርክሲዝም ‘ሳይንሳዊ’ ፖለቲካ ‘በማረም’ ፤ በዘመናዊ ታሪክ ራሱን በኃይል እና በሴራ ፤ የስልጣን ንጥቂያና እርሱንም ተከትሎ የእሚመጣውን ፍፁማዊ አምባገነን መንግሥት ምሥረታ በጉልህነት የመራ ልዩ ፖለቲካዊ ኃይል አድርጓል ።


ከማርክሲዝም በፊት የነበረው የተጨባጫዊያን ፖለቲካ ፤ በሴራ ስልጣን መያዝ ከቻልኽ ያዝ ከእሚል ግርድፍ ማበረታቻ በአሻገር ፤ ይኽን መሰሉን ተግባር ከታዋቂ የፍልስፍና መርህዎች አንጻር የእሚደግፍ ፍልስፍናዊ መዋቅር አልነበረውም ። የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ ፣ የስነ ምግባር ትንታኔ ፣ የስነ እውቀት ትንታኔ የለውም ፤ ስለ እዚኽ ፦ ማንኛውም አንጃ ፥ የተደራጀ የወንጀል ቡድንን ጨምሮ ፤ እየተነሳ ተጫባጫዊ ነኝ በማለት ፤ ራሱን ፖለቲካዊ ስልጣን እጩ አድርጎ ማቅረብ እንዲችል የእሚያበረታታ እና አንጀኝነትን የእሚያፈላ አሰራር ነበር ።

ማርክሲዝምም ይኽን ግርድፍ የማንም መንገደኛ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ መኾን የእሚችልን አካኼድ ፤ ሳይንሳዊ ካባ በማልበስ ከተርታው ሰው ቀምቶ ‘የሳይንሳዊው’ ፖለቲከኛ መሳሪያ ለማድረግ ፦ ከፍልስፍናው ፦ የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ ፥ ቁሳዊነትን (Materialism) ፣ በስነ እውቀቱ መስክ ፦ የሙግት ቁሳዊነት (Dialectical Materialism) እና በሳይንሳዊ የታሪክ ትንታኔ ፦ የታሪክ ቁሳዊነት (Historical Materialism) የእሚባሉ መላምቶችን በማዘጋጀት ፤ የፖለቲካ ስልጣንን ፦ በሴራ ፣ በአብዮት ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት በማስነሳት ፣ በሽብር ጥቃት ፣ ሕዝብ በማሥራብ ፣ ወዘተ ፤ መያዝ ትችላለኽን ወይንም ተጨባጫዊነትን ሳይንሳዊ ለማድረግ ሞክሯል ። በእዚኽም አካኼዱ የሴራ እና የነውጥ ፖለቲከኞች ኹሉ የጡት አባት በመሆን ፤ በስልጣን ላይ በቆየባቸው ዘመናት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተቀናቃኝ አልባ አምባገነናዊ ተጨባጫዊ ለመሆን በቅቷል ።


በእዚኽ መልኩ ‘ሳይንሳዊ’ የኾነው ተጨባጫዊነት ፥ ማርክሲዝም ፤ በእዚኽ አካኼዱ ከእርሱ ቀደም ከነበሩ ተጨባጫዊያን ኹሉ የላቀ ፖለቲካዊ አቅም ስለ ገነባ ፤ ሌላውን ተራ የቦዘኔ ፖለቲካ እና ሌሎቹን የአምባገነን ስረዓቶች በሙሉ በቀላሉ ከመንገድ አስወጥቶ ፤ ቦዘኔ ፖለቲከኞች እና ከማርክሲዝም ውጭ የኾኑ ሌሎች አምባገነናዊ ስረዓቶች በነበሩባቸው የዓለም ሐገራት ፤ ከአንድ ዓለም ዓቀፋዊ ማዛዣ ጣቢያ የእሚመራ ፍፁማዊ የፖለቲካ ስልጣን ኾኖ ነበር ።


ማርክሲዝም ፤ ልማዳዊ ተጨባጫዊነትን ሳይንሳዊ ካባ የማልበስ ሥራውን መሥራት የቻለው ፤ የፍልስፍናውን መሠረት በጥንታዊው የልዕለ-ተፈጥሮ ዘውግ በሆነው ቁሳዊነት (Materialism) እና የእርሱም ዋና አካል በሆነው ‘የእማያቋርጥ የግጭት ዑደት (Reality of Change) የቁሱ ዓለም መመሪያ ነው’ በእሚሉት ኹለት መላምቶች ፤ ላይ በማድረግ ነው ።


እነ እዚኽ ማርክሲዝም የተመሠረተባቸው የቁሳዊነት መላምቶች ፤ በጥንታዊ የግሪክ ፈላስፎች የተቀነቀኑ ናቸው ።

 

አንደኛው ኃሳብ ፤ የዴሞክሪተስ (Democritus 460 – 360 ቅ.ክ)  ፦


“በተጨባጫዊነት ከዐተሞች እና ከቦታ በስተቀር ምንም የለም”


“In reality there is nothing but atoms and space [13]“  


የእሚለው ሲኾን ፤ ኹለተኛው ፤ የለውጥ ተጨባጭነት ወይንም  ለውጥ ያለ መቋረጥ የእሚካኼድ መጀመሪያም መጨረሻም የሌለው ሕግ ነው  የእሚለው በሔራክሊተስ (Heraclitus 530-470 ቅ.ክ) ተይዞ የነበረው ኃሳብ ነው ፦


“ኹሉ ነገር ፤ ለዘላለም በፍሰት እና በለውጥ ኺደት ውስጥ ነው ፤ በአንድ ቦታ እንኳን ረግቶ በተቀመጠ ነገር ውስጥ የእማይታይ ውዝዋዜ እና እንቅስቃሴ አለ ። ዓለማዊው ታሪክ ኹሉ በእማያቋርጥ ዑደት ውስጥ ነው ፤ እያንዳንዱ በእሳት ጀምሮ በእሳት እያበቃ …   ‘በጠብ’ ይላል ሔራክልተስ ፤ ኹሉ ነገር ይጀምራል በእርሱም ይከስማል …   ጦርነት የኹሉ አባት እና ንጉሥ ነው ፡ አንዳንዶችን ዓማልክት ፣ አንዳንዶችን ሰዎች ፣ አንዳንዶችን ጨዋ ፣ አንዳንዶችን ባሪያ አድርጓል’። ጠብ በሌለበት በእዚያኽ ዝገት አለ ፤ ‘የእማይወዘወዝ ስብጥር ይብሰብሳል’። በእዚኽ የለውጥ ውዝዋዜ ፣ ትግል እና ምርጫ ፤ አንድ ነገር ቋሚ ነው ፤ እርሱም ይኽ ሕግ ነው ።’ ይኽ ለኹሉም የጋራ የኾነ ሕግ ፤ ሰው ወይንም ዓማልክት የሰሩት ሰአይኾን  ፤ ኹል ግዜ የነበረ ፣ የአለ እና የእሚኖር ነው ።”


“All things forever flow and change, he said; even in the stillest matter there is unseen flux and movement. Cosmic history runs in repetitious cycles, each beginning and ending in fire ... “Through strife,” says Heraclitus, “all things arise and pass away ... War is the father and king of all: some he has made gods, and some men; some slaves, and some free.” Where there is no strife there is decay: “the mixture which is not shaken decomposes.” In this flux of change and struggle and selection, only one thing is constant, and that is law. “This order, the same for all things, no one of gods or men has made; but it always was, and is, and shall be. [13]“ 


የግሪኮቹ ዴሞክሪተስ እና ሔራክልተስ ፤ እንደ ዳበረ ስልጣኔ ወራሽ ፤ እነዚኽን ኹለት ኃሳቦች ፤ ለሳይንሳዊ አዕምሮ በእሚመች መልኩ ቢያቀርቡትም ፤ እነ እዚኽ የቁሳዊ የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ ( Materialism ) መሠረት የሆኑት ፤  ከቁስ እና ከባዶ ቦታ በስተቀር ምንም የለም እና በእዚኽ ዓለም ቋሚ ነገር የለም ፤ ኹሉም ነገር በእማያቆም የለውጥ ኺደት ውስጥ ነው የእሚሉት አስተሳሰቦች ፤ እንደ ግሪኮቹ በጠራ መልኩም በአይኾን ፤ ከእነርሱ በፊት በነበሩት የግብፅ እና የኀንድ ስልጣኔዎች ውስጥ ፤ በኃይማኖታዊ ደርዙም ቢኾን ተቀምጠው እናገኛቸዋለን ።

 

ቡድኃ ካርማ የእሚለው ፤ የፍርድ ስረዓት ፤ እንደ ሔራክልተስ ፤ ተቃራኒ አካላት መካከል ባለ ግጭት ዘዋሪነት ሰአይኾን  መልካሙን ከመጥፎው በእሚለይ የፍርድ ስረዓት ፤ ፍጥረትን በሙሉ ፥ በዑደት እየሞቱ እንደገና አዲስ ፍጥረት እንዲኾኑ ያደርጋቸዋል ይላል ። 


 በቡድኃ አስተሳሰብ ፤ ቁስ ሆኖ መፈጠር አንድም ለመከራ አንድም ለመሞት ነው ፥ ትልቁ ስኬት ካርማ የእሚባለው የለውጥ ሕግ ወይንም የፍርድ ስርዓት ዳግም ቁስ አድርጎ እንደ አይፈጥረን ማድረግ ነው ። ቁስ ኾኖ አለመፈጠር እስኪሳካ ግን ፤ መልካም ሥራ መሥራት ፥ በእማያቆመው ፤ የመፈጠር እና የመሞት ዑደት ፤ የተሻለ ፍጥረት  (ዝቅተኛ የመከራ ተጋላጭነት የአለው) ሆኖ ለመምጣት ይጠቅማል  ።

 

ከእዚኽ የመከራ አዙሪት መውጣት (በስተመጨረሻ ቁስ ኾኖ ከመፈጠር መትረፍ) የእሚሳካው ወይንም ሊሳካ የእሚችለው ፦ መንኖ በዱር ውስጥ እየኖሩ (ምንም እንኳን በጥሩ ለማሰላሰል ጥሩ መብላት አለብኝ ቢሊም) ፤ ክፉ ሳያስቡ ፥ ክፉ ሳይሰሩ ኃሳብን ኹሉ በእላይኛው በጎ ነገር ላይ በማሳረፍ ነው ፦ 


“ሰው የፍትሕ ሕይወት መኖር ከተሳካለት… ልቦናውን በዘላለማዊ ነግሮች ላይ ማሳረፍ ከቻለ ፥ ልቡ ተጀምረው በእሚጠፉ ነግሮች ላይ ሳይታሰር …  በሰተመጨረሻ ነፍሱ ከህሊና በላይ ከኾነው ዘላለማዊነት ጋር ትዋኃዳለች ።”


“If, however, a man could live a life of justice ... if he could tie his thoughts on eternal things, not binding HIS HEART TO THOSE THAT BEGIN AND PASS AWAY, he would be spared rebirth...and the soul would merge at last with unconscious infinity. [4]“


ስለ እዚኽ ፤ ቡዲስት መነኮሳት ራሳቸውን ከኹሉ ነገር አግልለው ፦ ክፉ እንደ አይናገሩ ፣ ክፉ እንደ አይሰሩ ፣ ወዘተ ፤ የእሚጥሩት ፤ ቁሳዊው ዓለም ካርማ በእሚባለው የፍርድ መርህ እየተመራ ፤ ከሞቱ በኋላ  ለብዙ ስቃይ የእሚጋለጥ እንደ ነብሳት ያለ ዝቅተኛ ፍጥረት አድርጎ እንደ አያመጣቸው በመስጋት ነው ። 


ለእነርሱ ፤ በምድር ላይ ኑሮን ለማቅለል መጣር ወይንም  ማንኛውንም ሳይንሳዊ ምርምር ማድረግ ወይንም ስልጣኔን ማምጣት ጥቅም የለውም ። ምክንያቱም ፦ ሰውም ፣ ድንጋዩም ፣ ከብቱም እኩል ቁስ የኾኑ እና በእማይቀየረው የመጥፋት እና እንደገና የመፈጠር ሕግ (ካርማ) ቅረፅ ቀይረው ፤ ድንጋይ የነበረው ዛፍ ፣ ከብት የነበረው አሳ ወይንም ሌላ አንዱን ቁሳዊ ፍጥረት ኾኖ በመምጣት ፤ አሰልቺ ዑደት ውስጥ በመኾናቸው ፤ ጠቃሚው እና የእሚበጀው ነገር በተቻለ መጠን ፤ ፀጥ ብሎ ኖሮ ፤ ከተሳካ ቅልጥ ብሎ ወደ የእማይታይ ኃይልነት (Energy) መቀየር ወይንም ከእዚኽ ቁሳዊ ዓለም ወደ ምናብ መቀየር ነው ትልቁ ነገር ፤ አለበለዚያ ስንሞት እንደገና ለመከራ ስንፈጠር ፤ ካርማ (የለውጥ ተጨባጭነት) ሲያሰቃየን ነው የእምንኖረው ፤ የእሚል እምነት ነው የአላቸው ።


 በአጭሩ ወደ እዚኽ ዓለም ምንም ኾኖ መምጣት ስቃይ ነው በእሚል ፤ ቁስ ኾኖ ለአለመፈጠር የእሚደረግ ጥረት ነው ።


በተመሳሳይም  ፤ እንደ ሔሮድተስ ዘገባ ፤ የሰው ነፍስ ሰውየው ከሞተ በኋላ ፥ በተለያዩ እንሰሳት ውስጥ እየገባ  በመቆየት ፤ በሦሥት ሺ ዓመት አንድ ግዜ እንደገና ሰው ኾኖ ይመጣል ፤ በእዚኽም የሰው ነፍስ አይሞትም የእሚል ፥ ነገሮች በለውጥ ኺደት ይሽከረከሩ ይኾናል እንጂ ይዘታቸውን አይለቁም ለእሚለው አስተሳሰብ ፤ መሠረት ሊኾን በእሚችል መልኩ ግብፆች ጋር ይኽን አመለካከት እናየዋለን ፦


“ … የሰው ነፍስ ኢምውታዊ ነው ብለው በመጀመሪያ ያስታወቁት ግብፆች ናቸው ፤ አካሉ ሲሞት በእዛ ሰዓት በእሚወለድ አንድ ሌላ ፍጥረት ውስጥ ይገባል ፤ በእዚኽ መልክ በኹሉም የየብስ ፣ የባሕር እና የአየር ላይ ፍጥረታት ውስጥ ሲፈራረቅ ከዋለ በኋላ ፤ በውልደት ወቅት ወደ ሌላ ሰው አካል ውስጥ ይገባል ፤ ይኽን የሽክርክሪት ዑደት በሦሥት ሺ ዓመታት አንዴ ያደርጋል ።“


“ … and the Egyptians are also the first who reported the doctrine that the soul of man is immortal, and that when the body dies, the soul enters into another creature which chances then to be coming to the birth, and when it has gone the round of all the creatures of land and sea and of the air, it enters again into a human body as it comes to the birth; and that it makes this round in a period of three thousand years. [5]“


የስልጣኔ ኃሳቦች በባሕሪያቸው በተተኪ ስልጣኔዎች የእሚወረሱ በመሆናቸው  ፤ ይኽ ያለ እና የነበረ ፤ የእማያቆም ዑደት ኃሳብ ፤ በስልጣኔ ታሪክ ቀዳሚ በሆነችው ግብፅ ፤ ከላይ በተቀመጠው መልኩ ጀምሮ ፤ በኋላ ህንዶች (ሒንዱ እና ቡዲዝም) ጋር ግበቶ ፤ በኋላ ላይ ፤ ለዘመናዊ የቁሳዊያን (Materialism) ፍልስፍና በእሚያመች መልኩ ፤ በዴሞክሪተስ እና ሔራክሊተስ ፦ ‘ከዐተም እና ባዶ ቦታ በስተቀር ምንም የለም’ እና ‘ለውጥ ብናየውም በአናየውም እየተከናወነ የእሚኖር እና ያለ እግዚአብሔር ወይንም የሰው ጣልቃ ገብነት የተቀመጠ ነው’ በእሚሉት አባባሎች ወደ አስቀመጡት ግሪኮች እንደ መጣ ፤ የሦሥቱ ተከታታይ ስልጣኔዎች የፍልስፍና ታሪክ ስንቃኝ መረዳት እንችላለን ።


የማርክሲዝም ፍልስፍናም ይኽንን ጥንታዊ ፍልስፍና የእሚለውን ፦ ዓለም ያለ እግዚአብሔር ፍፁም እና በጎ ፈቃድ ፤ በራሷ ግዜ ያለች ፣ የነበረች እና ወደፊትም የእምትኖር ሆና በውስጧ በያዘቻቸው ተቃራኒ አካላት መካከል በእሚደረግ የእማያቆም ግጭት ፤ ግጭቱ አዳዲስ ቅርጾች በመፍጠር መልኳን እየ አስቀየራት ‘ለዘላለም’ ያለምንም አጋዥነት ትኖራለች ፤ የእሚለውን እንደ አለ ተቀብሎ ወይንም ቁሳዊ (Materialist) በመሆን ነው የእሚጀምረው ።

 

የካርል ማርክስ የከምኒዝም  ፍልስፍና አዕማድ የኾኑት ፤ የታሪክ ቁሳዊነት እና የሙግት ቁሳዊነት  የእሚባሉት መላምቶች ፤ በእነዚኽ ጥንታዊ የግሪክ ፍልስፍናዎች ላይ ስለ መመሥረታቸው  ፤ ሚሎቨን ዲለስ (Milovan Djilas) የእሚባለው እና ስታሊንን የመሰሉ የራሺያ ከሚንስት ፓርቲ አመራሮች ጋር  የቅርብ ግንኙነት እና ትውውቅ የነበረው የዩጎዝላቪያ ከሚንስት ፓርቲ ማዕከላዊ ከሚቲ አባል ፣ እንደ እዚኽ ይላል ፦


“የከምኒዝም  መሠረታዊ ኃሳቦች ፤ የቁስ ቀዳማዊነት እና የለውጥ ተጨባጭነት ናቸው…   ምንም እንኳን አንድ ግዜ ከምኒዝም  እግሩ መሬት ከረገጠ ብኋላ ቀስ በቀስ ሚናቸው እየደበዘዘ ቢኼድም”


  “communism’s basic ideas are the primacy of matter and the realty of change… as communism endures and gains strength, these ideas play a less and less role [11] “


ሚሎቨን ዲለስ (Milovan Djilas) የእነዚኽ ኃሳቦች የመጀመሪያ አዳባሪዎች ፤ ጥንታዊያኑ ዴሞክሪተስ እና ሔራክሊተስ መሰል ፈላስፎች እንደ ኾኑም ይነግረናል ፦


“እንደ ዴሞክሪተስ ያሉ የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፎች….. እንደ እዚኹም ተመሳሳይ ኃሳብ ትንሽ ለየት ባለ መልኩ በሔራክሊተስ ተገልፀው ነበር ።”


 “Earlier thinkers including Democritus in ancient Greek...the same idea had been expressed in a different way by Heraclitus (dialectics) [11]“


ከሚለቨን ዲለስ በተጨማሪ የማርክሲዝም ስረዓት ዋነኛ መሪዎች ከእሚባሉት ውስጥ ቀዳሚ የኾነው ጆሴፍ ስታሊንም ፦ ሌኒንን በመጥቀስ ፤ የእነ ሔራክልተስ ኃሳብ ለማርክሲዝም ፍልስፍና መሠረት እንደኾነ አስቀምጧል ፦


 “ስለ ጥንታዊው ፈላሳፋ ፤ ሔራክልተስ ፥ ‘ዓለም ፥ ኹሉም በአንድ ግዜ የተፈጠረው በኾነ ዓምላክ ወይንም ሰው አይደለም ፤ ነገር ግን የነበረ እና የእሚኖር በራሱ ቀመር የእሚጎመራ እና የእሚከስም ነው’ በማለት ስለ ቁሳዊነት የያዘው ምልከታ ላይ ሌኒን አስተያየት ሲሰጥ ‘የሙግት ቁሳዊነት ላይ የተሰጠ የመጀመሪያ እና ጥሩ ማብራሪያ’ በማለት ነው ።”


“Speaking of the materialist views of the ancient philosopher Heraclitus, who held that ‘the world, the all in one, was not created by any god or man, but was, is and ever will be a living flame, systematically flaring up and systematically dying down’ Lenin comments : ‘A very good exposition of the rudiments of dialectical materialism.’ [14]“ 


በእዚኽ ጥንታዊው የቁሳዊነት መላምት ላይ የተገነባው ማርክሲዝም ፤ ኹለት ዋነኛ አስተምርሆዎች ወይንም ንዑስ መላምቶች አሉት ። እነርሱም ፦ የመጀመሪያው ፤ የሙግት ቁሳዊነት (Dialectical Materialism) ሲባል ኹለተኛው የታሪክ ቁሳዊነት (Historical Materialism) በመባል ይታወቃሉ ።


የሙግት ቁሳዊነት ፤ በዋናነት ፥ የሰው ልጆች ፖለቲካዊ ግንዛቤ ከየት ይመነጫል? የእሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የእሚጥር መስክ ሲኾን ፤ ኹለተኛው ፥ የታሪክ ቁሳዊነት ደግሞ  ፤ የሰው ልጆች ፥ በሙግት ቁሳዊነት በእሚያገኙት ፖለቲካዊ ግንዛቤያቸው እየተመሩ ፤  ፖለቲካዊ ታሪካቸው ከጀመረበት ፤ ከጥንታዊ ጋርዮሽ (Primitive Communism) ተነስተው ፤ በመደብ ትግል ግንዛቤ አቀጣጣይነት ፤ የመጨረሻው እና ምንም ማሕበራዊ ቅራኔ የሌለበት ፣ የሰዎች ኢከነሚያዊ ፍላጎት ከሥራ አስተዋፆዋቸው ውጪ እንደ ፍላጎታቸው የእሚሟላበት ፤ የመጨረሻው ከምኒስታዊ ምድረገነት ላይ የእሚደርሱበትን አካኼድ የእሚገልፅ ነው ።

ጆሴፍ ስታሊን ፤ የማርክሲዝም ፍልስፍና ገሚስ ክፍል ፥ የሙግት ቁሳዊነትን (Dialectical Materialism) ኃሳብ ፤  እንዲኽ ያስቀምጠዋል  ፦


“ቁስ ነው በስሜት ህዋሶቻችን በኩል እያለፈ የተለያየ ስሜት የእሚፈጥርብን ፤ የእማያወላዳ ተጨባጭ እውነታ ኾኖ በስሜታችን የእሚመጣው ቁስ ነው … ቁስ ፣ ተፈጥሮ ፣ ኾንታው ፣ ግዑዙ ቀዳሚ ነው ፥ መንፈስ ፣ ግንዛቤ ፣ መሰማት ፣ ስነ ልቦናዊው ኹለተኛ ነው ።”


“Matter is that which, acting upon our sense-organs, produces sensation; matter is the objective reality given to us in sensation...Matter, nature, being, the physical is primary, and spirit, consciousness, sensation, the psychological is secondary. [14]“  


የሙግት እና የታሪክ ቁሳዊነት የእሚሉት የማርክሲዝም አዕማዶች ፤ በጽንሰ ኃሳብ ደረጃ ማርክስ እና ኤንግልስ ለመጀመሪያ ግዜ የማዳበሪያ ሥራ ሰሩበት የእሚባለው እና ከማርክስ ህልፈት በኋላ ፤ የጀርመን ስነኃሳብ ወይንም የጀርመኖች ኃሳባዊነት (German Ideology) በእሚል በተታተመው መጽሐፍ ውስጥ ፤ ማርክስ እንደ እዚኽ ይላል ፦


“በሰዎች አዕምሮ ውስጥ የእሚከሰቱት ውልብታዎች ፤ በአስገዳጅነት ፥ በተግባር ሊረጋገጥ በእሚችልበት እና ከቁሱ ጋር ሊነጣጠል በእማይችልበት መልኩ ፤ የቁሳዊ ህይወት ኺደት ጥለ፟ቶች ናቸው። … አስተውሎት አይደለም ህይወትን የእሚወስነው ፤ ነገር ግን ፦ ህይወት ነው አስተውሎትን የእሚወስነው።”


“The phantoms formed in the brains of men are also, necessarily, sublimates of their material life process, which is empirically verifiable and bound to material process … It is not consciousness that determines life, but life that determines consciousness. [15]“


ከእዚኽ እና መሰል የማርክሲዝም የሙግት ቁሳዊነት ገለጻዎች ተነስተን ፤ የሙግት ቁሳዊነት ፤ በፍልስፍናው መስክ የስነ ዕውቀት (Epistemology) ዓይነት እንደ ሆነ እንረዳለን ።


ይኽ የስነ እውቀት መስክ ፦ ሰው የማወቅ አቅሙን ከየት አገኘው?  እውቀትንስ እንዴት ነው የእሚያገኘው? ዓይነት ጥያቄዎችን ለመመለስ የእሚጥር የፍልስፍና መስክ ነው ።


በእዚኽም መሠረት የማርክሲዝም ፤ የሙግት ቁሳዊነት የስነ-ዕውቀት መላምት በዋነኝነት የሰው ልጅ ግንዛቤ ወይንም እውቀት ምንጭ ምንድን ነው? የእሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የእሚጥር ሆኖ ፤ ለእዚኽም ስነ-ዕውቀታዊ ጥያቄ የእሚሰጠው መልስ ፦ እውቀታችን ኹሉ ፥ በስሜት ህዋሳቶቻችን ከቁሳዊው ዓለም የእምንቀበላቸው አዕምሮዋዊ ምስል ናቸው ወይንም ከቁሳዊው ዓለም በስሜት ህዋሶቻችን ወደ አዕምሮዋችን ያልገባ እውቀት ሊኖረን አይችልም የእሚል ነው ። 


ለምሳሌ ፦ እሳትን ከማየቴ በፊት ስለ እሳት እውቀት ሊኖረኝ አይችልም ፤ የእሳት እውቀቴ ወይንም ግንዛቤዬ ፤ እሳት ከእሚባለው ቁስ ጋር ከእሚኖረኝ መስተጋብር የእሚመነጭ ነው ። በተመሳሳይም ፤ በአዕምሮዬ ውስጥ የአለው ማንኛውም ኃሳብ ወይንም እውቀት ፤ ከከባቢዬ ብቻ የመነጨ ነው የእሚል ነው። 


ስለ እዚኽ ፦ እስከ አኹን በአየነው ፤ ማርክሲዝም ሦሥት መሠረታዊ ቢህሎች አስቀምጧል ፦

    ከቁስ ውጭ በዓለም ላይ ምንም የለም

    ቁሱ ደግሞ በውስጡ ያሉ ተቃራኒ አካላት በቋሚነት የእሚጋጩበት ነው 

    ሰው ግንዛቤውን የእሚያገኘው ከእዚኽ ቁሳዊው ዓለም ነው

በእሚሉ።


እነ እዚኽ ማርክሲስታዊ ብኺሎች ደግሞ የራሳቸው ማርክሲስታዊ ድምዳሜዎች ያስከትላሉ ።


ከድምዳሜዎቹም ቀዳሚው ፦ የአለው ቁስ ብቻ ከሆነ ፥ ቁሳዊው ዓለም እንደ ኾነው ግንዛቤያችን እንደ እዛው ነው ወይንም ግንዛቤያችን የቁሳዊው ዓለም እስረኛ ነው ፤ የእሚል ነው ። 


ጆሴፍ ስታሊን ፤ ይኽንን ኃሳብ ሲያስረዳ እንደ እዚኽ ይላል ፦


“…ተፈጥሮ ፥ ቁሳዊው ዓለም ኾኖ ቀዳሚ ከኾነ ፤ አስተውሎት ፥ ኃሳብ ደግሞ ኹለተኛ ፥ የእርሱ ቅጂ ከኾነ ፤ ቁሳዊው ዓለም ተጨባጩን እውነታ ከሰዎች አስተውሎ በተናጠል የእሚወክል ከኾነ ፥ አስተውሎት የእዚኽ ተጨባጭ ኹኔታ ነፀብራቅ ሲኾን ፤ የማሕበርሰብ ቁሳዊ ሕይወቱ ፥ ሕልውናው ቀዳሚ ፣ መንፈሳዊ ሕይወቱ ዳግማዊ ፥ ክፋይ ነው የእሚለውን ያስከትላል ፣ እናም የማሕበረሰብ ቁሳዊ ሕይወት ከሰዎች ፈቃድ ተነጥሎ በራሱ የእሚኖር ተጨባጭ እውነታ ሲኾን መንፈሳዊ ሕይወቱ ደግሞ የእዚኽ ተጨባጭ እውነታ ነፀብራቅ ፥ የማንነቱ ነፅብራቅ ይኾናል ።

እንዲያኽም በመኾኑ ፥ የማሕበረሰብ መንፈሳዊ ሕይወት መሥራች ምንጭ ፥ የማሕበረሰባዊ ኃሳቦች ምንጭ ፤ በኃሳቦች ፣ በመላምቶች ፣ አመለካከቶች እና ፖለቲካዊ ተቋሞች ውስጥ መፈለግ የለበትም ፤ ነገር ግን የእነዚኽ ኃሳቦች ፣ መላምቶች ፣ አመለካከቶች ፣ ወዘተ ፤ ነፀብራቆችን የፈጠራቸው አንድ ማሕበረሰብ የእሚኖርበት ቁሳዊ ኹኔታ ውስጥ ፥ በማሕበረስባዊ ማንነቱ/ህልውናው ውስጥ ነው መፈለግ የአለበት ።”


“Further, if nature, being, the material world, is primary, and consciousness, thought, is secondary, derivative; if the material world represents objective reality existing independently of the consciousness of men, while consciousness is a reflection of this objective reality, is also primary, and its spiritual life secondary, derivative, and that the material life of society an objective reality existing independently of the will of men, while the spiritual life of society is a reflection of this objective reality, a reflecting of being.

Hence, the source of formation of the spiritual life of society, the origin of social ideas, social theories, political views and political institutions, should not be sought for in the ideas, theories, views and political institutions themselves, but in the conditions of the material life of society, in social being, of which these ideas, theories, views, etc..., are the reflection. [14]“


በእዚኽ ምክንያት ፤ በማርክስ የሙግት ቁሳዊነት መሠረት ፤ የሰዎች ወይንም የሕዝብ ፖለቲካዊ ግንዛቤ የእሚቀዳው ፤ በብቸኝነት ከእሚኖሩበት ቁሳዊ (ኢከነሚያዊ እና ፖለቲካዊ) ኹኔታ ነው ። 


ይኽ ፥ የሰዋዊ ግንዛቤያችን ወይንም እውቀተቻን ብቸኛ ምንጭ የኾነው ፤ ቁሳዊው ዓለም ደግሞ የእሚመራበት አንድ ቋሚ ሕግ ፤ በውስጡ በእሚገኙ ተቃራኒ አካላት መካከል በእሚደረግ ግጭት አዲስ ዓይነት ቁስ የመፍጠር ነው ወይንም ለውጥ/ግጭት የእማያቆም ተፈጥሮዋዊ ሕግ ነው ። ዲያሌክቲክ ወይንም ሙግት ማለትም ይኽ በተቃራኒዎች መካከል የእሚድረግ ግጭት መኾኑ ነው ። 


ጆሴፍ ስታሊን ፤ ሌኒን በመጥቀስ ስለ ሙግት ወይንም ዲያሌክቲክስ እንዲኽ ይላል ፦


“‘በትክክለኛው ትርጉሙ’ ሌኒን እንዳለው ‘ሙግት (ዴያሌክቲክስ) በቁስ ውስጥ ያሉ ተፈጥሮዋዊ ተቃርኖዎችን/ግጭቶችን የእምናጠናበት አግባብ ነው’ ።”


“‘In its proper meaning’, Lenin says, ‘dialectics is the study of the contradiction within the very essence of things.’ [14]“


ይኽም የቁሱ ዓለም የእሚመራበት የእማያቆም የግጭት ወይንም የለውጥ መርህ ደግሞ ፤ ከግጭቱ በኋላ ፤ ተቃራኒ ተጋጪዎቹን በማዋኃድ ወይንም አንዱ አንዱን በማጥፋት ፤ አዳዲስ ነገሮች ወይንም እርጎች (states) የእሚፈጠሩበት ኺደት በመሆኑ ፤ ለውጥ ወይንም እድገትን መረዳት ማለት ፤ ይኽንን የግጭት መርህ መረዳት ማለት ነው ።

 

ስለ እዚኽ ጉዳይ ቭላድሚር ሌኒን ፤ እድገት ማለት የተቃራኒዎች ግጭት ነው ብሏል ፦


“እድገት የተፃራሪዎች ‘ትግል’ ነው ።”

“Development is the ‘struggle’ of opposites. [14]“


አኹንም በድጋሚ ፤ ማርክሲዝም እስከ አኹን የአየናቸውን ብኺሎች አጠናቅሮ ፤ ማለትም ፦

    ከቁስ ውጭ በዓለም ላይ ምንም የለም

    ቁሱ ደግሞ በውስጡ ያሉ ተቃራኒ አካላት በቋሚነት የእሚጋጩበት ነው 

    ሰው ግንዛቤውን የእሚያገኘው ከእዚኽ በተቃራኒ አካላት መካከል በአለ ግጭት መርኽ ከእሚመራው ቁስ ነው

ወይንም የአለው ቁስ ብቻ ነው ፣ ቁሱም የእሚመራው በተቃራኒ ቁሶች መካከል ግጭት እየተፈጠረ እና ይኽም ግጭት ወደ አዲስ እርጋታ በማምራት ነው ፣ የእኛ የሰዎች የግንዛቤያችን ብቸኛው ምንጭ ቁስ ነው ፤ ስለ እዚኽም ፦ እኛ ግንዛቤያችን የቁስ ዓለሙ እስረኞች የኾንን ሰዎች ፤ የእሚኖረን ግንዛቤ ፤ በከባቢያችን ባለው ቁሳዊ ኹኔታ የተቀረፀ እና ከእኛ በተቃራኒ ቁሳዊ ኹኔታ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ለመጋጨት የተዘጋጀ ግንዛቤ ወይንም የተቃራኒ መደብ አስተውሎ (Antagonistic Class Consciousness) ነው ያለን ይላል ማርክሲዝም ።


የማርክሲዝም የሙግት ቁሳዊነት ስነ-ዕውቀት ዋነኛ ምርትም ፤ ተጻራሪ የመደብ ትግል አስተውሎ ፤ በቁሱ ዓለም አስገዳጅነት በሰው ልጆች ላይ የተጫነ ፤ አማራጭ የሌለው ፖለቲካዊ ግንዛቤ ነው የእሚለው አስተሳሰብ ነው ።

 

ይኽን የመደብ ትግል አስተሳሰብ በማርክሲስታዊ ዘዬ ጆሴፍ ስታሊን እንደ እዚኽ አስቀምጦታል ፦


“… እድገት ውስጣዊ ተቃርኖዎችን ወደ አደባባይ በማውጣት ፣ እነ እዚኽን ተቃርኖዎችን ድል ለመንሳት ፣ በእነ እዚኽ ተቃርኖዎች ላይ የተመሠረተ የተፃራሪ ኃይሎች ግጭት የእሚመጣ ከኾነ ፤ የሠራተኛው የመደብ ትግል እጅግ ተፈጥሮዋዊ እና ሊቀር የእማይችል ክስተት መኾኑ ግልፅ ነው ። …

ስለ እዚኽም ፦ በፖሊሲ ጉዳይ ለአለመሳሳት ፤ አንድ ሰው መከተል የአለበት ያልተሸቃቀጠውን የሠራተኛው መደብ ፖሊሲ ነው እንጂ ፤ የአዳሾቹን ፥ የሠራተኛውን እና የቡርዣውን ፍላጎት ማጣጣም የእሚለውን ፖሊሲ አይደለም ፤ ካፒታሊዝምን ወደ ሶሻሊዝም በዝግመት ‘ማሳደግ’ የእሚለውን የሸቃጮቹን ፖሊሲ አይደለም ።”


“…, if development proceeds by way of the disclosure of internal contradictions, by way of collisions between opposite forces on the basis of these contradictions, then it is clear that the class struggle of the proletariat is a quite natural and inevitable phenomenon. …

Hence, in order not to err in policy, one must pursue an uncompromising proletarian class policy, not a reformist policy of harmony of the interest of the proletariat and the bourgeoisie, not a compromisers’ policy of the ‘growing of capitalism into socialism. [14]“


ይኽ ጆሴፍ ስታሊን ስለ መደብ ትግል የእሚያስረዳበት ከላይ የአለው የማርክሲዝም ድምዳሜ ፤ ቀለል በአለ አገላለፅ እያለ የአለው ፤ በእውነት የአለው ቁስ ብቻ በመሆኑ እና ቁሱም በተቃራኒ አካላት መካከል በእሚደረግ ግጭት ስለ እሚመራ እናም ሰዋዊ ግንዛቤ የቁሱ ዓለም ነጸብራቅ እንጂ ከቁሱ የተነጠለ የራሱ ህልውና የሌለው በመሆኑ ፤ የብቸኛው እውነታ ፥ የቁሱ ፤ ነጸብራቅ የሆነው የመደባዊ ተቃርኖ ግንዛቤ ፤ ሰዎች ፈልገው ወይንም መርጠው የእሚይዙት ግንዛቤ ሰአይሆን ፤ ከባቢያቸው ፥ ብቸኛው እውነታ እና የእውቀታቸው ምንጭ ፤ ከሰዎቹ ፍላጎት እና አቅም ውጭ በአዕምሮዋቸው ውስጥ የእሚፈጥረው  ነጸብራቅ ነው ።


ይኽም በመሆኑ ፤ ከመደብ ተቃርኖ ወይንም ትግል ውጭ ያለ አስተሳሰብ በሙሉ ፤ ስህተት በመሆኑ ፤ ማንም ሰው እንደ እውነት እና ትክክል ሊቀበለው አይገባም የእሚል ነው ።


ይኽ ማርክሲስታዊ ድምዳሜ ፤ ፍፁማዊ እና ፅንፈኛ የፖለቲካ ድምድሜ በመኾን ፤ ከአጠፋፊ የመደብ ትግል ሌላ ምንም ዓይነት አማራጭ የፖለቲካ ኃሳብ የእማይቀበልበት ዋነኛው ምክንያትም ፤ የመደብ ትግል አስተሳሰብ ፤ የሰው ልጅ ፈልጎት ወይንም ተመራምሮ የእሚደርስበት የግንዛቤ ደረጃ ሰአይኾን ፤ የሰው ልጅ የእሚኖርበት ቁሳዊ ኹኔታ ብቻ የእሚፈጥርበት ግንዛቤ ፤ ስለ እዚኽም ፦ ተፈጥሮዋዊ እና የማይሻር ሕግ ነው ስለ እሚል ነው ።

 

ከእዚኽ ውጭ የአለው ፤ ሰላማዊ እና ዝግመታዊ ለውጥ ወይንም ተቃራኒ ፍላጎቶችን ማቻቻል ወይንም ማንኛውም የማርክሲዝምን የመደብ ተቃርኖ ትግል የእሚለውጥ አስተሳሰብ የፖሊሲ ስህተት ነው ለማርክሲዝም ።


ይኽ መደባዊ ግጭት ደግሞ ፤ እንደ ማርክስ የታሪክ መዘውር ወይንም ሞተር ነው ፤ ምክንያቱም ፦ ማሕበርሰብ በእዚኽ የሙግት ቁሳዊነት ምርት በኾነው የመደብ ግጭት አስተውሎ እየተመራ ፤ ከጥንታዊ ጋርዮሽ ጀምሮ የተለያዩ ማሕበራዊ የእድገት ደረጃዎችን ወይንም እርጎች እየፈጠረ የመጨረሻውን መደብ እና ቅራኔ አልባውን ፤ የጋርዮሽ ስረዓት እስኪ መሠርት ድረስ ፤ በእማያቋርጥ የመደብ ግጭት ውስጥ ይቀጥላል ።


ይኽንን ማሕበረሰብ በመደብ ግጭት አስተውሎ እየተመራ ከጥንታዊ የጋርዮሽ ማሕበራዊ አወቃቀር ተነስቶ ፤ አኹን እስከ እሚገኝበት እና ወደ ፊትም ስለ እሚኖረው አወቃቀር መላምት የእሚያስቀምጠው የማርክሲዝም ፍልስፍና ኹለተኛው ክፍል ደግሞ የታሪክ ቁሳዊነት (Historical Materialism) ነው ።


የታሪክ ቁሳዊነት ፤ የሰው ልጅ ታሪክ ምን ይመስል ነበር ብቻ ሰአይኾን  ወደ ፊት ምን ይኾናል የእሚለውን የእሚመልስ ወይንም እመልሳለሁ የእሚል ነው ። ይኽም ደግሞ ፤ ጨዋታ አዋቂው ጆሴፍ ሹም ፒተር እንደ አለው ፤ ከምኒዝም  ነብይ (ካርል ማርክስ ) ፣ የተስፋ ምድር (የመጨረሻው የከምኒዝም  ደረጃ ) እና በእምነት የእሚቀበሉት ዶግማ  (ማርክሲዝም) የአለው በመኾኑ ኃይማኖት ያደርገዋል ። 


ሹምፒተር ፦ ካፒታሊዝም ፣ ሶሻሊዝም እና ዴሞክራሲ (Capitalism, Socialism and Democracy) ፤ በእሚለው መጽሐፉ ውስጥ ፤ የከምኒዝምን ኃይማኖታዊ ባሕሪ ለማሳየት ‘ነብዩ ማርክስ’ (MARX THE PROPHET) ብሎ የሰየመውን ምዕራፍ እንደ እዚኽ ብሎ ይጀምረዋል   ፦


“በአጋጣሚ አይደለም ከኃይማኖቱ ዓለም የተወሰደ ምሳሌ ወደ እዚኽ ምዕራፍ ውስጥ የገባው ። ከምሳሌነት ያለፈ መመሳሰል አለ ፤ ማርክሲዝም ኃይማኖት ነው ። ለአማኙ ፤ በመጀመሪያ ለሕይወት ትርጉም የእሚሰጡ የመጨረሻ ግብ የእሚባሉ እና ፍፁማዊ የኾኑ ክስተቶችን እና ተግባራትን የእሚመዝኑ መመዘኛዎች ሲያቀርብ ፤ በመቀጠል ደግሞ ከመዳኛ መንገድ ጋር የእሚመሳሰሉ ወደ እዚኽ ግብ የእሚያደርሱ እና ከፉውን በማመልከት ፤ ከእዚኽ ክፋት የተመረጡት የሰው ልጆች የእሚድኑበትን ያሳያል ። እንደገናም የማርክሲዝም ሶሻሊዝምን ፤ ከመቃብር በፊት ገነትን ለማውረስ ተስፋ ከእሚሰጡ ንዑስ ጎራዎች ልንፈርጀው እንችላለን ።”


“It was not by a slip of an analog from the world of religion was permitted to intrude into the title of this chapter. There is more than analogy. In one important sense, Marxism is a religion. To the believer it presents, first, a system of ultimate ends that embody the meaning of life and are absolute standards by which to judge events and actions; and, secondly, a guide to those ends which implies a plan of salvation and the indication of the evil from which mankind, nor a chosen section of mankind, is to be saved. We may specify still further: Marxist socialism also belongs to the subgroup which promises paradise on this side of the grave. [16]“


ያለፉት ታሪታዊ ክስተቶች ለምን እንደ ተከሰቱ ያለ ስኽተት አስረዳለሁ ፤ የወደፊቱንም ተስፋ እንቅጩን እተነብያለኹ በእሚለው በማርክሱ የታሪክ ቁሳዊነት ውስጥ ፤ ማሕብረሰባት ስድስት ታሪካዊ ደረጃዎች ይኖራቸዋል ።


ከእነ እዚኽ ስድስት የታሪክ ደረጃዎች መካከል የመጀመሪያዎቹን አምስቱን ፤ ጆሴፍ ስታሊን እንደ እዚኽ ያስቀምጣቸዋል ፦


  “በታሪክ አምስት ዓይነት የምርት ግንኙነቶች ይታወቃሉ ፤ ጥንታዊ ጋርዮሽ ፣ ባሪያ ፣ ፊውዳል ፣ ካፒታሊስት እና ሶሻሊስት።”

“Five main types of relations of production are known to history: primitive communal, slave, feudal, capitalist and socialist. [14]“


በእዚኽም መሠረት ፤ የሰው ልጅ ታሪክ ፤ በጥንታዊ የጋርዮሽ ስረዓት ይጀምራል ። በእዚኽ የጥንታዊ ጋርዮሽ ዘመን ፤ ሰዎች ኑሮዋቸው ኹሉ የጋራ ሆኖ ፤ ማንኛውም የማምረቻ መሳሪያዎች በግል ሰአይኾን  በጋራ በኹሉም ባለቤትነት የእሚተዳደሩበት ወቅት ነው ።


ከእዚኽ በመቀጠል የሰው ልጅ የገባበት ማሕበራዊ አወቃቀር  ፤ የባሪያ አሳዳሪ ስረዓት ነው ። በባሪያ አሳዳሪው ስረዓት ፤ የማምረቻ መሳሪያዎች ከማሕበራዊ የጋራ ባለቤትነት ወጥተው ፤ ኹሉም የማምረቻ መሳሪያዎች በባሪያ አሳዳሪው በግል ንብረትነት የተያዙበት ነው ። በባሪያ አሳዳሪው ስረዓት ጌታው ማምረቻ መሳሪያውን ብቻ ሰአይሆን በባለቤትነት የእሚይዘው ፤ ባሪያው ራሱም የባሪያ አሳዳሪው የግል ንብረት በመሆኑ ፤ ባሪያ አሳዳሪው ባሪያውን ፤ እንደ ማንኛውም ንብረት ፦ ሊገዛው ፣ ሊሸጠው ፣ ሊቀጣው እንዲኹም  ሊገድለው ፣ ለሌላ ሰው በተውሶ ሊሰጠው ፤ ሙሉ ስልጣን አለው  ።


ከእዚኽ በመቀጠል ፤ የፊውዳል ስረዓት ይመጣል ። ይኽ የፊውዳል ስረዓት ፤ ከባሪያ አሳዳሪው ስረዐት ጋር ፤ ሠራተኛውን ሙሉ በሙሉ እንደ ንብረት የራሱ አድርጎ የእሚይዝ እና ከአስፈለገም መሸጥ የእሚችል በመኾኑ ከባሪያ ስረዓት ጋር ሲያመሳስለው ፤ በሕይወት የማቆየት እና የመግደል ስልጣን ስለሌለው ከባሪያው ስረዓት ይለያል ።


በአራተኝነት ፤ የካፒታሊስት ስረዓት ይመጣል ። በካፒታሊስት ስረዓት ፤ ንብረት መሆን የእሚችለው ቁስ እንጂ ሰው አይደለም ። ይኽም በመሆኑ ካፒታሊስቱ የማምረቻ መሳሪያዎችን ብቻ በባለቤትነት ሲይዝ ፤ በሠራተኛው ላይ ግን እንደ ባሪያ አሳዳሪው እስከ መግደል የእሚያደርስ መብት ወይንም እንደ ፊውዳሉ በባለቤትነት የመያዝ መብት የለውም ። ስለ እዚኽ ፦ ካፒታሊስቱ ሠራተኛውን መቅጠር እንጂ ፤ መግዛት ፣ መሸጥ ፣ መግደል ፣ ወዘተ አይችልም ። ሆኖም ግን ሠራተኛው ድኃ ስለ ኾነ ፤ ሠራተኛውን በርካሽ ክፍያ እያሰራ ጉልበቱን ይበዘብዘዋል ።


አምስተኛው ደረጃ ሶሻሊዝም ሲኾን ፤ በእዚኽ ወቅት ፤ ካፒታሊስቱ በርካሽ ዋጋ እያሰራ ጉልበቱን የበዘበዘው ሠራተኛው ፤ አብዮት አካኺዶ ፤ ማምረቻ መሳሪያውን ከካፒታሊስቱ ወርሶ እና የሠራተኛው የጋራ ንብረት አድርጎ ፤ የእሚያመርተውን ምርት ፤ እንደ አዋጣው የሥራ ሰዓት ልክ ይከፋፈለዋል ። ይኽም ሶሻሊስታዊ ወይንም የጋርዮሽ (በማሕበር) የስልተ ምርት አወቃቀር ፤ እንደ ማርክስ ፦ ሠራተኛውን በካፒታሊስቱ ሲደርስበት ከነበረበት የጉልበት ብዝበዛ ያድነዋል ። ስታሊን ሶሻሊዝምን እንደ እዚኽ ይገልፀዋል ፦


“እዚኽ ደረጃ ላይ በዝባዥ እና ተበዝባዥ የለም ። የተመረቱት መልካሞች (ሸቀጦች) ፤ ‘የእማይሰራ አይበላም’ በእሚለው መርኽ መሠረት እንደ አዋጣው የሥራ መጠን ስለ እሚከፋፈል።”


 “Here there are no longer exploiters and exploited. The goods produced are distributed according to labor performed, on the principle : “He who does not work, neither shall he eat. [17]“


በስታሊን መዘርዘር ፤ የማርክስ የታሪክ ቁሳዊነት የእሚያስቀምጣቸው ፤ የማሕበረሰብ የእድገት ደረጃዎች ሶሻሊዝም ላይ ቢያቆምም ፤ ሶሻሊዝም ራሱ አንድ ደረጃ ወደ ፊት ኼዶ ፤ ኹሉም እንደ አዋጣው የሥራ ድርሻ ብቻ ሰአይኾን  እንደ የእሚያስፈልገው የእሚከፋፈልበት ፤ ወይንም የመጨረሻው ደረጃ ገነታዊ ከምኒዝም  እንደ ኾነ ማርክስ ይላል ፦


“የከምኒስት ማሕበረሰብ ከፍተኛውን ደረጃ ሲደርስ ፥ ሰዎች ባሪያ ለእሚያደርጋቸው የሥራ ክፍፍል ፥ በእዚኽም የሰው ተጻራሪ የኾነው የአዕምሮ እና የጉልበት ሥራ ክፍፍል ፈፅሞ ከጠፋ በኋላ ፤ ሥራ ለመኖር የእምንሰራው ነገር ሰአይኾን  የሕይወት ቀዳሚ ፍላጎት ሲኾን ፤ የማምረት ኃይላት ፥ የሰው ልጅ በኹሉ መስክ የአለገደብ አምራች በመኾን ሲገነባ እና ከእዚኽም የተነሳ የማሕበረሰብ የጋራ ማምረት አቅም ጎልብቶ ኃብት ተትረፍርፎ ሲፈስ ፤ ያን ግዜ የቡርዣው መብትን (የግል ንብረት ባለቤትነት) ተሻግሮ ማሕበረሰብ ፤ ‘ከኹሉም እንደ አቅሙ ለኹሉም እንደ ፍላጎቱ’ የእሚለውን መፈክር መጻፍ ይችላል ።”


“In a higher phase of communist society, after the enslaving subordination of the individual to the division of labor, and therewith also the antithesis between mental and physical labor, has vanished; after labor has become not only a means of life but life’s prime want; after the productive forces have also increased with the all-around development of the individual, and all the springs of co-operative wealth flow more abundantly—only then can the narrow horizon of bourgeois right be crossed in its entirety and society inscribe on its banners: From each according to his ability, to each according to his needs! [17]“


ይኽ ማርክስ የመጨረሻው ወይንም ከፍተኛው የከምኒዝም  ደረጃ ወይንም ከላይ በአስቀመጥኹት ቅደም ተከተል ፤ ከሶሻሊዝም በኋላ የእሚመጣው ማሕበራዊ መዋቅር ፤ ወይንም የከምኒዝም  ምድረ ገነት (Communist Utopia) እና የመጨረሻው የታሪክ ቁሳዊነት ደረጃ ፤ በሙግት ቁሳዊነት እየተዘወረ ማሕበረሰብ የእሚደርስበት የመጨረሻው እና የእማይሻረው ታሪካዊ ማሕበረሰባዊ የአወቃቀር ደረጃ ነው ።

እዚኽ ደረጃ ለመድረስ ግን ፤ መጀመሪያ የሰው ልጅ ይለወጥና አልችልም የእሚለው ሥራ አይኖርም ። ኹሉም ሰው ኹሉንም ነገር መሥራት የእሚችልበት ደረጃ ላይ ስለ እሚደርስ የሥራ ክፍፍል የእሚባል አይኖርም ። አንዱ ሰው ፤ ፓይለትም ፣ ዳክተርም ፣ አናጢም ፣ አስተዳዳሪም ፣ ገበሬም መኾን ይችላል ። ሞያ እና ሞያተኛ አንድ ለአንድ የእሚጣመሩበት ኺደት ይጠፋል ። 


በመጨረሻው የከምኒዝም ደረጃ ፤ የሞያ ክፍፍል ጠፍቶ ፤ ኹሉም ሰው ኹሉንም ነገር መሥራት የእሚችል እና ሥራም ሱሱ ይኾናል ብቻ አይደለም ማርክሲዝም የእሚለው ፤ ይኽ የከምኒዝም ደረጃ ኃይማኖትን ፣ መንግሥትን በአጠቃላይ በሰዎች መካከል ልዩነትን ኹሉ ያጠፋልም ይላል ፦


“ነገር ግን ፤ ከምኒዝም  የእምንለው የታሪካዊ እድገት ደረጃ ላይ ስንደርስ አኹን ያሉት ኃይማኖቶች በሙሉ ጥቅም አልባ በመኾን ይጠፋሉ ።”


“But communism is the stage of historical development which makes all existing religions superfluous and brings about their disappearance. [18]“ 


ሞያ እና ኃይማኖት ብቻም አይደለም ፤ የግል ንብረት ፣ መንግሥታት ፣ ሐገራት እና ዜግነቶች ይጠፋሉ ይላል ማርክስ ፤ ከምኒዝም  የመጨረሻው ደረጃ ላይ ሲደርስ ፦


“የሕዝብ የተለያዩ ዜግነቶች ራሳቸውን በማሕበራዊ ሕጉ እንዲያስተባብሩ ኹኔታው እያስገደዳቸው ፤ ለመቀላቀል  የተናጠል ሕልውናቸውን ያከስማሉ ፤ ልክ የተለያዩ መደቦች እና የኃብት ግዛቶች መሰረታቸው የኾነው የግል ንብረት ባለቤትነት ሲሻር እንደ እሚጠፉት ።”


“The nationalities of the peoples associating themselves in accordance with the principle of community will be compelled to mingle with each other as a result of this association and thereby to dissolve themselves, just as the various estate and class distinctions must disappear through the abolition of their basis, private property [18].” 


ስለ እዚኽ ከምኒዝም  ወይንም በሙግት ቁሳዊነት የእሚመራው ቁሳዊ ታሪክ ወይንም የማሕበረሰብ ታሪክ ፤ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስ ፤ ሐገር ፣ ኃይማኖት ፣ ሞያ ፣ ቤተሰብ በአጠቃላይ ይጠፉ እና ዓለም ልዩነት እና ግጭት የሌለባት ፤ ሰዎች በፍፁም ነፃነት እና እኩልነት (“አንድ ዓይነትነት”) የእሚኖሩባት ትኾናለች ። 


የስታሊን አምስት የማሕበረሰባዊ የእድገት ደረጃ ዝርዝር ላይ ፤ ማርክስ የመጨረሻው ደረጃ የአለውን የታሪክ ቁሳዊነት ደረጃ ስንጨምርበት ወይንም በካርል ማርክስ ፥ የታሪክ ቁሳዊነት መሠረት ፤ ማሕበረሰብ ፤ በመደብ ግጭት እየተመራ ፤ የእሚከተለውን የማሕበረሰብ አወቃቀር ተራ በተራ እየያዘ ይኼዳል ፦


1.    የጥንታዊ ጋርዮሽ ስረዓት

2.    የባሪያ አሳዳሪ ስርዓት

3.    የባላባት (የፊውዳል) ስረዓት

4.    የቡርዥዋዚ (የካፒታሊስት) ስረዓት

5.    የሶሻሊዝም ስረዓት

6.    በስተመጨረሻም መደብ ፣ መንግሥት ፣ ኃይማኖት የሌለበት በእዚኽም የመደብ ግጭት የሌለበት ምድረገነት ወይንም ጋርዮሽ ይኾናል የእሚል ነው ።


ይኽንንም መላ ምታቸውን ይዘው ፤ ማርክሲስቶች ፦ የካፒታሊስት ስልተ ምርት ላይ የደረሰው ማሕበረሰብ የሠራተኛ መደባት ፤  በእውቀት የታጠቁት እና የነቁ በመሆናቸው ፤ ሌላውን የዓለም ጭቁኖች ( ባሪያውን ፣ ጭሰኛውን ) በከምኒስታዊ የመደብ ትግል አስተውሎ እየመሩ ፤ የዓለም ጭቁኖች አብዮት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በማድረግ ፤ የከምኒስት አብዮትን በማቀጣጠል ፤ ወደ ዓለም ዓቀፋዊ መደብ አልባ የጋርዮሽ ምድራዊ ገነት የእሚደረገውን ጉዞ ማቀላጠፍ አለባቸው አሉ።


ስለ እዚኽ ፦ ማርክሲስቶች ፦ ታሪክ ተፈጥሮዋዊ ጉዞውን ያደርግ ዘንድ ፤ ማለትም ማሕበረሰብ ወደ መደብ የለሹ የማሕበረሰብ አወቃቀር ይደርስ ዘንድ ፤ በቡርዥዋ ወይንም በካፒታሊስቱ እና በሠራተኛው መካከል የመደብ ትግል ሊካኼድ ይገባዋል ወይንም ይኽን የመጠፋፋት ደም አፋሳሽ የመደብ ትግል ፤ የእማይቀር ታሪካዊ እና ተፈጥሮዋዊ ግዴታ አድርገው አስቀመጡት ። 


ይኽንም ተከትለው ማርክሲስቶች ፤ እውቀታችን ፍፁም እና የእማይሻር ነው ፤ እርሱም በተፈጥሮዋዊ እና በእማይቀረው የመደብ ትግል መርህ ማሕበረሰብ አኹን ከአለበት እና ሠራተኛው ጉልበቱ በካፒታሊስቱ ከእሚበዘበዝበት ስልተ ምርት ፤ በደም አፋሳሽ የመደብ ግጭት አብዮት ፤ ታሪክ ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም ፥ ከሶሻሊዝም ወደ ከምኒስታዊ ገነት ይሸጋገራል አሉ ።


እነ እዚኽም በካፒታሊስቱ ሐገራት ውስጥ ያሉ የሠራተኛ መደባት ትግሎች ፤ ሌላው ኋላ ቀሩን የዓለም ሕዝብ ወደ ኮምኒስታዊ ምደረ ገነት የእሚደረገውን ትግል እንዲቀላቀል መምራት አለባቸው አሉ። 


በእዚኽም ምክንያት ፤ በመደብ የመጠፋፋት ትግል ውስጥ ገብቶ ፤ ጭቁኑ የሠራተኛው መደብ ፤ ጨቋኙን የባለኃብት ፣ የቡርዣ ወይንም የካፒታሊስት መደብ  በመደምሰስ ፤  ሶሻሊስታዊ ስረዓትን በአብዮት ፤ በግዜ ኺደት ደግሞ ኮምኒስታዊ ምደረ ገነት ይገነባል ። 


 

ሠንጠረዥ  2፡ የማርክሲዝም ርዕዮት የፍልስፍና መዋቅር።


ይኽን መሰል መልክ የአለውን ማርክሲዝም በቁሙ ስንመዝነው ፤ መግቢያችን ላይ ፤ ማርክሲዝም ፤ የመንገደኛ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የሆነውን ተጨባጫዊነት ሳይንሳዊ ለምድ ለማልበስ የእሚሞክር እንጂ በይዘቱ የመንገደኛው ፖለቲካዊ ፍልስፍና (A Pedestrian Political Philosophy) የሆነው ተጨባጫዊነት ነው ያልኩበት ምክንያት ግልፅ ይሆናል ።


በዝርዝር እንደ አየነው በማርክሲዝም ፍልስፍና ውስጥ ፤ በሙግት ቁሳዊነት ምክንያት ብቸኛው እና ትክክለኛው የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ አብዮት ነው ። አብዮት ሲባል ደግሞ ፤ የአስተሳሰብ ፣ የአደራረግ እና የአደረጃጀት እድገት ወይንም ምጥቀት አምጭ አብዮት ሰአይሆን ፤ ደም አፋሳሽ የሆነ ፤ የመደብ በአላንጣን ፈጽሞ ማጥፋት እና ማዳከም ሊለወጥ የእማይችል መንገዱ እና ግቡ የአደረገ አብዮትን ግድ የእሚል አብዮት ነው ። በአጭሩ ማርክሲዝም ፤ ሳይንሳዊ ካባ የለበሰ ማካቬልያዊነት ነው ።


ይኽንንም ማርክስ እና ኤንግልስ ፤ የጀርመን ኃሳባዊነት ተብሎ በስማቸው በታተመው መጽሐፍ ውስጥ የደም አፋሳሹን አብዮት አስፈላጊነት ፦ በእነርሱ ርዕዮት መሠረት የፖለቲካ ስልጣን የእሚያዘው በደም አፋሳሽ አብዮት ብቻ በመሆኑ እና ይኽን መሰሉ ደምሳሽ አብዮትም የቀድሞውን አሮጌ አሰራር ቅሬታ ለማጥፋት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለው ፤ አብዮት ከእሚደረግበት ምክንያት አንዱ ፤ በማርክሲስት ርዕዮት መሠረት ትክክለኛው የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ደም አፋሳሽ አብዮት ስለ መሆኑ ፤ ይኽን ይላሉ ፦


“…አብዮት አስፈላጊ የሆነው ፤ ገዢው መደብ ከአብዮት ውጭ በሌላ መንገድ ሊወገድ ስለ እማይችል ብቻ ሰአይሆን ፤ ገዢውን መደብ በአብዮት አስወጋጁ መደብ ራሱን ዘመናት ከለጠፉበት እድፍ (ጭቃ ፣ ሊጥ ፣ ግራሶ) አላቆ አዲስ ማሕበረሰብን ለመመሥረት ስለ እሚያስችለውም ጭምር ነው።”

“…the revolution is necessary, therefore, not only because the ruling class cannot be overthrown in any other way, but also because the class overthrowing it can only in a revolution succeed in ridding itself of all the muck of ages and become fitted to found society anew. [15]“


በእዚኽ ገለጻቸው ፤ ማርክሲስቶች የፖለቲካ ስልጣን የእሚያዘው በአብዮት እና በአብዮት ወይንም በኃይል እና በኃይል ብቻ እንደ ሆነ በእማያሻማ መልኩ አስቀምጠዋል።


ይኽም ፤ የፖለቲካ በአላንጣን ያለምንም ማመንታት እና ሊለወጥ በእማይችል መልኩ የማጥፋት ግብ እና የፍልስፍናው አቅም በሰጠው ተቀባይነት ምክንያት ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለምዕተ ዓመት ለእሚጠጋ ቆይታ የፖለቲካዊ ጽንፈኝነት ቁንጮ ሆኖ መቆየቱ ፤ ማርክሲዝምን የፖለቲካዊ ፅንፈኝነት ዳሰሳችን ዋነኛ ርዕስ አድርጎታል ።


ማርክሲዚም ፤ የማካቬሊያዊነት ሳይንሳዊ ለምድ ወይንም ማስመሰያ ካባ ብቻም ሰአይሆን ፤ ካባ አድርጎ የአቀረበው ሳይንሳዊነት ፤ በፅንሰ ኃሳብ እና በተግባር መፈተኛ ሲፈተሽ ግድፈት የአለበት ነው። 


የእሚከተሉት ነጥቦች ፦ የማርክሲዝም ሳይንሳዊነት የአሉበትን ግድፈቶች እና የማርክሲዝምን አሉታዊ ገጽታዎች ያሳዩናል ፦

 

1.    ፍልስፍናን እና ሳይንስን በማምታት ፤ ፍልስፍናዊ እምነቱን ሳይንሳዊ አድርጎ ለማቅረብ ይሞክራል

2.    ኢሳይንሳዊ ነው ፡ ማለትም የቲየሪ እና የዳታ ተቃርኖ አለው

3.    ጸረ ሳይንስ ነው ፤ ነባራዊው የሳይንስ እውቀት መሻር አለበት ይላል

4.    ህሊናቢስ ወይንም ጸረ ስነምግባራዊ ነው

5.    ጠንሳሾቹን ጨምሮ ተግባሪዎቹ ፤ ለሳይንሳዊነቱ ሰአይሆን ለእሚያስገኘው ስልጣን ቅድሚያ በመስጠት ፤ ከፍልስፍናቸው በታቃራኒ ሲንቀሳቀሱ በመኖራቸው ፤ የራሳቸው ተግባር ለኢሳይንሳዊነቱ ምስክር ነው ።

6.    እነ እዚኽም መሠረታዊ ችግሮቹ ፤ ማርክሲዝምን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሲተገበር ፤ ከፍተኛ የሆነ ኢከነሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ እንዲያስከትል አድርጎታል

እነ እዚኽን ነጥቦች ተራ በተራ በዝርዝር እንመልከታቸው ።


1.    ፍልስፍናን እና ሳይንስን ማምታት

በፍልስፍና እና በሳይንስ መካከል መሠረታዊ ልዩነት አለ ። 

ምንም እንኳን ኹለቱም ፥ ፍልስፍና እና ሳይንስ ፦ በወጉ የተዋቀረ የአስተሳሰብ ስረዓት የአላቸው ቢሆኑም ፤ በፍልስፍናው መስክ በአንድ ጥያቄ ላይ የተለያየ ምላሽ የእሚሰጡ የአስተሳሰብ መዋቅር የአላቸው ፍልስፍናዎች ይኖራሉ ፦


“የፍልስፍና ስረዓት የአንድ ነጠላ ፈላስፋ ፍልስፍና የያዘ ልዩ እና ብቸኛ መዋቅር ነው ። የጋራ እና ዓለም ዓቀፋዊ የሆነ የፍልስፍና ስረዓት የለም …”

“The Philosophical System is a unique and singular one which constitutes the philosophy of one individual thinker. There is no objective and universal philosophical system … [19]“ 


  ከፍልስፍናው በተቃራኒ ፤ በሳይንሱ መስክ ግን ለሳይንሳዊ ጥያቄ የተሰጠ መልስ ከአለ ፤ መልሱ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት የአለው ነው ። የአንድ ሦሥት መዓዘን ስፋት የእሚለካበት ቀመር አንድ ግዜ ከተቀመረ እና ትክክልኛነቱ ከተረጋገጠ ፤ ያ ቀመር በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የጋራ ተቀባይነት የአለው ነው ። አንድ የሒሳብ ሊቅ ፤ አይ እኔ የእዚኸኛው የፍልስፍና ትምህርት ቤት ደቀ መዝሙር ነኝ እና ይኽንን የሦሥት መዓዘን ስፋት መለኪያ ዘዴ አልቀበለም ሊል አይችልም። 


በፍልስፍና እና ሳይንስ መሐከል የአለው ልዩነት ይኽ ሆኖ ፤ የሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ብቸኛው ወኪል ነኝ የእሚለው ማርክሲዝም ፤ የተመሠረተበት ቁሳዊነት ወይንም በዓለም ላይ በተጨባጭነት የአለው ፤ ማንም ሳይፈጥረው በራሱ የእሚኖረው ቁስ ነው እና የመኖሪያ መርሁም በውስጡ የእሚገኙትን ተቃርኖዎች በእማያቆም ግጭት ማጥፋት ነው የእሚለው እምነቱ ፤ ፍልስፍና እንጂ ሳይንስ አይደለም ። 


ምክንያቱም ይኽ ከላይ የገለጽነው እና የማርክሲዝም መሠረት የሆነው ቁሳዊነት (Materialism) የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ በእሚባለው የፍልስፍና (Metaphysics) መስክ የአለ ፤ አንድ ዓይነት የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ እንጂ ዓለም ዓቀፋዊ ወጥ ተቀባይነት የአለው ሳይንሳዊ ድምዳሜ ወይንም እውቀት አይደለም ። 


ቁሳዊነት የእሚባለው ዘውግ ፤ በልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ (Metaphysics) መስክ እንደ አለው ፤ ይኽንን ቁሳዊነት የእሚቃወሙ ኃሳባዊያን (Idealist or Dualist) የእሚባሉ እና ይኽ የእምናየው ቁሳዊ ዓለም በመንፈስ ወይንም በአንድ የእማይታይ ኃይል የተፈጠረ ነው የእሚሉ እና እንደ ቁሳዊያውኑ የራሳቸው ሙግት የእሚያቀርቡ  ተቃራኒ ጎራዎች ያሉ በመሆናቸው እና በእነ እዚኽ ኹለት ተቃራኒ የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ መላምቶች መካከል የአለው ልዩነትም ፤ በሺ ዓመታት የእሚቆጠር እድሜ የአለው ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በሳይንሳዊ መንገድ ሊፈታ ያልቻለ እና በሰዎች ፈቃዳዊ ምርጫ ብቻ የእሚያዝ አመለካከት ወይንም እምነት ነው ።

 ለምሳሌ ፦  እንደ እነ ዴሞክሪተስ እና ሔራክሊተስ ፤ ዓለም እና የእምትመራበት ውስብስብ ተፈጥሮዋዊ ሕግጋት ሳይፈጠሩ ድሮውንም በራሳቸው ግዜ ነበሩ እና ከቁሱ ውጭ ምንም የለም ብሎ ማመንን የመረጠ  ሰው ፤ ግዑዙ ዓለም ከባዶ ወይንም ከምንም (Out of Vacuum) እንዴት በራሱ ግዜ ሊፈጠር እንደ እሚችልና ፤ ሕይወት የአላቸው ነገሮች ፤ በግዑዝ ንጥረ ነገሮች ግጭት ብቻ እንዴት ሊፈጠሩ እንደ እሚችሉ ፤ ለምሳሌ ፦ የእነ ሊውስ ፓስተርን (Louis Pasteur) ፖስቸራይዜሽን  መሰል ፤ ከግዑዝ ነገር ሕይወት የአለው ነገር ሊመጣ አይችልም የእሚሉ ፤ ተግባራዊ እና ሳይንሳዊ ከልካይ ማስረጃዎችን ተሻግሮ ማስረዳት አለበት ። 

ቁሳዊነት ሳይንሳዊ የመኾን ፈተና እንደ አለበት ኹሉ ኃሳባዊነትም (Idealism) ተመሳሳይ ፈተና አለበት ። እግዚአብሔር ፣ መንፈስ ወይንም ነፍስ አለ ፤ ይኽ የእምናየው ዓለም የእግዚአብሔር ሥራ ነው ፤ የሰውም እንቅስቃሴ ከመንፈሱ ወይንም ከነፍሱ ነው የእሚመነጨው የእሚለው ሰው  ፤ የእማይታዩትን እግዚአብሔርን ፣ መንፈስን ወይንም ነፍስን የማሳየት ፈተና አለበት ። 


ዋናው ቁም ነገር ፤ የልዕለ ተፈጥሮ (Metaphysics) ተቃራኒ ዘውግ የኾኑት ፤ ቁሳዊነት (Materialism) እና ኃሳባዊነት (Idealism) ፤ መሳ ለመሳ የእሚቆሙ የፍልስፍና መስኮች ኾነው ፤ ልዩነታቸው በሳይንሳዊ መርህ ሊፈታ የእማይችል የልዕለ ተፈጥሮ ተጻራሪ ዘውጎች ናቸው  ።


እውነታው ይኽ ቢሆንም ፤ ሳይንሳዊ ነኝ የእሚለውን ማርክሲዝም ከቁሳዊነት ፍልስፍናው ከለየነው ፤ የሙግት ቁሳዊነት እና የታሪክ ቁሳዊነት መላምቶቹ በሙሉ እንደ ተበሳ ጎማ ነው የእሚተነፍሱት ። 


ምክንያቱም ፦ የሙግት ቁሳዊነት ውጤት የሆነው የተጻራሪ መደባት ትግል አስተውሎ (The antagonistic class consciousness) ፤ በገኃድ የአለው ቁስ ብቻ ነው እና ቁሱም የእሚመራው በተቃርኖ ግጭት ነው ፤ የእሚለው ቁሳዊነት ከሌለ መኖር አይችልም ። የመደብ ግጭት ከሌለ ደግሞ ፤ የታሪክ ቁሳዊነት እንደ እሚለው በማሕበረሰብ ውስጥ ተቃራኒ መደቦች እየተጋጩ ፤ ማሕበረሰብ ከባሪያ አሳዳሪ ስረዓት ወደ ፊውዳል ስረዓት ፣ ከፊውዳል ስረዓት ወደ ቡርዥዋ ወይንም ካፒታሊስት ስረዓት ፣ ወዘተ ፤ ሊቀየር አይችልም ።


ይኽም በመሆኑ ማርክሲዝም ፤ ምንም እንኳን ሳይንሳዊ ነኝ ቢልም ፤ ሳይንሳዊ አይደለም ፤ ምክንያቱም ፦ ሳይንሳዊ ሰአይሆን ፍልስፍናዊ ከሆነው ቁሳዊነቱ መሠረቱ ውጭ ህልውና ስለ ሌለው ።


ይኽም በመሆኑ ፤ ማርክሲስቶች ማርክሲዝም እንደ ፊዚክስ ፣ ኬሚስትሪ ፣ ወዘተ ፤ ውስጥ እንደ አሉ ፤ ለምሳሌ ፦ ኹለት የውኃ ዐተሞች እና አንድ የዖክስጂን ዐተም ሲዋኃዱ አንድ የውኃ መለኪውል ይፈጠራል እንደ እሚሉት የተፈጥሮ ሳይንስ ሕግጋት ፤ የእማይሻር እና ኹሉም ሰው ሊቀበለው የእሚገባው ብቸኛ እና ትክክለኛ ሳይንሳዊ የማሕበረሰብ መመሪያ ሕግ ነው ብለው ማቅረባቸው ፤ ተራ ኬሚስት ነን ባይ አልኬሚስቶች (Alchemists) ከተራ ብረት ወርቅ እናወጣለን ዓይነት አጉል ድፍረት እና ድርቅና እንጂ ሳይንስ አይደለም ማለት ነው ።


2.    ኢሳይንሳዊ ነው


ማርክሲዝም ሳይንሳዊ ነኝ እያለ ፤ ሳይንሳዊ በአልሆነ ፍልስፍና ላይ የመ፟መ፟ሥረት ስህተት ብቻ ሰአይሆን የእሚሰራው ፤ ከእዚኽ በአሻገር የእሚያስቀምጣቸው እና ሰው ኹሉ ሳያወላዳ እንደ እማይለወጡ የሳይንሳዊ ኃቅ ሊቀበላቸው ይገባል እያለ የእሚያስቀምጣቸው መላምቶች ፤ የፅንሰ ኃሳብ መጣረስ ያለባቸው እና ከፅንሰ ኃሳብ መጣረስም በአሻገር ፤ ከታሪካዊ ኃቆች ጋር የእማይገጥሙ ናቸው ወይንም የቲየሪ እና የዴታ ተቃርኖ ያዘሉ ናቸው ።


ይኽን ለማሳየት ፤ ከማርክሲዝም ቲየሪ ሦሥት የፅንሰ ኃሳብ ተፋልሶዎችን እና የተወሰኑ ታሪካዊ ክስተቶች በማሳያነት በማቅረብ ፥ ታሪካዊው ኃቅ ከመላምቱ ጋር እንደ እማይገጥም እንመልከት ።


ከፅንሰ ኃሳብ አንፃር የመጀመሪያውን መጣረስ የእምናገኘው ፤ ማርክሲዝም ጥንታዊው የጋርዮሽ ስረዓት ወደ ባሪያ አሳዳሪ ስረዓት የተለወጠበትን መንገድ በእሚያብራራበት ወቅት ነው ። 


በማርክሲዝም መሠረት ፤ ከላይ የተጠቀሱት ስድስት የማሕበረሰብ የእድገት ደረጃዎች ፤ ከማሕበራዊ የቁስ ኹኔታ ልዩነት በእሚመነጭ መደባዊ አስተውሎ ልዩነት እናም ይኽ የመደባዊ አስተውሎ ልዩነት በእሚፈጥረው ተቃርኖዎቹ እየተነዱ ነው ፤ ከአንድ ስልተ ምርት ወደ ሌላ ስልተ ምርት ወይንም መሐበራዊ አወቃቀር የእሚሸጋገሩት ተብሏል ።


ይኽ ከኾነ ግን ፤ ኹሉም የማምረቻ መሳሪያዎች በጋራ የማሕበረሰብ ንብረት በኾኑበት እና ከተራ ጥቃቅን ንብረቶች በስተቀር የግል ንብረት የእሚባል በአልነበረበት በመጀመሪያው ጥንታዊ ጋርዮሽ ስረዓት ፤ ስለ እዚኽም ፦ ተቃራኒ መደባዊ ግንዝቤ ሊፈጥሩ የእሚችሉት የተለያዩት ቁሳዊ (ኢከነሚያዊ) ኹኔታዎች በሌሉበት እንዴት ባሪያ እና ጌታ የእሚባሉት ተቃራኒ መደቦች ሊፈጠሩ ቻሉ?


በአጭሩ ፤ የሕዝብ ፖለቲካዊ ግንዛቤ ከቁሳዊ (ኢከነሚያዊ) ኹናቴ ብቻ የእሚመነጭ ከኾነ ፤ በአንድ ዓይነት የቁሳዊ (ኢከነሚያዊ) ኹኔታዎች ውስጥ የነበሩት ጥንታዊ ማሕበረሰባት ፤ በውስጣቸው እንዴት የተለያዩ እና ተቃራኒ መደቦች በመፍጠር ባሪያ እና ባሪያ አሳዳሪ ብለው የመደብ ተቃርኖ በማምጣት ወደ አዲስ ስልተ ምርት ሊሸጋገሩ ቻሉ? 


የሰዎች ኢከነሚያዊ መዋቅር ፤ መጀመሪያ ከጥንታዊ ጋርዮሽ ወደ ባሪያ አሳዳሪ ስረዓት ነው የተቀየረው የእሚለው ጉዳይ የአለው ታሪካዊ ቋሚ እውንነት አጠያያቂ መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ፤ የማርክስን የሙግት ቁሳዊነት ለመፈትን ስንል ብቻ እንደ ታሪካዊ እውን ብንወስደው እንኳን ፤ የሰው ግንዛቤ ከቁሱ ወይንም ከነባራዊው ኢከነሚያዊ መዋቅር ብቻ የእሚመነጭ ከሆነ ፤ የሰውል ልጅ በእኩልነት በጋራ ፍራፍሬ ለቃቅሞ እና አድኖ ከእሚኖርበት ማሕበራዊ አደረጃጀት ፤ ሰዎች ከማርክሲዝም አስተሳሰብ በተቃራኒ አስተውሎታቸው አከባቢያቸውን ወይንም ሕይወታቸውን እንዲለውጡ ከአላደረጋቸው ፤ ጥቂት ባሪያ አሳዳሪዎች ብዙውን ሰው ባሪያ ወደ እሚያድርጉበት ሊመጡ አይችሉም ።


በተመሳሳይ ቁሳዊ ኹኔታ ውስጥ ሆነው ሰዎች የተለያየ የአስተሳሰብ እና የግንዛቤ ቅርጽ ይዘው ፤ ባሪያ እና ባሪያ አሳዳሪ ሆነው ሊከፋፈሉ የእሚችሉት ፤ ከማርክስ የሙግት ቁሳዊነት መላምት በተቃራኒ ፤ ሰዎች ከእሚኖሩበት ቁሳዊ ኹኔታ በተለየ መልኩ ግንዛቤ የእሚያገኙበት ሌላ ተጨማሪ መንገድ ከኖረ ብቻ ነው ።


ይኽም ብቻ ሰአይኾን ፤ በእነዚኽ ስድስት የማሕበረሰብ የእደገት ደረጃዎች ፤ ማርክሲዝም የመጨረሻው ስድስተኛው የእድገት ደረጃ ላይ የደረሰ ማሕበረሰብ ፤ አንድ ዓይነት ቁሳዊ ኹኔታ ላይ በመድረሱ ከማሕበረሰቡ ውስጥ ተቃርኖ ስለ እሚጠፋ የመደብ ትግል ላይመለስ ለዘላለም ይጠፋል ይላል ። 


ተመሳሳይ ምህዳር የአለው የመጀመሪያው ጋርዮሽ (Communism) በባሪያ አሳዳሪ ስረዓት ተተክቷል የአለው ማርክሲዝም ፤ በዘፈቀደ የመጨረሻው ጋርዮሽ ፀንቶ ይኖራል በማለቱ ፤ ከላይ ያስቀመጥነው ተፋልሶ በሌላ መንገድ እንደገና እየደገመው ነው ። ምክንያቱም ፦ ዳያለክቲክሱ (ሙግቱ) መለወጥ የእማይችል እና ኹል ግዜ የነበረ የተፈጥሮ ሕግ ከኾነና የእሚመነጨውም ከቁሳዊው ዓለም ስሪት ከሆነ ፤ ጥንታዊው ከምኒዝም መደብ አልባ ኾኖ መቀጠል ከአልቻለ አዲሱ እና የመጨረሻው ከምኒዝምም መደብ አልባ ኾኖ በምን ምክንያት ሊቀጥል ይችላል?

 

በአዲሱ ከምኒዝም የሰው ሰብዓዊ ባሕሪ ስለ እሚቀየር ነው መደብ የእሚጠፋው ከተባለ ፤ ግንዛቤ የቁሱ ዓለም ነፀብራቅ ነው እንጂ የራሱ ህልውና የለውም የእሚለው የሙግት ቁሳዊነት ወይንም የማርክስ ዲያሌክቲክ ልክ አይደለም ማለት ነው ።

 

ምክንያቱም ፦ የቁስ ሙግት ቋሚ እና የእማይሻር የተፈጥሮ ሕግ ነው ብለን ፣ ከእዛም ይኽ ቁስ የእውቀት ምንጭ ነው ብለን ፣ ከእዛም የሰው ልጅ እውቀት በቁሱ የእማይመራበት ደረጃ ላይ ይደርሳል እያልን መኾኑ ስለኾነ ።

 

ይኽም ብቻ ሰአይኾን ፤ ሰው በታሪክ ከታወቀበት ግዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ሰብዓዊ ባሕሪው ሲለወጥ ታይቶ ስለ እማይታወቅ እንዲኽ ዓይነት ‘ትንቢታዊ’ ድፍረት ሳይንስ ሊኾን አይችልም ። እንደ እዚኽ ዓይነቱን መሠረት የለሽ ‘ሳይንሳዊ’ ትንበያ ነው ቶማስ ማልተስ በእሚከተለው መልኩ የተቃወመው ፦


 “ወደ አንድ ሙግት ውስጥ በእምገባበት ወቅት ፤ በሳይንሳዊ መርኽ ላይ የእማይመሠረቱ ፤ በሬ ወለደ ወይንም አቡኑ ሰጠኝ ዓይነት መከራከሪያዎችን ከጥያቄ ማውጣት አለብኝ ። አንድ ሰው ፦ የሰው ልጅ ኼዶ ኼዶ ፤ አንድ ቦታ ላይ ሰጎን ይኾናል ብሎ እንደ እሚያምን ፤ ሊነግረኝ ይችላል ። እንዲኽ የእሚለኝን ሰው በአግባቡ አይኾንም ብዬ ልሞግተው አልችልም ። ይኽን ዓይነቱ ሰው ግን ፤ የማመዛዘን አቅም የአለውን ማንኛውንም ሰው በኃሳቡ ከማሳመኑ በፊት ፦ የሰው አንገት ቀስ በቀስ እየሰለለ እና እየረዘመ መኼዱን ፥ ከንፈሩም እየጠረረ እና እየሾጠጠ መኼዱን ፥ እግሩ እና እጁ በእየቀኑ ቅርፃቸውን እየለወጡ መኾናቸውን ፥ ፀጉሩም ወደ ላባ ሰበዝነት እየተቀየረ መኾኑን ማሳየት አለበት ።”

“In entering upon the argument, I must premise that I put out of the question, at present, all mere conjectures, that is, all suppositions, the probable realization of which cannot be inferred upon any just philosophical grounds. A writer may tell me that he thinks man will ultimately become an ostrich. I cannot properly contradict him. But before he can expect to bring any reasonable person over to his opinion, he ought to shew that the necks of mankind have been gradually elongating, that the lips have grown harder and more prominent, that the legs and feet are daily altering their shape, and that the hair is beginning to change into stubs of feathers. [20]“


እንደ ገና በሌላ ማሳያም ፤ ምንም እንኳን ማርክሲዝም ፤ የአንድ ሕዝብ የማሕበረ ኢከነሚ (ቁሱ) ኹኔታ የፖለቲካ ግንዛቤው ብቸኛ ምንጭ ነው ፤ ስለ እዚኽ ተቀራራቢ ወይንም ተመሳሳይ ማሕበረ ኢከነሚ የአላቸው ሕዝብ ተመሳሳይ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ይኖራቸዋል ቢልም ፤ ሚሎቨን ዲለስ ፤ በፈረንሳይ እና በጣሊያን ፤ ከራሺያ ጋር ተመሳሳይ የማሕበረ-ኢከነሚ ምህዳር ቢኖርም ፤ በእነዚኽ ሐገራት የሶሻሊስት አብዮት ሊሳካ እንደ አልቻለ ይነግረናል  ፦


“ስለ እዚኽም ፤ በፈረንሳይ እና በጣልያን አብዮት ስኬት ራቀው ። ምክንያቱም ፦ ፖለቲካዊ ዴሞክራሲ በዳበረበት ምህዳር ውስጥ በመኖራቸው ፤ የሐገሬው ከምኒስቶች ራሳቸው ከፓርላማ ማማለል ነፃ ማድረግ አልቻሉም ። በእዚኽም ፤ አብዮትን በተመለከተ በዓለም ዓቀፉ የከምኒዝም  እንቅስቃሴ እና በሶቭየት ሕብረት ራሺያ ላይ ነው የተደገፉት ከራሳቸው አብዮታዊ አቅም ይልቅ ። የእነዚኽ ተከታዮች ደግሞ ፤ መሪዎቻቸው ለዲሞክራሲ እድገት እና ለሰቆቃ ማብቃት የእሚታገሉ እየመሰላቸው ፤ ለጋው አዕምሮዋቸው በመሪዎቻቸው እንዲያምኑ አደረጋቸው ።”


“Therefore, in France and Italy revolution did not have а real chance. Since they were living and operating in an environment of political democracy, even the leaders of their Comunist parties were notable to free themselves entirely of parliamentary illusions. As far as revolution was concerned, they tended to rely on the international Communist movement and the aid of the U.S.S.R than on their own revolutionary power. Their followers, considering their leaders to be fighters against poverty апd misery, naively believed that the party was fighting for а broader and truer democracy. [11]“


ኹለተኛው የማርክሲዝም ፅንሰ ኃሳባዊ ስህተት ማሳያ የእሚኾነው ካርል ማርክስ ለኢከነሚክስ ሳይንስ የአለው ባይተዋርነት ነው ። ምንም እንኳን ማርክስ እና ኤንግልስ ፤ ዳስ ካፒታል የተባለውን ባለ ሦሥት ጥራዝ ትልቅ የካፒታሊዝምን ስረዓት ኢከነሚክስ የእሚተች መጽሐፍ ቢጽፉም ፤ በዘመናዊው የኢከነሚክስ ካሪኩለም ውስጥ አንዱም ትችታቸው ውኃ የእሚቋጥር ሆኖ ተቀባይነት አልተሰጠውም ።


ይኽም ማርክስ ቀላል የእማይባል የኢከነሚክስ ሳይንስ ግንዛቤ እጥረት እንደ አለበት ማሳያ ነው።

ማርክስ በካፒታሊስት የኢከነሚክስ ስረዓት ላይ የአቀረበው ኂስ ጭብጥ ይኽንን ይመስላል ፦ በፍትኃዊ ዓለም ብንኖር ኖሮ ፤ የኢከነሚ ትርፍ የእሚባል ነገር መኖር አልነበረትም። እስከ ዛሬ በእሚታወቀው ፤ በተለይም በካፒታሊስቱ ስረዓት ውስጥ የኢከነሚ ትርፍ መኖር የቻለው ፤ የጉልበት ብዝበዛ ስለ አለ ነው። ሰዎች ኹሉ ያለ ጉልበት ብዝበዛ አምራች ቢሆኑ የኢከነሚ ትርፍ ይጠፋ እና አንዱ ኃብታም ሌላው ድኃ የእሚሆንበት ኹኔታ አይኖርም ነበር የእሚል ነው።


ይኽ የተሳሳተ የማርክስ አስተሳሰብ እውን እንዲሆን ግን ሌላው የተሳሳተው እና ለእዚኽ አስተሳሰብ መሠረት የሆነው የማርክስ ኢከነሚያዊ አስተሳሰብ እውነት መሆን አለበት ፤ ይኽም የማርክስ አስተሳሰብ እንደ እዚኽ ይላል ፦ የሸቀጦች ዋጋ ሸቀጦቹን ለማምረት በዋለው የሥራ ሰዓት ልክ ይወሰናል ይላል ፦


“ስለ እዚኽ ፦ መጠቀሚያ እሴት ወይንም የእሚጠቅም ቁስ ፤ ዋጋ  የአለው ፤ የሰው ጉልበት በረቂቅነት በወስጡ ስለተዋኃደ ወይንም ስለ ተካተተ ነው።”

“A use value, or useful article, therefore, has value only because human labor in the abstract has been embodied or materialized in it. [21]“


ይኽ የማርክስ የጉልበት መጠን የሸቀጦችን ዋጋ ይወስናል የእሚለው የኢከነሚክስ መርህ እንደ እማይሰራ ለማሳየት ፤ በጣም ጥንታዊ እና ተራ የጉልበት መጠን የእሚወስድ የማምረት ኺደት የሆነውን ፤ የፍራፍሬ ለቀማ ማሳያ አድርገን መጠቀም እንችላለን። 


በተመሳሳይ የአካል ቁመና ላይ ያሉ ኹለት የፍራፍሬ ለቃሚዎች ወደ አንድ ደን ውስጥ ገብተው ፤ በግላቸው የተለያየ ምክንያት ፤ እኩል ስምንት ሰዓት ሰርተው የተለያየ መጠን እና ጥራት የአለው ፍራፍሬ ሊለቅሙ ይችላሉ። በእዚኽም መሠረት አንደኛው በስምንት ሰዓት 100 ኪሎ የእሚመዝን እና የተሻለ ጥራት የአለው ፍራፍሬ ሲለቅም ፤ ሌላኛው በተመሳሳይ ስምንት ሰዓት ውስጥ 90 ኪሎ የእሚመዝን እና አነስ ያለ ጥራት የአለው ፍራፍሬ ለቀመ እንበል። 


ማርክስ ትክክል ከሆነ ፤ የእነ እዚኽ ኹለት ሰዎች ፍራፍሬ ፤ 100 ኪሎው እና 90 ኪሎው ፤ የስምንት ሰዓት ጉልበት እኩል ስለ ፈሰሰባቸው ፤ በገበያ እኩል ዋጋ ሊኖራቸው ይገባል ማለት ነው። ይኽ ሊሆን እንደ እማይችል ግን ፤ አይደለም የኢከነሚክስ ሳይንስ ተማሪ ፤ የቤት ፍጆታ የእምትገዛ ፊደል የአልቆጠረች አንድ የቤት እመቤትም የእምታውቀው ነው።


ስለ እዚኽ ማርክስ የካፒታሊስት ስልተ ምርትን እተቻለሁ ብሎ ፤ የሸቀጦች ዋጋ ለማምረት በፈጁት ጉልበት ልክ ይወሰናል እና የኢከነሚ ትርፍ ምንጩ የጉልበት ብዝበዛ ነው የእሚለው አባባል ምንም መሠረት የሌለው መሆኑ ግልጽ ነው። 


እዚኽ ጋር ሊስተዋል የእሚገባው ጉዳይ ፤ በጉልበት ብዝበዛ የእሚመጣ የኢከነሚ ትርፍ የለም አይደለም። ልክ በስርቆት የእሚመጣ የኢከነሚ ትርፍ እንደ አለው ኹሉ ፤ በጉልበት ብዝበዛም የእሚመጣ የኢከነሚ ትርፍ አለ። በስርቆት የእሚመጣ የኢከነሚ ትርፍ አለ ማለት ግን ፤ የኢከነሚ ትርፍ ኹሉ የእሚመጣው በስርቆት ነው ማለት አይደለም። 


የኢከነሚ ትርፍ በብዙ ምክንያት ሊመጣ ይችላል ፦ አዲስ የአመራረት ስልት በማስተዋውቅ ፣ የሸማቾች ፍላጎት በመ፟ቀየሩ ፣ በተፈጥሮ በእሚከሰቱ ጉዳቶች በእሚያስከትሉዋቸው ጉዳቶች በተፈጠሩ የግብአት አቅርቦት እጥረት ፣ በስርቆት ፣ በብዝበዛ ፣ ሆን ብሎ እቃ በማስወደድ ፣ በስህተት ፣ ወዘተ ። 


ለምሳሌ ፦ ከላይ 100 ኪሎ ፍራፍሬ የለቀመው ሰው ፤ ፍራፍሬውን ወይንም ጥራጥሬውን ፤ በእሚወደድበት ሰዓት ጠብቆ በመሸጥ ፤ በተለመደው ሰዓት ቢሸጥ ከእሚያገኘው በላይ ትርፍ ሊያገኝ ይችላል። ይኽ ሰው ፤ የትርፍ መጠነኑ ለመጨመር የማንንም ሰው ጉልበት አልበዘበዘም።


እንደ እዚኹም አንድ ሰው በፍጥነት እና በጥራት ፍራፍሬ የእሚሰበሰብበት ስልት በማስተዋወቅ በአጭር ግዜ ብዙ ፍራፍሬ በፍጥነት መሰብሰብ በመቻል ከፍራፍሬው ሽያጭ የእሚያገኘውን ትርፍ ሊጨምር ይችላል ፤ ይኽ ሰው በእዚኽ ኺደት የማንንም ጉልበት አልበዘበዘም።


በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ፍራፍሬው የተለቀመበት ደን ቢቃጠል ፤ ተለቅሞ ገበያ የአልወጣው ፍራፍሬ በአንድ ግዜ ዋጋው ይንራል ። 


እንዲኽ እንዲኽ እያልን ፤ ምንም እንኳን ፤ የጉልበት ብዝበዛ የኢከነሚ ትርፍ ሊያመጣ እንደ እሚችል በአያከራክርም ፤ የማንም ጉልበት ሳይበዘበዝ የኢከነሚ ትርፍ የእሚፈጠርባቸው እጅግ በጣም ብዙ መንገዶች እንደ አሉ ማሳየት ይቻላል።  


ስለ እዚኽ ፤ ማርክስ የካፒታሊስት ኢከነሚውን ስልተምርት አብጠርጥሬ አውቃለሁ በእሚል ፤ የካፒታሊስቱ ስልተ ምርት ኃብታም እና ድኃ የእሚፈጥረው ፤ የሰውን ጉልበት በመበዝበዝ ብቻ እና ብቻ ነው የእሚለው ፤ ውኃ የእማይቋጥር የኢከነሚ ትንታኔ ላይ የተመሠረተ ነው ። 


ይልቁንም ዘመናዊ የኢከነሚክስ ሳይንስ እንደ እሚያስረዳን ፤ የሸቀጦች ዋጋ የእሚወሰነው ፤ ሸቀጦቹ በሠራተኛ ማሕበር ይመረቱ ወይንም በሶሻሊስት መንግሥት ቁጥጥር ስር በአለ ድርጅቶች ይመረቱ ወይንም የግል በአለኃብት በእሚፈቀድበት ስረዓት ውስጥ በአሉ የግል በአለ ኃብቶች ይመረቱ ፤ ዋጋቸው የእሚወሰነው ፤ ሸቀጦቹን በተመለከተ በገበያ ውስጥ በአለው የፍላጎት እና የአቅርቦት መሳሳብ ነው። 


ስለ እዚኽ ፤ ሦሥት ጥራዝ ባለ ብዙ መቶ ገጽ መጽሐፍ የአጻፋቸው የማርክስ እና የኤንግሊስ የካፒታሊስት ኢከነሚ ስረዓት ትችት የተመሠረተበት ፤ በካፒታሊስት ስረዓት ውስጥ የአለው የኢከነሚ ትርፍ ምንጭ የጉልበት ብዝበዛ ነው የእሚለው አስተሳሰብ ፤ በጣም ተራ እና እጅግ ጨለምተኝነት የተንጸባረቀበት ስህተት በመሆኑ ፤ ማርክሲዝም ሳይንሳዊነቱ የጽንሰ ኃሳብ ተፋልሶ የአለበት ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው። 


ማርክስ ግን በእዚኽ ስኹት የካፒታሊስት ኢከነሚክስ አረዳዱ ላይ ተመርኩዞ  ፤ የካፒታሊስት ስረዓት ለምርት ሥራ ከሰው ጉልበት ይልቅ በማሽን ላይ እየተደገፈ ሲኼድ ፤ የሠራተኛው አስፈላጊነት እየቀነሰ በእዚኽም የጉልበቱ ዋጋ እያሽቆለቆለ ይኼዳል ብሏል ። ይኽም ብቻ ሰአይኾን  ፤ ሠራተኛው በእዚኽ መልኩ ስለ እሚደኸይ እና በማሽን ጉልበት ገበያውን በምርት ያጥለቀለቀው ካፒታሊስት ገበያ ስለ እሚያጣ ፤ ካፒታሊዝም ያርጥ እና ማምረቻ መሳሪያዎች እና ምርት ተትረፍርፈው እያሉ ፤ በካፒታሊስት ማሽኖች ከሥራ ተነሳፎ ቀጣሪ አጥቶ እና ደህይቶ መግዣ ያጣው ሠራተኛው አምፆ ስለ እሚነሳ ነው የሠራተኛው አብዮት የእሚነሳው ይላል ፦


“በሰፊው ሕዝብ ላይ ራሳቸው በአደረሱበት ውድቀት ምክንያት ለሸቀጦቻቸው በቂ ፍላጎት በማጣት ፤ ምርት ለማቃጠል ፣ የተመረቱ ሸቀጦች ለማጥፋት ፣ የማምረት ኺደትን ማቆም እና ፋብሪካዎችን ማጥፋት ይጀምራሉ … ይኽም ማለት ካፒታሊዝም አብዮትን አርግዟል ፥ … ።”

“Finding no effective demand for their goods owing to the ruin of the mass of the population which they themselves have brought about, are compelled to burn products, destroy manufactured goods, suspend production, and destroy productive forces ... this means that the capitalism is pregnant with revolution, ... [14]“


ማሽኖች በከፍተኛ ደረጃ የሰውን ጉልበት በመተካት በግዜያዊነት ሰውን የእሚተኩ ቢሆንም ፤ የሰው ልጅ ግን በዘመኑ በሙሉ ፤ የማምረት እና የመኖር ኺደቱን እንዲያግዙለት ፤ ከእንስሳት ጉልበት አንስቶ የተለያዩ መሳሪያዎችን ሲጠቀም የነበረ በመሆኑ ፤ እንዴት ተቀጥረው እርሻኽን ሊያርሱልህ የእሚችሉ ሥራ የአጡ ሰዎች እያሉ በጥማድ በሬ ማረስ የእሚባል ስልት አምጥተኽ የሠራተኛ ጉልበት ቀንሰኽ ፤ በርካሽ ብዙ የማምረት ኺደት ውስጥ ትገባለህ? ማለት ቂልነት የሆነውን ያኽል ፤ በፋብሪካ የተቀጠሩ ሰዎች የእሚሰሩዋቸውን ሥራዎች በማሽን መተካት የካፒታሊዝም ችግር ነው ማለትም እንደ እዛው ነው ፤ ምክንያቱም እንደ እዚኽ ዓይነት መተካካት በሌለበት ኹኔታ ፤ የኢከነሚ የመዋቅር ሽግግር (Economic Structural Change) የእሚባል ነገር የሌለ በመሆኑ። 


በእዚኽ መልኩ ነው የሰው ልጅ ፤ ከግብርና ኢከነሚ ወደ ኢንደስትራላይዝድ ፣ ከኢንደስትራላይዝድ ኢከነሚ ወደ አገልግሎት ሰጪ (የእውቀት ፣ የመረጃ ፣ ቀላል ሥራዎች) የተሸጋገረው።    


በኹለተኝነት ፦ በገበያ መርህ የእሚመራ ካፒታሊዝም ፤ ፋብሪካዎቹን እስከ መዝጋት እና ምርቶቹን እስከ ማቃጠል ድረስ የእሚደርስ ገበያ የለሽ ምርት ማምረት ውስጥ ፤ ለዛውም በቋሚነት ፤ ሊገባ እንደ እማይችል የኢከነሚክስ ሳይንስ እውቀት ሰአይኾን  የነጋዴ እውቀት ራሱ በቂ በመኾኑ ፤ ማርክስ ስር የሰደደ መሠረታዊ የኾነ የፅንሰ ኃሳብ አረዳድ መፋለስ ችግር እንደ አለበት ይኽ ኹለተኛ ማሳያ ነው ።


ሦሥተኛው ፤ በማርክስ ዴያሌክቲክ የመደብ ግጭት ግንዛቤ ምንጩ የቁሱ ዓለም የእሚመራበት የግጭት ሕግ ነው ይላል ፦


“… እድገት ውስጥዊ ተቃርኖዎችን ወደ አደባባይ በማውጣት ፣ እነዚኽን ተቃርኖዎችን ድል ለመንሳት ፣ በእነዚኽ ተቃርኖዎች ላይ የተመሠረተ የተፃራሪ ኃይሎች ግጭት የእሚመጣ ከኾነ ፤ የሠራተኛው የመደብ ትግል እጅግ ተፈጥሮዋዊ እና ሊቀር የእማይችል ክስተት መኾኑ ግልፅ ነው ።”

“…, if development proceeds by way of the disclosure of internal contradictions, by way of collisions between opposite forces on the basis of these contradictions, then it is clear that the class struggle of the proletariat is a quite natural and inevitable phenomenon. [14]“


በዝባዥ እና ተበዝባዥ ወይንም በባለ ኃብት እና በድህነት የእሚማቅቅ የባለ ኃብቱ ሠራተኛ መደባዊ ተቃርኖ ውስጥ ናቸው ማለት አንድ ነገር ነው ፤ የእዚኽ ግንዛቤ ምንጭ ግን የቁሱ ዓለም የእሚመራበት የተቃርኖ ሕግ ነው ማለት ግን ፤ ግርድፍ ድምዳሜ በመሆኑ ብዙ ጥያቄ የእሚያስነሳ ነው ። 


በቁሱ ዓለም ውስጥ የእሚገኘው የትኛው የታቃርኖ ዓይነት ነው ወደ መደባዊ ተቃርኖ አስተውሎ የእሚለወጠው? ለምሳሌ ፦ አንድ በቪላ ውስጥ የእሚኖር ባለጸጋ እና በደካማ መኖሪያ ቤት ውስጥ በእሚኖር ድኃ መሐከል ተቃርኖ ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ የተወሰነ ተቀባይነት ሊኖረው ቢችልም ፤ ቁስ የሆኑት ቪላ እና ደካማ መኖሪያ መካከል ቁሳዊ ግጭት ለመኖሩ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ማስረጃ የለም ወይንም ኃብት እና እጦት ውስጥ የእሚኖሩ ዜጎች መሐከል ተቃርኖ ሊኖር ቢችልም ማንም ሰው በተትረፈረፈ ገንዘብ እና ጥቂት በሆነ ገንዘብ መካከል ቁሳዊ ግጭት አለ ብሎ ማሳየት አይችልም ። ብዙ ኃብት እና ጥቂት ኃብት መሐከል ምን ዓይነት ተቃርኖ ሊኖር ይችላል ፤ በቁስነታቸው ?


ከእዚያኽ በተጨማሪም ፤ ቁሶቹ ከሆኑ ማሕበራዊ መደባትን የእሚፈጥሩት ፤ በምን አግባብ ነው ፤ የትኛውን ሰው ባሪያ እና የትኛውን ሰው ባሪያ አሳዳሪ ፣ የትኛውን ሰው ጭሰኛ እና የትኛውን ሰው በአላባት ፣ የትኛውን ሰው ድኃ እና የትኛውን ሰው ኃብታም ለማድረግ የእሚመርጡት? በየትኛው ሳይንስ ነው ይኽንን ድምዳሜ በእርግጠነት ማስቀመጥ የእሚቻለው? ስለ እዚኽ ቁሳዊ ተቃርኖ ነው የመደባዊ ጠላትነት ግንዛቤያችን ምንጭ ነው የእሚለው ማርክሲስታዊ ድምድሜ ፤ ከሰማዩ በአሻገር የወርቅ ወንዝ አለ ከእሚል እና ሊፈተን ከእማይችል ድምዳሜ በምንም የእማይለይ ጭፍን ርግጠኝነት ነው ።


በአጠቃላይ ሲታይ ማርክሲዝም ፤ ከጥንታዊ የግሪክ ፈላስፎች መጽኃፍት ላይ የነበሩ ኃሳቦችን ገልብጦ ፤ በትንሽ ማስተካከያ እንደ ዘመናዊ እና አዲስ ኃሳብ የማስቀመጥ አባዜ እንጂ ፤ ማርክሲዝም ስለ ራሱ እንደ እሚለው በማርክስ የተገኘ አዲስ ኃሳብም አይመስልም ።


ለምሳሌ ፦ ማርክስ ፤ በከምኒስት ማንፌስቶ ላይ ፤ ሰዎች በሙግት ቁሳዊነት በእሚያገኙት ግንዛቤ ፤ እየተነዱ መደብ ለይተው እንደ እሚጋጩ እንዲኽ ብሏል ፦


“ከእዚኽ በፊት የነበሩ ማሕበረሰባት ታሪክ ኹሉ የመደብ ትግል ታሪክ ነው ። ነፃ እና ባሪያ ፣ በአላባት እና ጭሰኛ ፣ ጌታ እና ሎሌ ፣ አለቃ እና ምንዝር ፤ በአጭሩ ጨቋኝ እና ተጨቋኝ ፤ ማብቂያ በሌለው ተፃራሪነት ተፋጠው ፤ አንዳንዴ በግልፅ አንዳንዴ በስውር እየተጋጩ ፤ ግጭቱ አብዮታዊ የኾነ ማሕበራዊ አዲስ አወቃቀር በመፍጠር የተጠናቀቀ ወይንም ተቃራኒ መደቦቹ በፍፁም የተጠፋፉበት ነው ።”

“The history of all hitherto existing society is the history of class struggles. Freeman and slave, patrician and plebeian, lord and serf, guild-master and journeyman, in a word, oppressor and oppressed, stood in constant opposition to one another, carried on an uninterrupted, now hidden, now open fight, a fight that each time ended, either in a revolutionary reconstitution of society at large, or in the common ruin of the contending classes. [18]“


ይኽ ከላይ የተቀመጠው ፤ የማርክስ የመደብ ትግል አስተሳሰብ ወይንም ድምዳሜ ፤ ቀደም ብለን ከጠቀስነው የሔራክሊተስ ለውጥ ቋሚ ነው ብሎ ከአስቀመጠው የለውጥ ኃሳብ ጋር የአላቸው ልዩነት ፤ የአውድ እና የአገባብ ከአልኾነ በስተቀር የይዘት እንደ አልኾነ ኹለቱን ለማነጻጸር የሞከረ ሰው የእሚረዳው ይመስለኛል  ፦


“ ኹሉ ነገር ፤ ለዘላለም በፍሰት እና በለውጥ ኺደት ውስጥ ነው ፤ አለ ። በአንድ ቦታ እንኳን ረግቶ በተቀመጠ ነገር ውስጥ  የእማይታይ ውዝዋዜ እና እንቅስቃሴ አለ ። ዓለማዊው ታሪክ ኹሉ በእማያቋርጥ ዑደት ውስጥ ነው ፤ እያንዳንዱ በእሳት ጀምሮ በእሳት እያበቃ … ’በጠብ’ ይላል ሔራክልተስ ፤ ኹሉ ነገር ይጀምራል በእርሱም ይከስማል … ጦርነት የኹሉ አባት እና ንጉሥ ነው ፡ አንዳንዶችን አማልክት ፣ አንዳንዶችን ሰዎች ፣ አንዳንዶችን ጨዋ ፣ አንዳንዶችን ባሪያ አድርጓል’ ። ጠብ በሌለበት በእዚያኽ ዝገት አለ ፤ ‘የማይወዘወዝ ስብጥር ይብሰብሳል’። በእዚኽ የለውጥ ውዝዋዜ ፣ ትግል እና ምርጫ ፤ አንድ ነገር ቋሚ ነው ፤ እርሱም ይኽ ሕግ ነው ።’ይኽ ለኹሉም የጋራ የኾነ ሕግ ፤ ሰው ወይንም ዓማልክት የሰሩት ሰአይኾን  ፤ ኹል ግዜ የነበረ ፣ ያለ እና የእሚኖር ነው ።”

“All things forever flow and change, he said; even in the stillest matter there is unseen flux and movement. Cosmic history runs in repetitious cycles, each beginning and ending in fire ... “Through strife,” says Heraclitus, “all things arise and pass away ... War is the father and king of all: some he has made gods, and some men; some slaves, and some free.” Where there is no strife there is decay: “the mixture which is not shaken decomposes.” In this flux of change and struggle and selection, only one thing is constant, and that is law. “This order, the same for all things, no one of gods or men has made; but it always was, and is, and shall be. [13]“  


ማርክስ እነ ሔራክልተስን ለቁሳዊነት መሠረት ከማድረግ በአለፈ ፤ ኃሳባቸውን የመገልበጥ እና የራሱ የማስመሰለም ሥራ የሰራ ይመስላል። 


ዴያሌክቲኩን (ሙጉቱን) ከሔራክሊተስ እንደ ቀዳው ፤ የታሪክ ቁሳዊነቱንም የማሕበረሰብ የአወቃቀር ደረጃ ከፕሌቶ ሪፐብሊክ እንደ ገለበጠው ይመስላል ። የፕሌቶ ሪፐብሊክ የእሚለው መጽሐፍ ፤ መጽሐፍ ስምንት ላይ ፤ ፕሌቶ ፍጹም ወይንም የመጨረሻው ትክክለኛው የመንግሥት አወቃቀር ፤ የግል ንብረት የሌለበት እና ኹሉም ነገር ማሕበረሰብ በጋራ የእሚያዝበት ነው ከአለ በኋላ ፤ ከእዚኽ ውጭ ስለ አሉት የተለያዩ (የውሸት ወይንም ሐሰተኛ) የማሕበረሰብ አወቃቀር የእሚተነትንበትን አግባብ  ፤ በፕሌቶ መጽሐፍ ስምንት እና በካርል ማርክስ የታሪክ ቁሳዊነት ውስጥ የተቀመጠቱት የስልተምርት ግንኙነት ደረጃዎች ማለትም ፦ ጥንታዊ ጋርዮሽ ፣ የባሪያ አሳዳሪ ፣ ፊውዳሊስም ፣ ወዘተ ፤ ብሎ ያስቀመጣቸውን ደረጃዎች የአለውን ተመሳሳይነት ለተመለከተ ሰው የካርል ማርክስ የታሪክ ቁሳዊነት መላምት የፕሌቶ መጽሐፍ ስምንት ማሻሻያ እንደ እሚመስል ፤ ኹለቱን አነጻጽሮ ሊገነዘብ ይችላል ፦


“ይኽ እውነታኛ ቅርጽ ከሆነ (ኹሉ ነገር በጋራ የእሚሆንበት የመንግሥት አወቃቀር) ፥ ሌሎቹ ደግሞ ሐሰት ይሆናሉ ፤ በትክክል ከአስታወስኩም እነ እዚኽ ሐሰተኛዎቹ አራት ዓይነት ሲሆኑ ፤ የእነ እዚኽን የሐሰተኛዎቹን ስህተት እና ከእያንዳንዱ ስረዓት ጋር የእሚዛመደውን የዜጎች ስህተት መመርመሩ ተገቢ ነው ብለኻል…ያልዃቸው አራቱ የመንግሥት አወቃቀር ዓይነታት ፤ በዝርዝር ስማቸው የእሚከተሉት ናችው ፦ የመጀመሪያው ፤ በብዙዎች በአባዛኛው የእሚወደሰው የቀርጤሶቹ እና የስፓርታ መንግሥት ነው ፣ ከእዛም በመቀጠል ኦሊጋሪኪ (መሳፍንታዊ መንግሥት) ይመጣል ፥ ይኽም ዓይነቱ መንግሥት ብዙም ጥሩ ስም የለውም በውስጡም ክፋት እስከ አፍጢሙ የሞላው ነው ፣ በሶስተኝነት ይኽንን ኦሊጋሪኪ ኹል ግዜ ተከትሎ የእሚመጣው ዴሞክራሲ ነው ምንም እንኳን ከኦሊጋሪኪው በይዘት በጣም ቢለይም ፤ በስተመጨረሻም አራተኛው እና ስረዓት አልበኝነት የነገሠበት እና የመጨረሻው ታላቁ እና ታዋቂው አምባገነንነት ይመጣል።”


“if this was the true form, then the others were false; and of the false forms, you said, as I remember, that there were four principal ones, and that their defects, and the defects of the individuals corresponding to them, were worth examining. …the four governments of which I spoke, so far as they have distinct names, are, first, those of Crete and Sparta, which are generally applauded; what is termed oligarchy comes next; this is not equally approved, and is a form of government which teems with evils: thirdly, democracy, which naturally follows oligarchy, although very different: and lastly comes tyranny, great and famous, which differs from them all, and is the fourth and worst disorder of a State. [22]“


እናም በእዚኽ የሪፐብሊክ መጽሐፍ ስምንት ላይ ፤ እኔ አንባቢን ላለማሰልቸት ስል የተውኹቱን ፤ፕሌቶ እነ እዚኽን የተለያዩ መንግሥታት የእሚገልጽበት እና እንዴት ከአንዱ ወደ ሌላው እንደ እሚልወጡ ወይንም እንደ እሚሸጋገሩ ያብራራበትን መንገድ የተመለከተ ሰው ፤ ከማርክስ የታሪክ ቁሳዊነት ማብራሪያ ጋር ቀላል የእማይባል መመሳሰል ያገኛል። 


በእነዚኽ ሦሥት ምሳሌዎች የማርክስን ፅንሰ ኃሳባዊ መፋለስ ችግር አይተናል ። የማርክሲዝም ችግር ግን ፅንሰ ኃሳባዊ ብቻም ሰአይኾን ፤ ምንም እንኳን ኹሉም ማርክሲስቶች አብዮታቸው እና መንግሥታቸው ፤ የማርክሲዝም ሳይንሳዊ ትንበያ መስረት የተካኼዱ ናቸው ብለው ቢያስረግጡም ወይንም የሰው ልጆች ፖለቲካዊ ታሪክ የእሚዘወረው ማርክስ በደረሰበት የሙግት ቁሳዊነት መርህ ነው ቢሉም ፥ በታሪክ ላብራቶሪ ሲፈተሽ ግን ሳይንሱ እና የሶሻሊዝም አብዮት የተካኼደበት አግባብ ፣ ከአብዮቱ በኋላ የተመሠረተው መንግሥት እና መንግሥቱም በስልጣን ላይ ሆኖ የከወናቸው ተግባራት ከ” ሳይንሱ” ፍጹም ተቃራኒ ናቸው ።


ይኽም ማለት ማርክሲዝም አይደለም የቀደመውን እና መጪውን ታሪክ በብቃት ሊተነትን ይቅር እና በራሱ ፍልስፍና የተመሩ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳን ከትንታኔው ጋር ማዋደድ ያልቻለ በመሆኑ ፤ መላምቱ የጽንሰ ኃሳባዊ ተፋልሶ ብቻ ሰአይሆን የአለበት ፤ ጽንሰ ኃሳቡ መሬት ላይ ከአለው እውነታ ጋር እንደ እማይጣጣም ወይንም ዴታው ከጽንሰ ኃሳቡ ጋር እንደ እማይሰምር እያሳየን ፤ የማርክሲዝም ኢሳይንሳዊነት ፍንትው አድርጎ ያወጣልናል   ።


ይኽንንም ተፋልሶ ለማሳየት የማርክሲስም ሶሻሊስታዊ አብዮት የተካኼደበት ማሕበረ-ኢከነሚ እና ከአብዮቱም በኋላ የተቋቋሙ ከምኒስታዊ መንግሥታት ውስጥ የነበሩ የስልጣን አወቃቀሮች ፤ ከማርክሲዝም ፍልስፍና ፍጹም ተቃራኒ በሆነ አግባብ እንደ የተካኼዱ መሆናቸው በቂ ማስረጃ ነው ።


እንደ እሚታወቀው የማርክስ የታሪክ ቁሳዊነት መላምት እንደ እሚለው ፤ በማርክሲስቶች ካፒታሊዝም በመባል የእሚታወቀው የምርት ግንኙነት ፤ የዳበረ ንቃት የአለውን ሠራተኛ በመበዝበዝ የድኃ ድኃ ስለ አደረገው ፤ ሰፊው እና ንቁው የካፒታሊስት ስረዓት ሠራተኛ ከእዚኽ ብዝበዛ ለመውጣት ሶሻሊስታዊ አብዮት አድርጎ ፤ የማምረቻ መሳሪያዎች ኹሉ የሠራተኛው የጋራ ንብረት የሆኑበትን ሶሻሊስታዊ ስረዓት መገንባቱ ፤ የእማይቀር ተፈጥሮዋዊ ሕግ ነው ተብሎ ተደምድሟል ። 


በታሪክ ግን ፤ ‘ሶሻሊዝምን’ ያመጡ የከምኒዝም  አብዮቶች በተሳካ ኹኔታ ተካኺደው መንግሥታዊ ለውጥ ማምጣት የቻሉት ካፒታሊስት በኾኑ ሐገራት እንደ አልሆነ እና ይልቁንም ፤ ይኽ ነው የእሚባል የካፒታሊስት ስረዓት በአልገነቡ ሐገሮች የከምኒዝም  አብዮት እንደ ተካኼደ እና እንደ ተሳካ ፤ ራሺያ ፣ ቻይና ፣ ኢትዮጵያ ዓይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው ። ይኽም የማርክሲዝም መርህ ስለ አልሰራ ነው ፤ ከማርክስ በኋላ የመጡ ማርክሲስቶች ኃሳዊ አስተውሎት  (False Consciousness) የእሚለውን አባባል የአመጡት።


ይኽም ማለት ፤ የከምኒዝም  አብዮት ታክቲክ የእሚሰራው ፤ ደካማ ፖለቲካዊ ስረዓት በአለባቸው ሐገራት ከኾነ እና የማርክስ መላምት እንደ እሚለው ተፈጥሮዋዊ ግዴታ ከአልኾነ ፤ መላምቱ ፋይዳቢስ ነው ማለት ነው ። 

በእዚኽ ረገድ ማርክሲስቶች የቀራቸው መከራከሪያ ፤ አንድ ቀን በካፒታሊሲቱ ስረዓት ውስጥ ሶሻሊስታዊ አብዮት መካኼዱ አይቀርም ወይንም እስከ አኹን አልተካኼደም ማለት ወደ ፊት አይካኼድም ማለት አይደለም የእሚል ፤ ላም አለኝ በሰማይ የሆነ ሙግት ነው።  


ምክንያቱም ፦ በታሪክ እስከ አኹን ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም የተሸጋገረ ሕዝብ አለመኖሩ ፣ የሶሻሊስት አብዮት የተሳካባቸው ሐገራት በአጠቃላይ የአልዳበረ የካፒታሊስት ማሕበረ ኢከነሚ የነበረባቸው ሐገራት መሆናቸው እና በእነ እዚኽ የአልዳበረ ማሕበረ ኢከነሚ በአለባቸው ሐገራትም የሶሻሊስት አብዮት የተሳካው ጠንካራ እና ፓርላመንተሪያዊ መንግሥት በአልገነቡ ሐገራት መሆኑ ፤ ማርክሲዝም የአስቀመጠው የማሕበረ ኢከነሚ ዝግመት እና የሰዎች ፖለቲካዊ ግንዛቤ በብቸኝነት ከእሚኖሩበት ማሕበረ ኢከነሚ ይመነጫል ከእሚለው ጋር የእማይጣጣም በመሆኑ ፤ የማርክስ መላምት እና ታሪካዊ ክስተቶች እንደ እማይስማሙ ያሳያል። 


የፊውዳሉ ስረዓት ወደ ካፒታሊስቱ ስረዓት በተለወጠባቸው ሐገራትም ፤ ፊውዳሉ ራሱ እየተራቀቀ ከግብርናው ይልቅ በንግዱ እና በኢንደስትሪው ላይ ቢሰመራ የእሚሻለው እየሆነ በገበያ አስገዳጅነት አንዳንዴም በፈቃዱ ተሸጋግሮ እንጂ በባላባቱ እና በጭሰኛው መካከል የመደብ ግጭት ተካኺዶ አይደለም ፤ ማሕበረሰቡ ከፊውዳል ወደ ካፒታሊስት ስረዓት የተሸጋገረው።


ሌላው እና ኹለተኛው ፤ የማርክሲዝም ትንታኔ እና ታሪካዊ ክስተቶች አለመጣጣማቸውን ከእሚያሳየን ክስተቶቹ አንዱ ፤ የከምኒዝም አብዮት በተሳካበት በራሺያ እና መሰል ሐገራት ፤ በማርክሲዙሙ ርዕዮት መሠረት የከምኒዝም አብዮቱ የተካኼደው በሰፊው ጭቁን ሕዝብ እና ወደ ስልጣን ያመጣው ሰፊውን የሠራተኛውን መደብ ሰአይኾን ፤ አብዮቱን ያካኼዱትም ሆነ ወደ ስልጣን የመጡት ራሳቸውን የሠራተኛው መደብ ወኪሎች ነን ያሉትን እና በማርክሲስታዊ የመደብ ክፍፍል ከሠራተኛው መደብ የእማይመደቡ ጥቂቶች መሆናቸው ነው ።


ማርክሲስቶች ፤ አብዮታችን የተፈጥሮ ሕግ እና የሰፊው ሕዝብ እንቅስቃሴ ነው ይበሉ እንጂ ፤ ብዙ የተባለለት የራሺያው ከምኒስት ፓርቲ ስልጣን በመያዣው መባቻ ወርኃ ጥቅምት ላይ ፤ በመቶ ሚልዮን የእሚቆጠር ሕዝብ በአለበት ሐገር 2 ሺ አባላት ብቻ የነበሩት ፓርቲ እንደ ነበር ፤ የከምኒዝም  ጥቁሩ መጽሐፍ እንደ እዚኽ ይላል  ፦


“በጥቅምት እ.አ.አ. 1917 ዓ.ም. መጀመሪያ አከባቢ የቦልሸቪክ አባላት ቁጥር ከ2 ሺ አይዘልም ነበር ፤ ነገር ግን በወቅቱ የነበረው የአንጃዎች ክፍፍል የፈጠረው ተቋውማዊ ክፍተት ፤ ትንሽ የተደራጀ ኃይል ክፍተቱን ተጠቅሞ ስልጣን እንዲይዝ አስችሎታል።” 

 «Membership in the Bolshevik movement seems to have numbered no more than two thousand at the beginning of October 1917….institutional vacuum of the autumn, the environment was perfect for a small, well-organized group to exercise a disproportionate amount of power. [23]“


የከምኒስት አብዮተኞች ግን ፤ ይኽ የቁጥር አናሳነታቸው ከማርክሲዝም ፍልስፍና ጋር ፍጹም ተቃራኒ እንደ ሆነ ሲተቹ ፤ የአመጡት መልስ ፤ በቁጥር አናሳ ብንሆንም የሰፊውን ሕዝብ ጥቅም ስለ እምንወክል ብዙኃን ነን ስለ እዚኽም እኛ ቦልሼቪክ ነን የእሚል ነው ።  


እንደ እሚታወቀው ፤ ቦልሼቪክ ማለት ብዝኃኑ ማለት ነው በራሺያ ቋንቋ ። ይኽም ብዝኃኑ የእሚለው ከማርክሲዝም ፍልስፍና የእሚመነጭ ሲኾን ፤ ኃሳቡም ሠራተኛው ፤ ሰፊው የሕብረተሰብ ክፍል ኾኖ ሳለ በጥቂቶቹ ካፒታሊስቶች እየተጨቆነ ስለኾነ ፤ ብዝኃኑ (ቦልሼቪኩ) በአብዮት ጥቂቱን ያስወጉድታል የእሚለውን ማርክሲስታዊ የአብዮት ትንታኔ የተመረኮዘ ነው ። 


የቦልሼቪኩ ፊታውራሪ ፥ ሌኒን ግን በአንድ በኩል ራሱ የእሚመራውን ቡድን ቦልሽቬኩ ብሎ እየጠራ ፤ በተግባር ደግሞ ለአባላቱ የቁጥር ብዙህነት ለማግኘት ብለን አብዮቱን ማዘግየት የለብንም ሲል ነበር ፦


“ቦልሼቪኩ ተገቢውን ብዛት እስኪያገኝ መጠበቅ ምንም ትርጉም የለውም አብዮት እንደ እዚኽ ዓይነት የተመቻቸ ኹኔታ አይጠብቅም።”

 “There is no point in waiting for the formal majority for the bolshevick, Revolutions don’t wait for such thing. [23]“ 


ይኽን የእሚለው ፤ የሠራተኛው አምባገነንነት እና ብዙኃኑ ጥቂቱን ይጨቁኑታል ብሎ ፤ ስለ ብዙኃኑ መንግሥት እና አብዮት (State and Revolution) የእሚል መጽሐፍ የጻፈው አቶ ሌኒን ነው ። 


በራሺያም የከምኒዝም አብዮት የተካኼደው ፤ በባላኃብቱ ወይንም በበአላባቱ ጉልበቴ እና ኃብቴ ተበዘበዞ ፤ ስለ እዚኽ ፦ ይኽንን በዝባዥ መደብ ወይንም ቡድን በኃይል አስወግዳለሁ ያለ የማሕበረሰብ ክፍል ስለ ነበረ አልነበረም ። ስለ እዚኽም ጉዳይ ሚለቨን ዲለስ እንደ እዚኽ ብሎ ይጠይቃል ፦


“ ለአዲስ ማሕበራዊ መዋቅር የሚያስፈልገው ቅድመ ኹኔታ ከሌለ ፤ አብዮቱን ማን ፈለገው ?”

“If the conditions for a new society were not sufficiently present, then who needed the revolution? [11]“


ስለ እዚኽ ፦ የከምኒስቶቹ አብዮት በተሳካባቸው ሐገሮች ፤ አብዮቱ በጥቂቶች ለጥቂቶች የተደረገ አብዮት ነበር ቢባል ብዙም ስህተት አይኾንም ። ሚሎቨን ዲላስ ፤ የከምኒስት ፓርቲ መሪዎች እንደ ማንኛውም ጨቋኝ ገዢ መደብ ስለ መሆናቸው እንደ እዚኽ ይላል ፦


“ከውሚውንስት በኾኑ ሐገራት በሙሉ ፤ የእሚከተለው ድምዳሜ የግድ ይኾናል ፦ በከምኒስት አውራዎች የእሚጀመር ለውጥ በሙሉ በአዲሱ መደብ  ፍላጎት እና ጥቅም የእሚመራ መኾኑ ነው ፤ ይኽ አዲሱ መደብ ደግሞ ፤ እንደ ማንኛውም መደብ ፤ ህልውናውን ለማስቀጠል ፣ ራሱን ለመከላከል ፣ ጥቅሙን ለማስጠበቅ እና አቅሙን ለመጨመር ይሰራል ። ይኽ ግን ፤ የከምኒስት ፓርቲው አመራር የራሱን ጥቅም በእሚያሳድድበት ወቅት የእሚጠቀም ሌላ የማሕበረሰብ ክፍል የለም ማለት ግን አይደለም ።”

“in Communist countries calls for the following conclusion: All changes initiated by the Communist chiefs are dictated first of all by the interests and aspirations of the new class, which, like every social group, lives and reacts, defends itself and advances, with the aim of increasing its power. This does not man, however, that such changes may not Ье important for the rest of the people as well [11]“


ይኽም ፤ በማርክሲዝም ስም የተካኼዱት አብዮቶች ፤ ከማርክሲዝም መላምት በተቃራኒ ፤ በሰፊው ሕዝብ እና ለሰፊው ሕዝብ ሰአይሆን ፤ ጥቂት አብዮተኞች በሰፊው ሕዝብ ስም የአደረጉት አብዮት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ ከአብዮቱም በኋላ የፖለቲካ ስልጣኑን ይዘው ፤ አብዮቱን የእሚያስቀጥሉት እና የአብዮቱ ቀዳሚ ተጠቃሚ የእሚሆኑት ፤ በስማቸው አብዮት የተካኼደባቸው ሕዝብ ሳይሆኑ ፤ በስማቸው አብዮት የአካኼዱት ጥቂቶቹ አብዮተኞች ናቸው። 


እንደ ማንኛውም ፤ በሕዝባዊ ውክልና ሰአይሆን በአመጽ ኃይል የፖለቲካ ስልጣን የያዘ ኃይል ፤ የማርክሲዝም አብዮተኞቹ ራሳቸውን ወደ ገዢ ወይንም ጨቋኝ መደብ ቀይረው ፤ ሕዝባዊ አብዮትን በመከላከል ስም የራሳቸውን ስልጣን መከላከል እና የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የእሚሰሩበት አካኼድ ፤ ሦሥተኛው ፤ የማርክሲዝም መላምት ከታሪካዊ እውነታዎች ጋር የእማይጣጣምበት ክስተት ነው። 


ሚሎቨን ዲለስ ፤ የከምኒስት ፓርቲው በተግባር ሲፈተሽ ፤ ከማርክሲዝም መርህ ፍጹም ተቃራኒ እንደ እሚንቀሳቀስ እንደ እዚኽ ይላል ፦


“የራሺያ አብዮት ዓለምን ‘በሳይንሳዊ መንፅር ብቻ በእሚመለከት’ እና ዓላማውም መደብ አልባ ማሕበረሰብን መፍጠር ነው በእሚል ትርክት ነው የተካኼደው። እውነታው ግን ፤ ከምኒስቶች ከእነርሱ በፊት ከነበረው ገዢ መደብ በተለየ ኹኔታ በተግባር አልተገኙም ። አዲስ እና እንከን የለሽ አዲስ ማሕበረሰብ እየገነባን ነው ብለው ፤ ለራሳቸው በእሚመቻቸው መልክ ብቻ ሲገነቡት ነበር።”

“The Russian revolution was carried out in the name of “a purely scientific view of the world” for the purpose of creating a classless society. In reality, the Communists were unable to act differently from any ruling class the PRECEDED them. Believing that they were building a new and ideal society, THEY BUILT IT FOR THEMSELVES in the only way they could [11].”


ይኽም ብቻ ሰአይኾን ፤ የጥቂቶችን አምባገነንነት አስወግደን ፤ የሠራተኛውን ወይንም የብዙኃኑን አምባገነንነት ማስፈን ነው ግባችን የእሚሉት ማርክሲስቶች ፤ አብዮታቸው በተሳካበት ሐገራት ኹሉ የጥቂቶች ብቻ ሰአይኾን የአንድ ሰው ፍፁማዊ አምባገነንነት የእሚያነግሱ ናቸው ፦


“የስረዓቱ አምታችነት የእሚታየው ፤ ይኽ ስረዓት የማሕበረሰብ እድገት ሕግ አካል ነው ብሎ ሲል ቆይቶ ፤ የስረዓቱ ብቸኛ አዕማድ የነበረው አንድ ሰው (ስታሊን) ሲሞት ፤ ለህልውናው አስፈላጊ የኾነ ነገር የጠፋበት ያኽል ተገራገጨ።”

“The paradox of a system that was supposedly part of the laws of social development, but in which actually everything depended on one man, so much so that when he died, it seemed that the system had lost something essential to its continued existence. [23]“


ይኽን መሰሎቹ ፤ በጥቂት ባለምዋሎች እና ሲበረታም በአንድ ሰው ትከሻ ላይ የመንጠልጠል ጉዳይ ፤ አፈንጋጭ ታሪካዊ ክስተት ሰአይሆን ፤ ከምኒዝም በተተገበረባቸው ሐገራት በሙሉ የእሚስተዋል በመሆኑ ፤ ስረዓታዊ ነው ፦


“… ስታሊን ሲሞት ፤ ራሱን እንደ ዓምላክ አስመስሎ አድርጎ ቀይሮ ነበር ።  እነ እዚኽ የስብዕና ለውጦች ግን ፤ በማሕበረሰቡ ውስጥ በስረዓቱ የተካኼዱ ለውጦች ነፀብራቅ የኾኑ እና የማንኛውም የከምኒዝም  ስረዓት ነፍስ (መንፈስ) ውጤቶች ናቸው ።” 

“…When Stalin died, he had already transformed himself into а god. These changes in personalities are only the reflection of changes which had already taken place and were the very soul of the Communist movement. [11] “


በታሪክም የከምኒስት ፓርቲ የነገሠባቸውን ሐገራት ስናይ የአንድ ሰው ‘ዓምላካዊነት’ የእሚስተዋልባቸው ናቸው ፦ ስታሊን በራሺያ ፣ ማዖ በቻይና ፣ ኾች ሚኒ በቬትናም ፣ ፖል ፖት በካምቦዲያ ፣ የካስትሮ ቤተሰቦች በኪውባ ፣ የኪም ቤተሰቦች በሰሜን ኮርያ ፣ ወዘተ ።


ስለ እዚኽ ፦ የከምኒስት አብዮት በዳበረ የካፒታሊስት ስረዓት በአለባቸው ሐገራት ሳይሳካ ፤ ኋላ ቀር መንግሥታዊ እና ኢከነሚያዊ መዋቅር በአለባቸው ሐገራት መሳካቱ ፣ ተመሳሳይ የማሕበረ ኢከነሚ ደረጃ ላይ በአሉ ሐገራት ውስጥ የከምኒዝም አብዮት በወጥነት አለመሳካቱ ፣ አብዮቱ በተሳካባቸውም ሐገራት ሰፊው እና ተጨቆነ የተባለው መደብ ሰአይሆን ጥቂቶች እና አንድ ሰው እንደ ‘ዓምላክ’ የሚገንበት መንግሥት መሆናቸው ፣ እነ እዚኽ ጥቂቶች አንድ ግዜ ወደ ስልጣን ከመጡም በኋላ እንደ በዝባዥ ገዢ መደብ ራሳቸውን በዋናነት የእሚጠቅሙ መሆናቸው ከምኒዝም በተግባርም ከሳይንሱ ጋር የእማይታረቅ ለመሆኑ ማሳያ ነው ። 

 

ሠንጠረዥ  3 ፡ የማርክሲዝም ኢሳይንሳዊነት ማሳያ መዘርዝር።    


ይኽን እና መሰል ብዙ ሳይንሳዊም ኾነ ታሪካዊ እውነታ የሌላቸው ግድፈት የሞላበት በመኾኑ ፤ ማንም ማርክሲዝምን ፦ እንደ ትርጉም የአለው ፖለቲካዊ ሳይንስ ቀመር ወይንም መመሪያ ሰአይኾን  ፤ በአንድ የታሪክ አጋጣሚ የነበረ በስረዓት አልበኞች የተዘወተረ የማሕበራዊ አምፅ መመሪያ ነው መታየት የአለበት  ። 

ማርክሲዝም ገዳይ መኾን የእሚችል ፖለቲካዊ ክትባት ነው ። ሕዝብ ጠንካራ እና ፋይዳ የአለው መንግሥት ከገነባ ማርክሲዝምን ተቋቁመው ይቀጥላል ፤ ጥገኛ ፖለቲካዊ ባሕል ያደከመው ከኾነ ፤ የጥገኝነት እና የአምባገነንነት ጥግ የኾነው ማርክሲዝም ወደ አለመኾን ያመጣዋል ።


ማርክሲዝም (የሙግት ቁሳዊነት እና የታሪክ ቁሳዊነት) ፤ የኢከነሚክስ ፣ የታሪክ ፣ የፍልስፍና እና የፖለቲካ ሳይንስ እውቀት የሌለውን የማሕበረሰብ ክፍል ፤ በእነዚኽ ሳይንሶች ስም ፤ ተበድለኃል ፣ ተጨቁነኃል ፣ ተበዝብዘኃል ብሎ ኾድ በማስባስ ፤ ለአመፅ እና ለአብዮት ማነሳሳት እንጂ ፤ ሳይንሳዊ እና በዛም ሊተገበር የእማይችል እንቶ ፈንቶ ነው ።


3.    ጸረ ሳይንስ ነው

ካርል ማርክስ ዳስ ካፒታል በእሚለው መጽሐፉ መግቢያ ላይ ፤ በሳይንስ ላይ ሰለ አለው እምነት እንደ እዚኽ ሲል ይነበባል ፦


“በሳይንሳዊ ትችት ላይ የተመሠረተ ማንኛውንም አስተያየት በደስታ የእምቀበለው ነው። ከእዚኽም በፊት ጆሮ ስለ እማልሰጣቸው ፤ የሕዝብ አስተያየት ስለ እሚባሉት ዝበቶች ግን ፤ የቀደሙ የታላቁ የፍሎረንሱ ሰው አባባል የግሌ ነው ‘አንተ ጎዳናህን ተከተል ሰዎችም ያውሩ  - ካዳንቴ የተወሰደ’።” 

“Every opinion based on scientific criticism I welcome. As to prejudices so called public opinion, to which I have never made concessions, now as aforetime the maxim of the great Florentine is mine. ’Follow your path and let people talk – Paraphrased from Dante. [21]“


 ካርል ማርክስ በሳይንስ ላይ ጽኑ እምነት እንደ አለው በእዚኽ መልኩ በዳስ ካፒታል ላይ ቢልም ቅሉ እንደ እዚኽ ከአሉት ጥራዝ ነጠቅ የማርክስ አባባሎች በስተቀር ፤ የማርክስ የማሕበረ ኢከነሚ ፍልስፍና ወይንም ማርክሲዝም እንደ ርዕዮት ጸረ ሳይንስ መሆኑ በርዕዮቱ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ ነው። 


ሳይንስ የእሚለው የእንግሊዘኛው ቃል ሲየንሻ (scientia) ከእሚለው እና እውቀት የእሚል ትርጉም ከአለው የላቲን ቃል የመጣ በመሆኑ ፤ ሳይንስ ማለት እውቀት ወይንም የተረጋገጠውን ትክክለኛ መረጃ የማፈላለግ ኺደት እንደሆነ የቃሉን ምንጭ ካላወቅን ወዲያው አይታየንም ፤ ሆኖም ፦ ሳይንስ ማለት የተፈተነውን እውቀት የማፈላለጊያ መንገድ ነው። 


በእርግጥ አንዳንድ እውቀቶች የተንዛዛ ማፈላለግ ሳይደረግባቸው በግልጽ ያሉ ናቸው። ለምሳሌ ፦ ፀሐይ በምሥራቅ ትወጣለች የእሚለው እውቀት ፤ ሳይንሳዊ እውቀት ቢሆንም ፤ ፀሐይ በምሥራቅ እንደ እምትወጣ ለማወቅ ፤ ሳይንሳዊ የእውቀት ማፈላለጊያ መንገድ መጠቀም ቢቻልም ፤ ከኹነቱ ገኃድነት የተነሳ የፀሐይ በምሥራቅ መውጣት ይኽ ነው የእሚባል ከበድ ያለ ምርምር የእሚጠይቅ አይደለም። 


እንደ ፀሐይ በምሥራቅ ትወጣለች ዓይነት ሳይንሳዊ እውቀቶች ቢኖሩም ኹሉም እውቀቶች በገኃድ በአደባባይ እና ለተርታው ሰው ግልጽ በሆነ መንገድ የእሚገኙ ግን አይደሉም።

 

ለእዚኽም ነው ሳይንስ ማለት እውቀት ከእሚለው ትርጓሜ በአሻገር ወደ አንድ አስተማማኝ ወይንም የተረጋገጠ እውቀት የእምንደርስበት መንገድ የእሚል ትርጉም የአለው የሆነው።

 

ሳይንስም ወደ አንድ አስተማማኝ ወይንም የተረጋገጠ እውቀት የእሚደርሰው በኹለት መንገድ ነው ፦

    ክትትልን ወደ ድምዳሜ በመለወጥ  (Deduction)

    ድምዳሜን በክትትል በማረጋገጥ (Induction)


የሰው ልጅ የመሬት የስበት ጉልበት 9.8 ሜትር በሰከንድ ነው የእሚለው እውቅት ወይንም ድምዳሜ ላይ ከመድረሱ በፊት ፤ አንድ ቁስ ከአንድ ከፍታ ቦታ ላይ ወደ መሬት ሲወድቅ በምን ያኽል ጥድፈት ይወድቃል? ብሎ ጠይቆ ይኽንን ጥያቄውን ለመመለስ ፡ የተለያዩ ክብደት የአላቸውን ነገሮች ከትልቅ ከፍታ ላይ ጥሎ ፤ የወደቁበትን ከፍታ ርቀት እና ከእዚያ ከፍታ ላይ መሬት ለመድረስ የወሰደባቸውን ሰዓት መዝግቦ ይኽንንም ሙከራ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ከአደረገ በኋላ ነው ፤ የመሬት የስበት ጉልበት 9.8 ሜትር በሰከንድ ነው የእሚለው። ይኽ ዓይነቱ እውቀት ፤ ክትትልን ወደ ድምዳሜ ወይንም የተረጋገጠ እውቀት መቀየር (Deduction) ነው።


ከእዚኽ በተቃራኒ ደግሞ ፤ ምንም እንኳን ክብደት የአላቸው ነገራት በእዚኽ የመሬት ስበት ጉልበት ምክንያት በአየር ላይ ተንሳፈው መቅረት የእማይችሉ ቢሆንም ፤ በአየር ላይ አእዋፋት ሲበሩ ተመልክቶ ፤ ይኽንን የመሬት ስበት ጉልበት በአንድ ዓይነት ስልት ማሸነፍ እና በአየር ላይ መጓዝ ይቻላል ብሎ አስቦ (ደምድሞ) ፤ እንዴት ይኽንን የመሬት የስበት ጉልበት አሸንፎ በአየር ላይ አንድ ክብደት የአለውን ነገር ማንሳፈፍ እንደ እሚቻል ለማገኘት ፤ የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጎ ፤ ከቁሱ በላይ የአለውን የአየር እመቃ መጠን ከቁሱ በታች ከእሚገኘው የአየር እመቃ የእሚያንስ በማድረግ ፤ አንድ ክብደት የአለውን ነገር በአየር ላይ ማንሳፈፍ ይቻላል ወደ እሚለው እውቀት ወይንም ድምዳሜ ላይ መድረስ ደግሞ ፤ ድምዳሜን በክትትል ማጠናከር በመሆኑ ሌላኛው (Induction) ዓይነት መንገድ የተገኘ ሳይንሳዊ እውቀት ነው።


በእዚኽ መልኩ ነው ሳይንስ ፤ ድምዳሜን በክትትል ወይንም ክትትልን በድምዳሜ በማጠናከር ወደ እርግጠኛ እውቀት የእሚደረሰው።   


በእዚኽ ዘመን ለእምንገኝ ሰዎች ፤ ይኽን መሰሉ እውቀት የመጨበጫ መንገድ በጣም ከመለመዱ እና ከእዚኽ ውጭም እወቅት ሊያዝበት የእሚችልበት መንገድ አለመኖሩ በጣም ግልጽ ስለ ሆነልን ፤ የሳይንሳዊነትን ፋይዳ ማድነቅ የእምንችለው ፤ ዘመነ ሕዳሴ የእሚባለው እ.አ.አ. 1500 ዓ.ም. በኋላ የመጣው ሳይንሳዊ አብዮት ከመፈንዳቱ በፊት የነበረው አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ስለ እውቀት የአለውን ግንዛቤ ስንመለከት ነው። 


ከሳይንሳዊ አብዮት በፊት የነበረው ዓለም አከባቢን እና ተፈጥሮን በእዚኽ መልኩ ተመራምሮ ድምዳሜን ማስቀመጥ እንደ ዓመጽ ወይንም ዓምላክን እንደ መዳፈር የእሚመለከት እና በግልጽ ከእሚታዩት እና ዓምላክ ገለጠለን የእሚሉ ሰዎች ከእሚያስተላልፉት ውጭ ያለ እውቀትን ወይንም ድምዳሜ ከእላይ በአስቀመጥነው የጠያቂነት ፣ የአገናዛቢነት እና የአመሳካሪነት አካኼድ ማስረገጥ እንደ ኑፋቄ (Heresy) የእሚመለከት ነበር።     

ስለ እዚኽ ፦ ከሳይንሳዊ አብዮት በፊት ፤ አንድ ሰው አከባቢውን ተመልክቶ ፤ በግልጽ ከእሚታየው ወይንም አምላክ ገለጠልን ብለው የጥንት ሰዎች ከአስተላለፉት እውቀት የተለየ ወይንም ከእርሱ የእሚቃረን አዲስ እውቀት ይዞ ከመጣ ፤ ያ ሰው እንደ አመጸኛ እና እንደ አሳች ታይቶ ፤ እስከ ሞት የእሚያደርስ ብዙ እንግልት ይደርስበት ነበር። 


ይኽ ዓይነቱ ወግ አጥባቂነት (Conservatism) ቅድመ ሳይንሳዊ አብዮት የነብረው ማሕበረሰብ በወግ ጠርቆ ይዞ ፤ ማሕበረሰብ በቆመበት እንዲቀር ብቻ ሳይሆን ፤ ከግዜ ወደ ግዜ የማሕበረሰብን ሕይወት በተለያየ ችግር ቀስፎ ይዞ ያስቀረ ስለ ነበር ፤ የሳይንሱ አብዮት ፤ በክትትል ይረጋገጥ እንጂ የመሰለኝን ድምዳሜ ማስቀመጥ መቻል አለብኝ እና ማንኛውንም ድምዳሜ በክትትል ከአላረጋገጥኩ ስለ እሚመስል ወይንም ደግሞ አንድ ጥንታዊ አባት አምላክ ገልጦልኛል ስለ አለው ብቻ አልቀበለም በእሚል ፤  በክትትል ያለ አረጋገጡኩትን ነገር አልቀበለም የእሚል እንቅስቃሴ ሆኖ መጣ።


ይኽን መሰል መልክ የነበረው የሳይንስ አብዮት ፤ ከላይ እንደ ማሳያ የጠቅስናቸው የመሬት የስበት ጉልበት መጠን እና የመሬት የስበት ጉልበትን እንዴት ማሸነፍ ይቻላል የእሚሉ ቁሳዊ ነገሮች ላይ ብቻም የተወሰነ ሳይሆን ቁሳዊ ያልሆኑ መንፈሳዊ ነገሮችንም የእሚከታተል እና ድምዳሜ ላይ የእሚደርስ ነበር።


ለምሳሌ ፦ እግዚአብሔር አለ ? ሰው ነፍስ አለው ? እወቀት ምንድ ነው ? ህሊና ወይንም አስተውሎት ምንድ ነው ? ሰው እውቀት የእሚያዳብረው እንዴት ነው ? ፍትኽ ምንድ ነው ? ወዘተ ፤ የእሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቆ እና ከእላይ በአስቀመጥናቸው በኹለቱ ፤ ከክትትል ወደ ድምዳሜ ወይንም ድምዳሜን በክትትል በማስረገጥ ፤ የተለያዩ እውቀቶችን የእሚያመርት ነበር። 


ለምሳሌ ፦ ሬነ ዴስካርት የተባለው የፈረንሳይ ፈላስፋ ፤ እውቀትን መፈለግ ፋሽን በነበረበት በእዚያኽ ዘመን ፤ የስሜት ሕዋሳቶቼ ስለ እሚያታልሉኝ በስሜት ሕዋሳቶቼ የእምሰበስባቸውን እውቀቶች እንዴት እንደ እርግጠኛ እውቅቶች ልወሳዳቸው እችላለኹ ? ለእሚለው ጥያቄ ፦ ስለ እማስብ ስለ እዚኽ እኔ ነኝ (Cogito Ergo sum or I think, therefore, I am) በመባል የእሚታወቀውን አባባሉ ላይ ተመስርቶ ስለ

እምናውቀው እውቀት ርግጠኛ መሆን እንደ እምንችል ሞግቷል፦


“እናም ፤ አንዳንድ ግዜ የስሜት ህዋሶቻችን ስለ እሚያታልሉን ፤ ምንም ነገር መስሎ እንደ እሚታየን አይደለም ብዬ ለማሰብ ፈለግኹ ፤ እንደ ገናም ሰዎች ትንታኔ በእሚሰሩበት ግዜ ስለ እሚሳሳቱ እና ቀላል በኾኑ የጂዖሜትሪ ፅንሰ ኃሳቦች ላይ እንኳን የኃሳብ መፋለስ ስለ እሚፈጥሩ ፤ እኔም እንደ እነርሱው ተመሳሳይ ስህተት ስለ ተሸከምሁ ፤ ከእዚኽ በፊት እውነቱን የእሚያሳዩ ናቸው የአልኹዋቸውን ምክንያቶች ኹሉ እንደ እማይረቡ ቆጠርኩዋቸሁ ። እንደ ገናም በውን ሳለን የእሚኖሩን ኃሳቦች እና ውጥኖች በህልማችንም ስለ እሚመጡ እና በህልማችን የእምናየው ምንም ነገር እውነት በአለ መኾኑ ፤ ወደ አዕምሮዬ የገባ ማንኛውም ኃሳብ ከህልሜ በተለየ እውነት አይደለም ብዬ ለማሰብ ቆረጥኹ ። ነገር ግን ፤ ኹሉም ነገር ውሸት ነው ብዬ ለማሰብ ስፈልግ ፤ ወድያውኑ ኹሉ ነገር ውሸት ነው ብዬ የእማስበው ‘እኔ’ መኖር ያለበኝ መኾኑ ሊካድ የእማይችል ኃቅ ኾኖ ፤ ‘ስለ እማስብ ስለ እዚኽ አለሁ’ የእሚለው አባባል ህልቆቢስ የኾኑት የጠርጣሮች ቢኾንታዎች በሙሉ ሊነቀንቁት የእማይችሉ ኾኖ አገኘኹት …”

“Thus, because our senses sometimes deceive us, I wished to suppose that nothing is just as they cause us to imagine it to be; and because there are men who deceive themselves in their reasoning and fall into paralogisms, even concerning the simplest matters of geometry, and judging that I was as subject to error as was any other, I rejected as false all the reasons formerly accepted by me as demonstrations. And since all the same thoughts and conceptions which we have while awake may also come to us in sleep, without any of them being at that time true, I resolved to assume that everything that ever entered into my mind was no more true than the illusions of my dreams. But immediately afterwards I noticed that whilst I thus wished to think all things false, it was absolutely essential that the ‘I’ who thought this should be somewhat, and remarking that this truth ‘ I think, therefore, I am’ was so certain and so assured that all the most extravagant suppositions  brought forward by the sceptics were incapable of shaking it, … [24]“


የዴስካርት አካኼድ ፤ መጠርጠር የተቻለውን ነገር ኹሉ አስወግዶ ፤ በእርግጠኝነት ማወቅ የእሚችሉትን ነገር ለማስቀረት የኼደበት አካኼድ ፤ አንድ ትልቅ ሕንፃ የእሚገነባ መሐንዲስ ፤ መሠረቱን ከመጣሉ በፊት ጠንካራ መሬት እስኪ ያገኝ ድረስ ቆፍሮ እና ሕንፃውን መሸከም የእማይችለውን ፥ የእማይረጋውን አፈር ከአስወገደ በኋላ የእሚያገኘውን ፤ ያንን ጠንካራ መሬት የመሠረቱ መሸከሚያ አድርጎ ትልቁን ህንፃ እንደ እሚያቆመው ፤ ዴስካርት ሊጠረጠሩ የእሚችሉ ማንኛውንም እውቀት የእሚባሉትን ነገሮች በሙሉ አስወግዶ ፤ እርግጠኛ ከኾነው እውቀት (በእርሱ አንፃር ) ‘ስለ እማስብ ስለ እዚኽ አለሁ’ በእሚለው ጀምሮ ወይንም ይኽንን የእማይናወጥ መሠረቱ አድርጎ በመነሳት ፤ አይደለም ስለ ቁስ እና ስለ ሒሳብ መሰል ስሌቶች ፤ እግዚአብሔር መኖሩን ራሱ እርግጠኛ መኾን እችላለኹ ወደ እሚል ድምዳሜ መጥቷል ፦


“ይኽንም ተከትሎ ፤ ቢያንስ ይኽ እጅግ ፍፁም የኾነው እግዚአብሔር ፤ ነው ወይንም አለ … “

“Consequently, it is at least as certain that God, who is a Being so perfect, is, or exists, … [24]“ 


ዴስከርት በእዚኽ መልኩ ምንም እንኳን የስሜት ህዋሶቻችን ግንዛቤአችንን ማዛባት ቢችሉም ፤ እንደ ሰው ትክክለኛውን እውቀት የማግኘት አቅም አለን ፤ ይኽም እውቀት የእሚታዩትን ብቻ ሳይሆን የእማይታየውን እግዚአብሔር እንኳን እስከ ማወቅ ሊደርስ ይችላል በሎ አስቀምጧል።  


ከሬኔ ዴስካርት በተጨማሪ የእንግሊዙ የፖለቲካ ሳይንቲስት እና ፈላስፋ ጆን ሎክ ፤ ከሬኔ ደስካርት ጋር ተቀራራቢነት ስለ አለው ፤ የእምናየው ግዑዙ ዓለም በእውነት ያለ ነው ወይንስ በኃሳባችን ውስጥ የአለ የኃሳብ ሰበዝ? ለእሚለው ጥያቄ ፤ ግዑዙ ዓለም ህልም ወይንም በኃሳባችን የፈጠርነው ቅዠት ሰአይሆን ፤ በእውን ያለ ነው ለማለት የእሚከተለውን ብሏል ፦


    “ማንም በህልምም እንደ እዛው ነው ቢል ... ይኽ ሰው ፥ በእሳት ውስጥ በህልም መኾንና በውን የመኾን ልዩነትን ይረዳል ብዬ አምናለኹ ። ነገር ግን ይኽ ሰው በድጋሚ እጅግ ተጠራጣሪ ለመኾን አስቦ ፤ በውን በእሳት ውስጥ መኾን የእምትለው ነገር ራሱ ህልም ነው ፤ ስለ እዚኽ እንደ እሳት የአሉ ነገሮች በተጨባጭ ከእኛ ውጭ መኖራቸውን ጨምሮ ምንንም ነገር በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም ቢል ፡ እንዲኽ እለዋለኹ ፥ እርካታ እና ህመም የእሚባሉት ስሜቶች ፤ ከእኛ ውጭ የአሉ ቁሶች  ፤ በስሜት ህዋሶቻችን አማካኝነት በውናችን ወይንም በህልማችን የእሚፈጥሩብን ዓዕምሮዋዊ ህትመቶች ናቸው ፤ እውቀትንም ኾነ በሕይወት መኖርን ደግሞ የእምንፈልገው ለእዚኹ ነው ፤ ደስታ ወይንም ሰቆቃ የእምንለውን ዋና ነገር ለመለማመድ ።”


“If anyone say, a dream may do the same thing,…That I believe he will allow a very manifest difference between dreaming of being in the fire, and being actually in it. But yet if he be resolved to appear so sceptical as to maintain, that what I call being actually in the fire is nothing but a dream; and that we cannot thereby certainly know, that any such thing as fire actually exists without us: I answer, That we certainly finding that pleasure or pain follows upon the application of certain objects to us, whose existence we perceive, or dream that we perceive, by our senses; this certainty is as great as our happiness or misery, beyond which we have no concernment to know or to be [25].”


ይኽ የጆን ሎክ ፤ ሐሳብ ሲብራራ ፤ በእርግጥ በህልሜም እንደ ውኔ አስባለኹ ፤ ኾኖም ፥ በውኔ እና በህልሜ መኾኑን ግን የመለየት ብቃት አለኝ ምክንያቱም ፦ ማንም በህልሙ እሳት ውስጥ ገብቶ ቢቃጠል እና በውኑ እሳት ውስጥ ገብቶ ሲቃጠል የአለውን ልዩነት ያውቀዋል ፤ ነገር ግን ፥ አይ ይኽ በውን የእምትለው ነገር ራሱ ህልም ነው ካለ ፤ ዋናው ቁም ነገር ፤ በውን ይኹን በህልም ፤ የደስታ እና የኃዘን ስሜት ህትመት በህሊናችን ላይ የእሚፅፉብን ነገሮች ከእኛ ውጭ ያሉ ነገሮች መኾናቸው ነው ።


እነዚኽ ከእኛ ውጭ ያሉ ነገሮች ደግሞ ፥ ወይ ያሳዝኑናል ወይንም ያስደስቱናል ፤ እኛም እንደ ሰው ፤ ደስታን ከመጨመር እና ኃዘናችንን ከመቀነስ የአለፈ እውቀትን የእምንፈልግበት ወይንም መኖር የእምንፈልግበት ምንም ምክንያት የለም ፤ ስለ እዚኽ ፦ በውኔ ይኹን በህልሜ ፤ ከእኔ ውጭ ያሉ ነገሮች ወይ ያስደስቱኛል ወይንም ያሳዝኑኛል ፤ ይኽን እርግጠኛ ከኾንኩ ወይንም ቁሱ ዓለም ከእኔ ኃሳብ ውጭ የአለ መሆኑን እርግጠኛ ስለሆንኹ ፤ የማወቄ ግቡን ፥ እርሱም መደሰት ወይንም ኃዘንን መቀነስ እርግጠኛ ነኝ ፤ የእሚያስፈልገውም እርሱ ነው ።

በእኔ እምነት ፤ በስሜት ህዋሶቻችን አማካኝነት ፤ ከእኛ ውጭ የአሉ ነገሮችን ፤ እንደኾኑት (as they are) ለመገንዘባችን ወይንም ይኽ ግንዛቤያችን ህልም አለ መኾኑን ተጨማሪ ማሳያ መኾን የእሚችለው ፤ የጋራ ግንዛቤ (Common Understanding) መኖሩ እና ይኽ የጋራ ግንዛቤ ደግሞ ትውልድ ተሻጋሪ መኾኑ ነው ።


እሳት የእሚሰጠው የማቃጠል ስሜት በአንድ ግለሰብ ብቻ የተወሰነ ሰአይሆን በቋሚነት ኹሉም ሰዎች የእሚጋሩት ነው ፤ ይኽ ዓይነቱ የጋራ ግንዛቤ ራሱ በህልም ውስጥ ቢሆንስ እንደ አይባል ፤ በህልሜም ሆነ በውኔ እኔ ፥ እኔ መሆኔን እማውቅ እና ከሌላ ሰው የእሚመጣን መረጃ መለየት የእምችል ነኝ ፤ ይኽም በመሆኑ የጋራ ልምምዱ  በህልሜ ቢኾንስ ብሎ የእሚጠራጠረው አዕምሮ ራሱ ሞቶ እና ታሪክ ኾኖም እሳት ተመሳሳይ የማቃጠል ሥራውን በእኔ ላይ መቀጠል መቻሉ  እና ይኽንንም ኃሳብ በአሉት እና በእሚመጡት ሰዎች ኹሉ ላይ  ማተም (impress) ማድረግ መቻሉ ፤ እሳት ከእኛ ውጭ ነው ብለን ማወቃችን እርግጠኛ እውቀት እንደኾነ መያዝ እንችላለን ። በእዚኽም መሠረት ፤ መላው በስሜት ሕዋሳችን የእምንገናኘው ቁሳዊው ዓለም ከሞላ ጎደል እንደ እምንገነዘበው እንደ እዛው ነው።  


መጠራጠር ፣ መጠየቅ ፣ መፈተሽ የሳይንስ ግብ ነው ። 


ሳይንስን እንደ ከውር ወይንም ማንጠሪያ ብንወስደው ፤ መዓድኑን ከቆሻሻው የእሚለይ ማጣሪያ እንጂ አንድ እውቅ ምሁር የእማይለወጥ የተፈጥሮ ሕግ በምርምር አግኝቷል እና እንደ ወረደ ተቀበሉት ማለት አይደለም ።

የወቅቱ ፈላስፎች ስለ እማውቀው ነገር እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለኹ ? የእሚሉትን ጥያቄዎች ከእላይ በአየነው መልኩ ሲመልሱ ፤ እውቀትን እንዴት ነው የእማገኘው? በእሚለው ጥያቄ ላይ ፤ ቶማስ ኾብስ (Thomas Hobbes እ.አ.አ.1588-1679 ዓ.ም.) እና ጆን ሎክ (John Locke እ.አ.አ.1632 – 1704 ዓ.ም.) የተባሉት የእንግሊዝ ፈላስፎች ፤ እውቀትን ከአከባቢያችን በስሜት ህዋሶቻችን አማካኘነት እና በማሰላሰል አቅም እንደ እምናዳብራቸው በእየራሳቸው መንገድ አስቀምጠዋል ።


ቶማስ ኾብስ (Thomas Hobbes ) እንደ እዚኽ ብሏል ፦


“የሰወችን ኃሳብ በተመለከተ ፥ መጀመሪያ ለብቻቸው እመለከታለሁ … በተናጠል(ብቻቸውን) አንድ የኾነ ይዘት ወይንም ከእኛ ውጭ ያለ ቁስ ፥ በተለምዶ ነገር/ጥጥር ብለን ለእምንጠራው ተምሳሌቶች ወይንም መልኮች ናቸው ። እነ እዚኽም ንጥር/ነገር/ቁስ እንደ ዓይን እና ጆሮ ባሉ የስሜት ህዋሳቶቻችን በኩል የተለያየ ዓይነት መልክ ይዘው ይቀርቡልናል ። የእነ እዚኽ መልኮች ኹሉ ምንጭ ስሜቶቻችን ናቸው ፤ ምክንያቱም ፦ በስሜታችን በኩል በከፊል ወይንም በሙሉ ሳያልፉ በአዕምሮዋችን ውስጥ የአሉ ግንዛቤዎች/እሳቤዎች ስለ ሌሉ ። የቀሩት ከእነዚኽ ከዋነኞቹ ይቀዳሉ ።”


“Concerning the thoughts of man, I will consider them first singly ...Singly, they are everyone a representation or appearance of some quality, or other accident of a body without us, which is commonly called an object. Which object worketh on the eyes, ears, and other parts of a man’s body, and by diversity of working produceth diversity of appearances. The original of them all is that which we call sense, (for there is no conception in a man’s mind which hath not at first, totally or by parts, been begotten upon the organs of sense). The rest are derived from that original. [26] “


ከእዚኽም ጋር ፤ ተመሳሳይነት የአላቸው ኃሳቦችን ፤ ጆን ሎክም ሲያስቀምጥ እናገኛለን ፦ 


“አዕምሮዋችን በውጫዊ እና ተጨባጭ ነገሮች ላይ ወይንም በአዕምሮዋችን ውስጣዊ አሰራሮች ላይ በእሚያደርገው ማሰላሰል የእሚቀበላቸው ወይንም የእሚያስባቸው ነገሮች ናቸው የግንዛቤዎቻችን(የማስተዋላችን) መሰረቶች ።”

“Our observation employed either, about external sensible objects, or about or the internal operations of our minds perceived and reflected by ourselves, is that which supplies our understanding with all the materials of thinking [25]. “


እውቀት እንዴት ነው የእሚዳብረው ለእሚለው ጥያቄ ኼግል የተባለው የጀርመን ፈላስፋ ፤ እውቀት በእየ ዘመኑ የእሚነሱ ኃሳብ አመንጪዎች እና ኃያሲዎቻቸው ፤ በእሚያደርጉት የኃሳብ ፍጭት የእሚዳብር ነው ለማለት ዲያሌክቲክስን በእራሱ መንገድ በድጋሚ አስተዋውቋል። በእዚኽም መሠረት ፤ አንዱ ፈላስፋ በአንዱ ጉዳይ ላይ አንድ ኃሳብ ሲያቀርብ ፤ ከእርሱ በኋላ የእሚነሳው ሌላው ፈላስፋ ደግሞ በእርሱ ኃሳብ ላይ ኃያሲ ሲሆን በስተመጨረሻ አስታራቂው ወይንም መካከለኛው ኃሳብ እውቀት እየሆነ ይመጣል ፤ ቀለል ባለ አገላለጽም Thesis, antithesis and synthesis የእሚባሉት ታሪካዊ ኺደቶች ናቸው እውቀትን ወደ ብርኃን የእሚያመጡት ማለት ነው። 


መግቢያው ላይ እንደ አልነው ሳይንሳዊ ትችትን እቀበላለው የእሚለው ማርክስ ግን የማርክሲዝም ፍልስፍና ዋነኛ መጽሐፍ ከእሚባሉት በአንደኛው ፦ የጀርመን ኃሳባዊነት (German Ideology) በእሚለው መጽሐፉ ላይ ፤ ኃሳብ እና ሕያሱ (ትችቱ) ሔግል እንደ እሚለው ወደ ፋይዳ የአለው እውቀት አያመሩም ለማለት ይኽን ብሏል ፦ 


“አንድ የእሚዘነጉት (የሔግል ደቂቃን) … ተቃውሞዋቸው  ሐረጎች ላይ የተወሰነ መኾኑን ነው ፤ ውጊያቸው የእዚኽን ዓለም ሐረጎች ላይ ብቻ እስከ አተኮሩ ድረስ ፤ በተጨባጭ የአለውን ዓለም እየተዋጉትት እንዳልኾነ ግልፅ ነው ።”

“They (Hegelians) forget that they … are opposing nothing but phrases, and they are in no way combating the real existing world when they are combating solely the phrases of this world. [15]“


ማርክስ ይኽን የእሚለውም ፤ ዓለምን ወይንም ነባራዊውን ስረዓት አፍርሶ እንደ አዲስ የእሚሰራ እውቀት እንጂ ሌላው ዓይነት እውቀት ፋይዳቢስ ነው ከእሚል አስተሳሰብ በመነሳት ነው ፦


“ፈላስፎች ዓለምን በተለያየ መንገድ በመተንተን ላይ ብቻ አተኩረዋል  ፤ ቁም ነገሩ ግን ዓለምን መቀየር ነው ።”

“The philosophers have only interpreted the world, in various ways; the point is to change it [27].”


ከእላይ የአሉት ሬኔ ዴስካርት ፣ ቶማስ ሆብስ ፣ ጆን ሎክ እና ፍሬድሪክ ኼግልስ እውቀትን በተመለከተ የተለያየ ኃሳብ ቢያነሱም ዋናው ኃሳባቸው ከላይ በአስቀመጥነው ሳይንሳዊ መንገድ ርግጠኛውን እወቀት ወደ ብርኃን በማምጣት ላይ ያተኮረ ነው። 


ሳይንሳዊ ነኝ የእሚለው እና ነገር ግን ሳይንሳዊ የእውቀት ዘዴዎች በሙሉ ደፍጥጦ በሳይንስ ያልተረጋገጠ እውቀትን ከሰማይ እንደ መጣ ትዕዛዝ ተቀበሉ የእሚለው ማርክስ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫው ደግሞ ነባራዊውን እውቀት እና በእዚኽ እውቀት የተፈጠረው ስረዓት የእማያጠፋ እውቀት ፤ እውቀት ተብሎ ሊወሰድ አይገባም የእሚል ነው። 


ማርክስ ይኽንን ኃሳቡን በከምኒስት ማንፌስቶ ላይ በእዚኽ መልኩ አስቀምጧል ፦


“ቡርዥዋዚው ከእዚኽ ቀደም የተከበረውን እና ሰዎች በአክብሮት ይይዙት ከነበረው ሞያ ኹሉ ላይ የክብራቸውን ፀዳል ገፏል ። ሊቁን ፣ ጠብቃውን ፣ ቄሱን ፣ ባለ ቅኔውን ፣ የሳይንሱን ሰው ፤ ኹሉንም ወደ ምንደኝነት ቀይሯል ።

ቡርዥዋዚው ፤ ቤተሰብን ጋርዶ ይዞ የነበረውን የፍቅር መጋረጃ አንስቶ ፤ ተራ የገንዘብ ግንኙነት አድርጎታል ። …

ዘመናዊው የቡርዥዋ ማሕበረሰብ ፤ በምርት ግንኙነቱ (ቀጣሪ እና ተቀጣሪ) ፣ በልውውጥ (ሽያጭ) እና የግል ንብረት ፣ እጅግ ግዙፍ የማምረቻ እና የልውውጥ አቅም ገንብቶ ፤ በድግምቱ በከርሰ ምድር ያሉትን የክፉ መናፍስት ኃይላት ጠርቶ ካወጣ በኋላ ሊቆጣጠራቸው እንደ አልቻለ ጠንቋይ መስሏል ።  …

ቤተሰብን ማፍረስ! እጅግ ፅንፈኛ የእሚባለው የለውጥ ናፋቂ ራሱ በእዚኽኛው የከሚኒስቶች እቅድ ይቆጣል ። … እየከሰሳችኹን የአላችኹት ልጆች ላይ በቤተሰቦቻቸው የእሚደርስባቸውን ብዝበዛ ለምን ታስቆማላችኹ ብላችኹ ነው? ይኽ ውንጀላ ጥፋተኝነታችንን የእምንቀበልበት ነው ። …

እንደገናም ከምኒስቶች ፤ ሐገርን እና ዜግነትን ለማጥፋት ይሰራሉ የእሚባል ነቀፋ ይደርስባቸዋል ። ሠራተኛ ሰዎች ሐገር የላቸውም! …

‘ያለጥርጥር’ ፤ እንደ እዚኽ መባሉ አይቀርም ፤ ‘ኃይማኖታዊ ፣ ህሊናዊ ፣ ፍልስፍናዊ አና የፍርድ እሳቤዎች በታሪካዊ እድገት ኺደት ውስጥ መሻሻል አሳይተዋል ። ነገር ግን ኃይማኖት ፣ ህሊና ፣ ፍልስፍና ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ፣ ሕግ ግን ይኽ ለውጥ አላጠፋቸውም ።’

‘በተጨማሪም ፤ ነፃነት ፣ ፍትሕ ፣ ወዘተ ፤ የእሚባሉ ፤ እስካ ዛሬ በነበሩ ኹሉም የማሕበረሰብ ደረጃዎች ውስጥ የነበሩ ዘላለማዊ እውነቶች አሉ ። ከምኒዝም ግን እነ እዚኽን ዘላለማዊ እውነቶች በአዲስ መሠረት ላይ ከማዋቀር ይልቅ እነ እዚኽን ዘላለማዊ እውነቶችን ያጠፋል ፣ ኃይማኖትን ያጠፋል ፣ ኹሉንም የስነምግባር አስተምህሮ ያጠፋል ፤ ስለ እዚኽም ፦ ከእዚኽ ቀደም ከነበረው ታሪካዊ ልምምድ ኹሉ በተቃራኒ የቆመ ነው’ … 

እነ እዚኽ ኹሉ የቀደመው ዓለም ማሕበራዊ አስተውሎቶች ፤ ምንም ዓይነታቸው እና ቁጥራቸው ቢበዛም ፤ በአንድ ጠቅላላ ማዕቀፍ ስር መሆናቸው ምንም ሊያስገርም አይገባም ፤ ይኽም በመሆኑ መሰረታቸው የኾነው የመደብ ተቃርኖ እስከ አልጠፋ መጥፋት አይችሉም። 

የከውሚውንስት ለውጥ (አብዮት) ከባሕላዊው የንብረት ግንኙነት አስተሳሰብ እጅግ የተለየ በመሆኑ ፤ እድገቱ ድንገተኛ የኾነ ከባህላዊው አካኼድ መገንጠልን ቢያስከትል ምንም አይገርምም ።”

“The bourgeoisie has stripped of its halo every occupation hitherto honored and looked up to with reverent awe. It has converted the physician, the lawyer, the priest, the poet, the man of science, into its paid wage laborers.

The bourgeoisie has torn away from the family its sentimental veil and has reduced the family relation to a mere money relation. …

Modern bourgeois society, with its relations of production, of exchange and of property, a society that has conjured up such a gigantic means of production and of exchange, is like the sorcerer who is no longer able to control the powers of the nether world whom he has called up by his spells. …

Abolition of the family! Even the most radical flare up at this infamous proposal of the Communists. … do you charge us with wanting to stop the exploitation of children by their parents? to this crime we plead guilty. …

The communists are further reproached with desiring to abolish countries and nationality. The working men have no country. …

‘undoubtedly,’ it will be said, ‘religious, moral, philosophical, and juridical ideas have been modified in the course if historical development. But religion, morality, philosophy, political science, and law, constantly survived this change.’

‘there are, besides, eternal truths, such as Freedom, Justice, etc., that are common to all states of society. But communism abolishes eternal truths, it abolishes all religion, and all morality, instead of constituting them on a new basis; it therefore acts in contradiction to all past historical experience.’ …

That the social consciousness of past ages, despite all the multiplicity and variety it displays, moves within certain common forms, or general ideas, which cannot completely vanish except with the total disappearance of class antagonisms.

The communist revolution is he most radical rupture with traditional property relations; no wonder that its development involved the most radical rupture with traditional ideas. [18]“ 


በእዚኽ ከከምኒስት ማንፌስቶ ላይ በተቀነጨበው ጽህፍ ላይ ፤ ማርክስ እያለ የአለው ፦ የግል ንብረት ባለቤትነትን የእሚፈቅደው እና በነጻ ገበያ የንብረት ሽያጭ እና ግዢን የእሚፈቅደው የካፒታሊስቱ ስረዓት ፤ ሞያን አዋርዷል ፣ ቅዱስ እና የተከበሩ የእሚባሉ ግንኙነቶችን አራክሷል በአጠቃላይም ኹሉንም ነገር ተራ ሸቀጥ አድርጓል ይኽም በመሆኑ ይኽ ነባራዊው ስረዓት እስከ እነ አካቴው መጥፋት አለበት ነው ።


ቀጠል አድርጎም ፤ ቤተሰብን እንኳን ሳይቀር ኹሉኑም ነባራዊ ማሕበራዊ ተቋሟት ለማፍረስ መነሳታችን ፤ አንዳንዶችን ቢያስደነግጥም ፤ እኛ ግን ኃይማኖት የሌለበት ፣ የሞያ ክፍፍል የሌለበት ፣ የግል ንብረት የሌለበት ፣ ሐገር የሌለበት ፣ በአጠቃላይ ምንም ዓይነት ማሕበራዊ ልዩነት የሌለበት አዲስ ማሕበራዊ አወቃቀር ዓልመን ተነስተናል እና የእምናፍርበት አይደለም ብሎ በድፍረት እያስቀመጠ ነው ። 


“ኃይማኖት ፣ ህሊና ፣ ፍልስፍና ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ፣ ሕግ” በለውጥ ኺደት ይሻሻላሉ እንጂ እስከ እነ አካቴው አይጠፉም ይባላል ፤ ይኽንንም አባባል ማርክስ ልክ አለመሆኑን ለማሳየት እየ አቀረበ የአለው ሙግት ፤ የአኹኑ ኃይማኖት ፣ ህሊና ፣ ፍልስፍና ፣ የፖለቲካ ሳይንስ፣ ሕግ የኖሩት የመደብ ልዩነት በመኖሩ ስለሆነ ፤ የመደብ ልዩነት ምንጭ የሆነውን የግል ንብረት ባለቤትነት መብት ስናጠፋ እነርሱም አብረው ይጠፋሉ እና ከምኒስት የሆነ ሰው ኃይማኖት ፣ ህሊና ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ፣ ወዘተ ፤ እንደ ትክክል መቀብል የለበትም በማለት ነው ጸረ ሳይንስነቱን የእሚያስቀምጠው። 


ጠቅለል እና አጠር በአለ አገላለጽ ማርክሲዝም ማለት ፦  ነባራዊው ዓለም ከእነ ተቋሟቱ ጠፍቶ አዲስ ማርክሲስት ዓለም መፈጠር አለበት ማለት ነው ። ሰዎች እንደ መልካም የእሚያዩዋቸው ፦ ነፃነት ፣ ፍትሕ ፣ የግል ንብረት ፣ ቤተሰብ ፣ ኃይማኖት ፣ ፍልስፍና ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ፣ ወዘተ ፤ ኹሉ አጥፍቶ ፤ በራሱ ማለትም በማርክሲዝም ፍልስፍና ብቻ የእሚመራ አዲስ ስረዓት መፍጠር የእሚፈልግ ፤ ርዕዮት ነው ።


እዚኽ ላይ ተመስርተን ያየነውን ማርክሲዝም ጸረ ሳይንስ ነው የእሚለውን ድምዳሜ ፤ አፍቃሪ ማርክሳዊያን ከእላይ በዳስ ካፒታል መቅድም ላይ እንደ አስቀመጠው ዓይነት ኃሳቦችን እና ማርክሲዝም በጠቅላላው ሳይንሳዊ ነኝ የእሚልበትን አባባል እያጣቀሱ ማርስክሲዝም ሳይንሳዊ እንጂ ጸረ ሳይንስ አይደለም ብለው ሊቃወሙ ይችላሉ።


ሳይንሳዊነት ግን ሳይንሳዊ ትችትን እቀበላለው በማለት ወይንም ሳይንሳዊ ነኝ በማለት ሳይሆን ፤ እውቀትን በምርምር ፣ በጥየቃ ፣ በማነጻጸር ፣ በመፈተሽ ፣ ለመያዝ መፈለግ ወይንም ይኽንን እወቀትን የመያዣ እና የማረጋገጫ መንገድ ትክክለኛነት መቀበል ማለት በመሆኑ ፤ ማርክሲዝም ሳይንሳዊ ነኝ ቢልም ይኽን ሳይንሳዊ የእውቀት መያዣ እና ማረጋገጫ መንገድ የእሚቃወም እና በእዚኽ መንገድ የዳበሩ ፤ ከማርክሲዝም ውጭ ያሉ እውቀቶችን እንደ ሳይንሳዊ የእማይቀበል በመሆኑ ጸረ ሳይንሳዊ ነው።


አንድ እዚኽ ጋር ሊሰመረበት የእሚገባው ጉዳይ ፤ የማርክስ ጸረ ሳይንሳዊነት ሊወገዝ የእሚገባው ጸረ ሳይንስ በመሆኑ በራሱ (per se) ብቻም ሳይሆን ፤ የሰው ልጆች እውቀትን የእሚጨብጡበት ከእላይ ከአስቀመጥናቸው ኹለት ሳይንሳዊ መንገዶች ውጭ ሌላ መንገድ የሌለ በመሆኑን ፤ ሌላ አዲስ ሳይንሳዊ መንገድ ሳያቀርቡ ሚዛን በእማይደፋ ሙግት ነባራዊው እውቅቶችን በጅምላ ይጥፋ በማለቱም ጭምር ነው።


ማርክስ ለእዚኽ ጸረ ሳይንሳዊነቱ የእሚያቀርበው ምክንያት ከፍተኛ የአመክንዮ መፋለስ (logical fallacy) የአለው በመሆኑ ፤ ማርክስ ጸረ ሳይንስ ሲሆን ፤ የእኔን ርዕዮት በጥየቃ እና በምርምር የእሚያሳጡትን ሳይንሳዊ መርሆች መሸሽ ፈልጋለኹ ለማለት ከመፈለግ ያለፈ ትርጉም ሊሰጠውም አይችልም።


ምክንያቱም ፦ ማርክስ ነባራዊው ፍልፍስና ፣ ሕግ ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ፣ ወዘተ ፤ መጥፋት አለባቸው ለማለት የእሚያቀርበው ምክንያት ፤ የነባራዊው ዓለም እውቀት በኃሳባዊያን (Idealists) የተያዘ ወይንም በእነርሱ የመጣ በመሆኑ ፤ የምኞት አስተሳሰብ እና ከቁሳዊያኑ(Materialists) ጋር የእሚቃረን ነው በእሚል ነው። 

በማርክስ እምነት እውቀት ፣ አስተውሎት የቁሱ ዓለም ነጸብራቅ እንጂ በራሱ ህልውና የሌለው በመሆኑ ፤ ከቁሱ ዓለም ያልመነጨ እውቀት ሊኖር አይገባውም ።


ለምሳሌ ፦ የማርክሲዝም መሠረት የሆነው ፤ ለመጠፋፋት የእሚደረግ የመደብ ግጭት ፤ ሰዎች ተመራምረውበት የእሚደርሱበት እውቀት ሳይሆን ፤ ቁሳዊው ዓለም የእሚመራበት መርህ በመሆኑ ፤ የሰዎች ግንዛቤ ምንጭ የሆነው ቁሳዊው ዓለም ፤ ሰዎች ሳይወዱ በግድ በመደብ ተከፋፍለው ለመጠፋፋት እንዲጋጩ ግድ ስለ እሚላቸው ነው የእሚለው የማርክሲዝም ፍልስፍና ፤ አንድ ኃሳባዊ ተነስቶ ፤ ሰዎች ሲፈጠሩ በልባቸው ውስጥ የአንዱ መደብ አባል ሆነው ፤ ተቃራኒያቸውን መደብ ለማጥፋት እንዲታገሉ የእሚያደርጋቸው አስተሳሰብ አብሯቸው ይወለዳል  ቢል ፤ ለማርክስ ሳይንሳዊነት የለውም ፤ በአጭሩ ለማርክስ ቁሳዊ ኹኔታ ያለፈጠረው ኃሳብ ወይንም እውቀት መኖር አይችልም። 


ይኽ የማርክስ ምክንያት ወይንም አመክንዮ ግን ኹለት ስህተት አለው ፦

1)    የነባራዊው ማሕበራዊ ሳይንስ ፤ ኃሳባዊ (Idealist)  የፍልስፍና መሠረት የአለው በመሆኑ ፤ ከተግባር የተፋታ ነው ወይንም ሳይንሳዊ አይደለም ማለት አይቻልም።


2)    ማርክስ ራሱ የሰዎችን ቁሳዊ ኹኔታ ለመለወጥ ኃሳባዊ ሙግት እየ አካኼደ ወይንም የእሚፈልገው ማሕበረ ኢከነሚ በአካል ሳይከሰት በፊት በአካል መከሰት አለበት ብሎ ኃሳባዊ ሙግት እየ አደረገ ፤ ነባራዊው ሳይንስ በኃሳባዊ አስተሳሰብ ላይ ስለ ተመሠረተ ስህተት ነው ብሎ መሞገት ተፋልሶ (fallacy) ለመሆኑ ብዙም አጠያያቂ አይደለም።


ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው ፤ በሳይንሳዊ መንገድ ውኃን ማጣራት እና ለሕብረተሰብ ማከፋፈል አስፈላጊ መሆኑን ለማስረገጥ በውኃ የስነ ፍጥረት ታሪክ ላይ መስማማት የለበትም።  ውኃን የፈጠረው ኢምዉታዊ የሆነው አምላክ ነው ብሎ ማመን (ኃሳባዊነት) ወይንም ውኃ የተፈጠረው ያለ አምላክ እንዲኹ ከምንም በድንገታዊነት ሳይፈጠሩ በራሳቸው በእሚኖሩ በንጥረ ነገሮች ግጭት ነው የተፈጠረው ብሎ ማመን (ቁሳዊነት) ፤ ውኃ ለሰው ልጅ የእለት ተእለት ኑሮ እንደ እሚያስፈልግ በሳይንሳዊ መንገድ ለማስረገጥ የእሚጠቅመው ነገር የለም። 

በተመሳሳይም ፤ በማሕበራዊ መስኩ ፤ ኃይማኖት ለሰው ልጅ ማሕበራዊ ጤንነት የእሚያስፈልግ ተቋም ነው ወይንስ አይደለም የእሚለውን በሳይንሳዊ መልኩ ለመበየን ፤ ኃይማኖት ከኃሳባዊነት ወይንስ ከቁሳዊነት ጎራ መፈረጁ ብዙም ፋይዳ የለውም።


አንድ የማሕበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ ፤ የኃይማኖትን ፋይዳ ፤ በግለሰብ እና በማሕበረሰብ ሕይወት ውስጥ የአላቸውን ፋይዳ ለመረዳት ፤ ማድረግ የእሚጠበቅበት ፤ ኃይማኖት በሰው ልጆች ዘንድ መከሰት ከጀመረበት ግዜ አንስቶ ኃይማኖት የሰዎችን በሕይወት የመቀጠል እና ሕይወትን የተሻለ የማድረግ ግብ አግዟል ወይንስ አዳክሟል በእሚል ፤ ኃይማኖት የነበረውን ሚና ከታሪክ መቃኘት እና በእዚኽ ላይ በመመርኮዝ ወደ ድምዳሜ መድረስ ነው የእሚጠበቅበት። 


በኢከነሚ ሳይንሱም መስክ ፤ የኢከነሚክስ መርህዎች በልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ አንጻር ፤ በኃሳባዊነት ወይንም በቁሳዊነት ላይ መመሥረታቸው አይደለም ዋናው ጉዳይ ። ይልቁንም በኃሳባዊነት ላይ ይመስረት በቁሳዊነት ላይ ፤ በኢከነሚው ረገድ ለግለሰቦች ግላዊ እና ማሕበራዊ ፍላጎታቸው ሸቀጦችን በተነጻጻሪነት በርካሽ እና በጥራት ማቅረብ ይችላሉ ወይንስ አይችሉም በእሚሉ መሰል መመዘኛዎች ነው መመዘን የአለባቸው።

 

እንደ እዚኹም ከፖለቲካ ሳይንስ ሊነጠል የእማይችለው የ”ፍትኽ ምንድ ነው?” ጥያቄ ፤ አንድ ሰው ኃሳባዊ ወይንም ቁሳዊ በመሆኑ ላይ የእሚወሰን አይደለም ፤ ማለትም ኹለት ሰዎች ኃሳባዊ እና ቁሳዊ ሆነው ፤ ፍትኽ ምንድ ነው በእሚለው ጥያቄ ላይ አንድ እና ተመሳሳይ መልስ ሊኖራቸው ይችላል።


ለምሳሌ ፦ ፍትኃዊ የኃብት ክፍፍል የቱ ነው በእሚለው ጥያቄ ላይ ፤ ኹለት ሰዎች ፤ በቁሳዊነት እና በኃሳባዊነት ሳይወሰኑ ፤ ፍትኃዊ የኃብት ክፍፍል ለኹሉም እንደ ማምረት አቅሙ ኃብትን የእሚያከፋፍለው ወይንም ከእዚኽ በተቃራኒ የማምረት አቅምን ሳያገናዘብ ለኹሉም እንደ ፍላጎቱ የእሚያከፋፍለው ነው የእሚል ኃሳብ ሊይዙ ይችላሉ። 


ይኽ የመላምታዊ ክርክር ጉዳይ ብቻም ሰዓይሆን ፤ ማርክስ እኔ ቁሳዊ ስለሆንኹ ወይንም በዓለም ላይ የአለው ቁሳዊ ነገር በሙሉ ያለ ፈጣሪ ወይንም ቅድመ እቅድ በራሱ ግዜ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም እንደ አለ ነው የአለው ብዬ በማመኔ ነው ፤ የሰው ልጅ ግንዛቤ የቁሳዊው ዓለም ነጸብራቅ ነው የአለኹት ቢልም ፤ ከእላይ እንደ አየነው ከኃሳባዊያን ወገን ወይንም ቁሳዊው ዓለም በእማይታየው ፈጣሪ እቅድ እና ኃይል መሠረት ነው የተፈጠሩት የእሚሉት ቶማስ ሆብስ እና ጆን ሎክም ብለውታል፦


“… በተናጠል(ብቻቸውን) አንድ የኾነ ይዘት ወይንም ከእኛ ውጭ ያለ ቁስ ፥ በተለምዶ ነገር/ጥጥር ብለን ለእምንጠራው ተምሳሌቶች ወይንም መልኮች ናቸው ።”

“..., they are everyone a representation or appearance of some quality, or other accident of a body without us, which is commonly called an object. [26] “


ከእዚኽም ጋር ፤ ተመሳሳይነት የአላቸው ኃሳቦችን ፤ ጆን ሎክም ሲያስቀምጥ እናገኛለን ፦ 


“አዕምሮዋችን በውጫዊ እና ተጨባጭ ነገሮች ላይ ወይንም በአዕምሮዋችን ውስጣዊ አሰራሮች ላይ በእሚያደርገው ማሰላሰል የእሚቀበላቸው ወይንም የእሚያስባቸው ነገሮች ናቸው የግንዛቤዎቻችን(የማስተዋላችን) መሰረቶች ።”


“Our observation employed either, about external sensible objects, or about or the internal operations of our minds perceived and reflected by ourselves, is that which supplies our understanding with all the materials of thinking [25]. “


 እነ እዚኽ ከእላይ የተቀመጡት የኃሳባዊያን የቶማስ ሆብስ እና የጆን ሎክ ኃሳባት ፤ ከእዚኽ ቀጥሎ የማርክስን የሙግት ቁሳዊነት ስታሊን ከአስቀመጠበት አግባብ ጋር የአላቸው ልዩነት የቃላት እና የአገባብ ብቻ እንጂ የይዘት እንደ አልሆነ የእሚታይ ነው ፦


“…ተፈጥሮ ፥ ቁሳዊው ዓለም ኾኖ ቀዳሚ ከኾነ ፤ አስተውሎት ፥ ኃሳብ ደግሞ ኹለተኛ ፥ የእርሱ ቅጂ ከኾነ ፤ ቁሳዊው ዓለም ተጨባጩን እውነታ ከሰዎች አስተውሎ በተናጠል የእሚወክል ከኾነ ፥ አስተውሎት የእዚኽ ተጨባጭ ኹኔታ ነፀብራቅ ሲኾን ፤ የማሕበርሰብ ቁሳዊ ሕይወቱ ፥ ሕልውናው ቀዳሚ ፣ መንፈሳዊ ሕይወቱ ዳግማዊ ፥ ክፋይ ነው የእሚለውን ያስከትላል ፣ እናም የማሕበረሰብ ቁሳዊ ሕይወት ከሰዎች ፈቃድ ተነጥሎ በራሱ የእሚኖር ተጨባጭ እውነታ ሲኾን መንፈሳዊ ሕይወቱ ደግሞ የእዚኽ ተጨባጭ እውነታ ነፀብራቅ ፥ የማንነቱ ነፅብራቅ ይኾናል ።”

“Hence, the source of formation of the spiritual life of society, the origin of social ideas, social theories, political views and political institutions, should not be sought for in the ideas, theories, views and political institutions themselves, but in the conditions of the material life of society, in social being, of which these ideas, theories, views, etc..., are the reflection. [14]“


ይኽም በመሆኑ ፦ ማርክስ የግል ንብረት መብትን ማክበር ፣ ኃይማኖት ፣ ነባራዊው የፍትሕ ግንዛቤ ፣ ፍልስፍና ፣ ፖለቲካ ሳይንስ ፣ ወዘተ ፤ በአጠቃላይ ነባራዊው የማሕበራዊ ሳይንስ እና ፍልስፍና ፤ ድኃ እና ኃብታም ወይንም ተጻራሪ መደቦች  የእሚፈጥሩ በመሆናቸው መጥፋት አለባቸው የእሚለው ሙግቱ ሊያከራክር ቢችልም ፤ እነ እዚኽ ነባራዊ አስተሳሰቦች እና ተቋሞች ስህተት የሆኑት በኃሳባዊያን(Idealism) መሠረት ላይ ስለ ተመሠረቱ ነው ማለት ፤ ከሳይንስ ይልቅ በከኃዲ አምላኪነት የእሚደረግ የኃይማኖት ጽንፈኝነት አስመስሎታል ፤ ምክንያቱም ፦ በአሳማኝ ቅድመ ኹኔታ ላይ የተደገፈ ድምዳሜ በአለመሆኑ። 


አንድ ከኃዲ አምላክ ፤ እግዚአብሔር አለመኖሩን በምንም ሳይንሳዊ መንገድ ማስረዳት ባይችልም ፤ ኃይማኖተኛውን የሕይወትኽ ችግር ኹሉ የእሚመነጨው እግዚአብሔር አለ ብለኽ ከማመንኽ ነው እንደ

እሚለው ዓይነት ነው ፤ ይኽ የማርክስ የጸረ ነባራዊው ሳይንስነት ክርክር። 


ማርክስ ራሱን ጸረ ነባራዊው ማሕበራዊ ሳይንስ አድርጎ የእሚያቀርብበት ኹለተኛው የተሳሳተው ምክንያት ፤ የሰዎች ኃሳብ ተግባራቸውን ይወስናል በእሚለው የኃሳባዊያን መርኽ ላይ ስለ ተመሠረተ ነው በማለት ነው። 

በማርክስ የቁሳዊነት አስተሳሰብ ወይንም ርዕዮት መሠረት ፤ ሰዎች መጀመሪያ አስበው ሰአይሆን የእሚያደርጉት ወይንም ተግባራቸው ከኃሳባቸው ሰአይሆን የእሚመነጨው ኃሳባቸው በተግባራቸው ከእሚፈጠረው ተጨባጭ ኹኔታ ነው የእሚመነጨው የእሚል ነው ፦ 


የጀርመን ኃሳባዊነት በእሚለው መጽሐፍ ላይ ማርክስ እንደ እዚኽ ብሏል፦

“… አስተውሎት አይደለም ህይወትን የእሚወስነው ፤ ነገር ግን ፦ ህይወት ነው አስተውሎትን የእሚወስነው።”

“… It is not consciousness that determines life, but life that determines consciousness. [15]“


ለእዛኽም ነው በከውሚንስት ማንፌስቶ ላይ ፤ ቤተሰብ ፣ ኃይማኖት ፣ ሐገር ፣ ነጻነት ፣ ፍትሕ ፣ ወዘተ ፤ ይጥፋ ስንል አትደንግጡ ፤ ምክንያቱም ፦ እነ እዚኽ ተቋማት እና እውቀቶች ጥሩ የእሚመስላችኹ ፤ በካፒታሊስት ስረዓት ውስጥ ስለ እምትኖሩ ነው እንጂ ፤ አንድ ግዜ ካፒታሊዝምን ከአጠፋነው ፤ ቤተሰብ ፣ ሐገር፣ ነጻነት ፣ ፍትሕ ፣ ወዘተ ፤ እንደ እማያስፈልጉ ወገግ ይልላችኋል ለማለት ፦


“እነ እዚኽ ኹሉ የቀደመው ዓለም ማሕበራዊ አስተውሎቶች ፤ ምንም ዓይነታቸው እና ቁጥራቸው ቢበዛም ፤ በአንድ ጠቅላላ ማዕቀፍ ስር ናቸው ፤ እርሱም መሰረታቸው የኾነው የመደብ ተቃርኖ እስከ አልጠፋ መጥፋት አይችሉም።”

“That the social consciousness of past ages, despite all the multiplicity and variety it displays, moves within certain common forms, or general ideas, which cannot completely vanish except with the total disappearance of class antagonisms. [18]“

የእሚለው።

 

እንደ እዚኽ ብሎ የእሚሞግተው ማርክስ ግን ፤ አንድ በአካል የሌለ የከምኒስት አብዮት እና የከምኒስት ማሕበረሰብ አወቃቀር ለመፍጠር የኃሳብ ሙግት የእሚያቀርብ ሰው ነው። 


ማርክስ ሰዎች በኢከነሚ መደባቸው ተቧድነው ፤ ደም አፋሳሽ አብዮት በማድረግ ወደ መደብ አልባ የማሕበረሰብ አወቃቀር ላይ ይደረሳሉ የእሚለውን ኃሳቡን ሲይዝ እና ይኽም እንዲሳካ የመደብ ትግል አስተሳሰብ መዛመት አለበት ብሎ ሲሞግት ፤ የመደብ ትግል እና ሊፈጠር ይገባል የእሚለው መደብ አልባው ከምኒስታዊ ማሕበረሰብ ገና የአልተፈጠረ በመሆኑ ወይንም ይኽንን አስተሳሰብ ከእሚገኝበት ቁሳዊ ኹኔታ ውጭ ያገኘው በመሆኑ ወይንም ይኽንን አስተሳሰብ የቀረጸበት ቁሳዊ ኹኔታ በአለመኖሩ ፤ ኃሳብ ከተግባር አይቀድምም ብሎ ፤ የራሱ ኃሳቡ ተግባሩን እየቀደመው በአለበት ኹኔታ ፤ መከራከር አይችልም ወይንም እንደ እዚኽ አይነት ክርክር ተፋልሶ (fallacy) ነው። 


ይኽም ብቻ ሰአይሆን ፤ ማርክስ ራሱ በራሱ የማሕበረሰብ የመደብ ክፍፍል መሠረት ፤ የገዢ መደብ የእሚባለው ሆኖ እና ከራሱ መደብ በተቃራኒ (ወይንም ከእሚገኝበት ቁሳዊ ኹኔታ የአፈነገጠ አስተሳሰብ ይዞ)፤ የሠራተኛው እና የጭቁኑ ተቆርቋሪ ሆኖ ወይንም በሌላ አገላለጽ ፤ ከእሚኖርበት ቁሳዊ ኹኔታ ውጭ የሆነ አስተውሎ አዳብሮ እየ አለ ፤ የአኹኑ ሳይንስ የአኹኑ ማሕበረ ኢከነሚ ውጤት ነው ብሎ ፤ ቁሳዊ መሠረቱን ስናጠፋ አስተሳሰቡ ይጠፋል በእሚል ፤ የአኹን ሳይንሳዊ እውቀት መጥፋት አለበት የእሚልበት አስተሳሰብ ተፋልሶ (fallacy) የአለበት ለመሆኑ ማሳያ ነው።


ስለ እዚኽ ማርክስ ፤ በእዚኽ መልኩ ለያዘው ጸረ ማሕበረ ሳይንስ አቋም በመከራከሪያነት የእሚያቀርበው ምክንያት አሳማኝም አይደለም።


ይኽም በመሆኑ ማርክሲዝም ጸረ ሳይንስ ብቻም ሰአይሆን ፤ ጸረ ሳይንስ ሆኖ ፤ ነባራዊው ሳይንስ እና የአመረታቸውን እውቀቶች መጥፋት አለባቸው የእሚለው ፤ ከሳይንስ አግባብ ውጭ እና በተፋለሰ ሙግት ነው። 



4.    ማርክሲስዝም ህሊናቢስ ወይንም ጸረ ስነምግባራዊም ነው


ማርክሲዝም ህሊናቢስ ወይንም ጸረ ስነ ምግባር ነው ሲባል የማጥላላት ዘመቻ እና መሠረት የለሽ ክስ የእሚመስል ቢሆንም ፤ ማርክሲዝም ግን በካርል ማርክስ እና በፍሬድሪክ ኤንግሊስ በተጻፈው የከምኒስት ማንፌስቶ ላይ በግልጽ ፤ ማርክሲዝም ህሊናቢስ ወይንም ጸረ ስነምግባር እንደ ሆነ ያለ ምንም ማቅማማት ያውጃል፦


“ሕግ ፣ ሕሊና (ስነ ምግባር) ፣ ኃይማኖት ለእርሱ (ለሠራተኛው) ፤ ከበስተኋላቸው የቡርዥዋው ጥቅም የሸመቀባቸው ፤ የቡርዥዋዚው ዝበት (ባዕድ አምልኮት) ናቸው።”

“Law, morality, religion, are to him so many bourgeoisie prejudices, behind which lurks in ambush just as many bourgeoisie interests. [18]“


ይኽ በማንፌስቶው ላይ የተቀመጠው ኃሳብ በግልጽ እንደ እሚለው ፤ የሕግ የበላይነት ፣ የስነ ምግባር መመሪያ ወይንም ለህሊና ማደር ፣ መንፈሳዊነት ወይንም ኃይማኖተኝነት ፤ የቡርዣው ስረዓት ጥቅሙን የእሚያስከብርባቸው መሳሪያዎች በመሆናቸው ፤ ሠራተኛው ወይንም የሶሻሊስት አብዮተኛው ፤ በእነ እዚኽ ማታለያዎች ሳይገደብ ፤ የመደብ በአላንጣዎቹን ለማጥፋት ፤ ደም አፋሳሽ የመደብ ትግሉን ያለ ምንም ማቅማማት እና ማመንታት ማካኼድ አለበት ብሎ ፤ ሠራተኛውን የማሕበረሰብ ክፍል ሠራተኛውን በእሚቀጥሩት የማሕበረሰብ አካላት ላይ የእሚቀሰቅስ ነው።


ማርክሲዝም በእዚኽ መልኩ በአደባባይ ህሊና ቢስነትን ወይንም ጸረ ስነምግባራዊነትን ሲያወጅ ግን ሳይንሳዊነት ወይንም ተመራማሪነት ፤ በሕግ ማደርን ፣ ስነ ምግባራዊነትን እና መንፈሳዊነትን ፤ አል አስፈላጊ ስለ እሚያደርጋቸው ሰአይሆን ፤ የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ደም አፋሳሽ እና አጠፋፊ የመደብ ትግል ነው ለእሚለው ወይንም ቀበሮ ለሆነው የተጨባጫዊው የፖለቲካ ርዕዮት የበግ ለመድ የሆነው ማርክሲዝም ፤ ይኽ የስልጣን አመክንዮው ፍልስፍና ሰፊ ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያ እንዲሆን ፤ በጸረ ሳይንሳዊነቱ የአመክንዮ ተቋማትን እና የአዕምሮ ምርመራን እንደ አስወገደው ኹሉ ፤ በጸረ ስነ ምግባራዊነት ደግሞ ፤ የህሊና ክልከላ ወይንም ስነ ምግባርን ማስወገድ ግድ ስለ እሚለው ነው።


ለሕግ ማደር ፣ የበጎ ህሊና ባለቤት መሆን ወይንም መልካም የሆነ ስነ ምግባር መያዝ ፣ መንፈሳዊ እምነት ማዳበር ፤ በሰዎች ልጆች ሕይወት ውስጥ ባላቸው ትልቅ ታሪካዊ ቦታ ምክንያት ፤ አንድ ሰው እንዲኹ ተነስቶ ሕግ ፣ ህሊና እና መንፈሳዊነት አያስፈልጉም ወይንም የኃብታሞች (የቡርዣው) ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች ናቸው ስለ አለ ብቻ ፤ አብዛኛው የሰው ልጅ እንደ ቀላል ነገር አውጥቶ የእሚጥላቸው አይደሉም። 

ምክንያቱም ፦ በዘመናዊ እና ሳይንሳዊ የስነምግባር (Ethics) አስተምህሮ ፤ ሰው ለህሊናው ማደር የአለበት እና በእራሱ ላይ ሊደረግ የእማይፈልገውን ነገር በሌላ ሰው ላይ ለማድረግ መፈለግ የለበትም የእሚባለው ፤ መጽሐፍ ቅዱሱ “እንግዲኽ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የእምትወዱትን ኹሉ እናንተ ደግሞ እንዲኹ አድርጉላቸው”  ስለ እሚል ወይንም ይኽ በጭፍን የእምንታዘዘው አምላካዊ ትዕዛዝ ስለ ሆነ ሰአይሆን ፤ የሌላውን ሰው መብት በጣሰበት ልክ የእራሱ መብት አደጋ ላይ የእሚወድቅ በመሆኑ ነው። ይኽንን መሠረታዊ ሰብዓዊ ስነ ምግባር የሰው ልጅ ቢያንስ ከእነ ኮንፊሸስ ግዜ አንስቶ የተዋወቃቸው ለመሆናቸው ደግሞ ታሪክ ይነግረናል።  


“ሲዚ-ኪውንግ እንዲኽ ብሎ ጠየቀ ፥ “ሰው በህይወቱ ዘመን ኹሉ ሊከተለው የእሚችለው አንድ መርህ (ቃል) ይኖራል?” ፥ ጌታውም መለሰ፣ “ተራክቦ እንዲኽ ዓይነቱ ቃል አይደለምን? በአንተ ላይ እንዲደረግ የእማትፈልገውን ፥ በሌሎች ላይ አታድርግ።”  

“Tsze-kung asked, saying, “is there one word which may serve as a rule of practice for all one’s life?” The master said, “is not RECIPROCITY such a word? What you do not want done to yourself, do not do to others. [28]”


ይኽም በመሆኑ ፤ ደም አፋሳሽ የመደብ ትግል ብቸኛ የፖለቲካ ስልጣን መያዣ መንገድ ነው  ለእሚለው ማርክሲዝም ርዕዮታዊ በአላንጣዎች በሆኑት ፤ ለሕግ ማደር ፣ ለህሊና ማደር ፣ መንፈሳዊ መሆን በእሚባሉት የሰው ልጆች እሴቶች ላይ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ዘመቻ ማድረግ ነበረበት ።     


ማርክሲዝም ይኽንንም ለማሳካት ፤ ሳይንሳዊ መሠረት እና ተቀባይነት የሌላቸው የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅሟል ።

 

በእዚኽም የመጀመሪያው ዘዴ ፤ እንደ ማንኛውም ዶግማ (dogma) በሳይንሳዊ መንገድ ሊፈተሽ የእማይችለውን ፤ ስለ እዚኽም ፦ ሳይንሳዊ ሰአይሆን ፍልስፍናዊ የሆነውን ቁሳዊነትን (Materialism) ፤ ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት እንደ አለው ሳይንሳዊ ሐቅ የርዕዮቱ መሠረት በማድረግ ነው።


ሳይንሳዊ ነኝ ለእሚለው ማርክሲዝም ፤ ቀደም ብለን እንደ አየነው ፤ በልዕለ ተፈጥሮው ትንታኔ (Metaphysics) ፤ ቅድመ ኃሳብ ፣ እግዚአብሔር ወይንም መንፈስ የእሚባል ነገር የለም ወይንም ብቸኛው ተጨባጭ እውነታ ዐተምስ እና ባዶ ቦታ ብቻ ናቸው የእሚለውን ፤ የቁሳዊያኑ (The Materialist) ጎራ እንዲ መርጥ የእሚያስችለው ሳይንሳዊ መሠረት የሌለ ነው። 


ሆኖም ግን ፤ ምንም እንኳን በእዚኽ ዘመን በአለው የስነምግባር (Ethics) ሳይንስ እውቀት ፤ በዋናነት ኃይማኖታዊ (ኃሳባዊ The Idealist) መሠረት ወይንም ምንጭ የአላቸውን ፤ አትግደል ፣ አትስረቅ  ፣ አትዋሽ ፣ አትቀማ ፣ ወዘተ ፤ የእሚሉትን እና ፖለቲካዊ ፋይዳ የአላቸውን የስነመግባር መርህዎች ፤ በቁሳዊነት ወይንም በበኃሳባዊነት ሳይወሰኑ (Regardless of one’s metaphysical belief, as a materialist or as an idealist) ፤ ትክክል ወይንም ተመራጭ መሆናቸውን ከእላይ በወርቃማው መርህ (The Golden Rule) ምሳሌነት በአስቀመጥነው ምሳሌ ማስረገጥ የእሚቻል ቢሆንም ፤ ማርክስ ለነበረበት እና በዋናነት የስነ ምግባር መርሆዎች ምንጭ የአምላክ ፍጹም ፈቃድ ወይንም የአባቶቻችን የቀደመው ባህል በመሆኑ ፤ በእዛኽ ዘመን በነበረው የስነምግባር እውቀት ፤ ማርክስ ያለ ሳይንሳዊ ምክንያት የመረጠው ቁሳዊነት ፤ ለምሳሌ ፦ ሰውን መግደል ኢስነምግባራዊ ነው ፤ እናም አታድርገው ብሎ ሊከለክለው የእሚችል የኃሳብ መዋቅር ማምጣት የእማይቻል በመሆኑ ወይንም ማርክሲዝም የሕግ የበላይነትን ፣ የህሊና ፍርድን እና የመንፈሳዊ ተቋማትን ተጽኖ በማስወገድ ከሕግ አግባብ ውጭ ፣ በማንኛውም የህሊና ፍርድ እና የመንፈሳዊ ተቋማት ስብከት ሳይገደቡ የመደብ ትግልን ለማካኼድ ያስችለዋል። 


በአጭሩ ማርክሲዝም በቁሳዊነት ላይ የተንተራሰው ፤ ወንዞችን በደም በማጨቅየት ነው የሠራተኛው አብዮት የእሚሳካው የእሚለውን እና የፖለቲካ በአላንጣን (ይልቁንም በማርክሲዝም መሠረት የመደብ በአላንጣን) ያለርህራኼ ለማስወገድ ካለው ፍላጎት ነው። ምክንያቱም ፦ አንድ ሰው በቁሳዊው የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔን ተጠቅሞ ፤ የአለው ቁስ ብቻ ከኾነ ፤ ሰውም ከቁሶች አንዱ ስለ እሚኾን ፤ በቁሳዊነት ለእሚያምን ሰው ፤ ከስነ ምግባር አንፃር ፥ ትግሉን አሸንፈው መኖር የእሚችሉት ብርቱዎቹ ብቻ ናቸውና (Survival of the fittest) ከቻልክ እና ከአስፈለገ ወይንም ፖለቲካዊ ጥቅም የእሚሰጥህ ከሆነ ሰውን እንደ ዛፍ ብትቆርጠው ምንም ችግር የለውም ፤ ምክንያቱም በፍልስፍናቸው ፦ ሰውም እንደ ዛፉ ቁስ ስለ ኾነ ማለት የእሚችል በመሆኑ ።

 

በተቃራኒው ፤ ቅድመ ኃሳብ ፣ እግዚአብሔር ወይንም መንፈስ አለ ብሎ የእሚያምነው  ወይንም ኃሳባዊው (The Idealist or the Dualist) ፤ ሰውን መግደል ኢሰነምግባራዊ የእሚሆንበት ግዜ አለ ብሎ ለማለት የእሚያስችለው መሠረት አለው ። ለምሳሌ ፦ ሰውን መግደል ፤ ኢስነምግባራዊ የኾነበትን ምክንያት ሲያስረዳም ፦ ሰውን መግደል ኢስነምግባራዊ የአደረገው ወይንም መግደል ኢስነምግባራዊ ተግባር ነው ብሎ ያስቀመጠ እና ህሊናዬን የእሚገዛ ፤ ቅድመ ኃሳብ ፣ እግዚአብሔር ወይንም መንፈስ ስለ አለ ፤ አስፈላጊ ኾኖ ስለ አገኘኹት ወይንም ፖለቲካዊ ጥቅም እንኳን ኖሮት እና የመግደል አቅሙም ስለነበረኝ ፤ ሰውን ገድዬ እንኳን ህሊናዬ ረፍት ያጣል ፤ ሊል ይችላል ።


ህሊና የቁሱ ዓለም ነጸብራቅ እንጂ በእራሱ ህልውና የለውም የእሚለው ቁሳዊው ግን ፤ ህሊናዬ ወቀሰኝ ወይንም ከለከለኝ ማለት አይቻልም ፤ ምክንያቱም ህሊና የአከባቢዬ ነጸብራቅ እንጂ የራሱ ህልውና የለውም የእሚል በመሆኑ።


እንደ ማርክስ ያለ ፤ ለሰው ልጆች ሕይወት ግድ ሳይለው በደም አፋሳሽ አብዮት ነባራዊውን የፖለቲካ ስረዓት አውድሞ ፤ የፖለቲካ ስልጣን መያ፟ዝ አለበት ወይንም የፖለቲካ ስልጣን በእዚያኽ መልክ ብቻ ነው የእሚያዘ፟ው የእሚል ‘ተጨባጫዊ’ ፤ ከኹለቱ የቱን ዘውግ ሊመርጥ እንደ እሚችል መገመት ደግሞ ቀላል ነው ።


ይኽ ማርክሲዝም ለጸረ ስነምግባራዊነት የመረጠው ቁሳዊነት ፤ ማርክስ በተጠቀመበት አግባብ ምንም እንኳን ሳይንስ እና ፍልስፍናን የማምታት ተፋልሶ ቢሆንም ፤ በተለይ ዘመነ አመክንዮ በእሚባለው እና እ.አ.አ. 1648 – 1789 ዓ.ም. በአለው ግዜ የተጀመረው ፤ የጸረ መንፈሳዊነት እንቅስቃሴ ጋር በመዳመር ለማርክሲዝም ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ አቅም ሰጥቶታል።


ብሩስ ሼሊ የተባለ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ ፤ የዘመነ አመክንዮን መንፈስ በእዚኽ መልኩ ይገልጸዋል ፦


“የዘመነ አምክንዮ (እ.አ.አ. 1648 – 1789 ዓ.ም.) መንፈስ ፤ ሌላ ምንም ሰአይሆን የእውቀት አብዮት ነበር ፤ እግዚአብሔርን ፣ ዓለምን እና ራስን በአዲስ መልኩ የመመልከት አካኼድ ነበር። የምድራዊነት ወይንም የግዜያዊነት ውልደት ነበር። የመካከለኛው እና የተኃድሶው ዘመን የእሚባሉት ፤ አምክንዮ እምነትን የእሚያግዝበት አዕምሮ ደግሞ ለስልጣን የእሚገዛባቸው ምዕተ ዓመታት ነበሩ ... ዘመነ አመክንዮ ይኽንን ወዲያ አለው። በእምነት ቦታ አመክንዮን አደረገ። የሰው ቀዳሚ ጭንቀት መጻይው ሕይወት ሰአይሆን ፤ በእዚኽ ምድር ላይ ደስተኛ መሆን እና መሳካት ነው ፤ ስለ እዚኽም ፦ የሰው እምነቱ ሰአይሆን አዕምሮው ወደ ደስታ የእሚያደርሰው ተመራጩ መሪው ነው ፤ ስሜቱ ወይንም አንዳች ምስጢር ፣ ወይንም ዝበት ሰአይሆን ፤ አለ።”

“The spirit of the Age of Reason (1648 - 1789) was nothing less than an intellectual revolution, a whole new way of looking at God, the world, and oneself. It was the birth of secularism. The Middle ages and the Reformation were centuries of faith in the sense that reason served faith, the mind obeyed authority… The Age of Reason rejected that. In place of faith it set reason. Man’s primary concern was not the next life, but happiness and fulfillment in this world; and the mind of man, rather than faith, was the best guide to happiness, not emotions, or myths, or superstitions. [8]“


ምንም እንኳን ይኽ ዘመነ አመክንዮ የአመጣው የእውቀት አብዮት ፤ በዋናነት መነሻው የመካከለኛው ዘመን (500-1500) በእሚባለው ዘመን ፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ እያደገ የመጣው ለከት ያጣ መንፈሳዊነት ቢሆንም የዘመነ አመክንዮ አቀንቃኞች ፤ ኹሉም ሊባል በእሚችል መልኩ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች የነበሩ ናቸው። በእዛያኽን ወቅት የነበሩ መንፈሳዊያን ፤ አዕምሮን ጥለው በመንፈሳዊ አስተምህሮ እና በመንፈሳዊ መንገድ ብቻ ኑሮዋቸውን መኖር መፈለጋቸው ፤ የተፈጥሮ ስለ እዚኽም የእግዚአብሔር ስሪት እና ስጦታ የሆነውን አዕምሮዋቸውን ስለ አስጣላቸው እና ይኽም ብዙ ቀውስ ስለ አስከተለ ነበር ዘመነ አመክንዮ የጀመረው።


በእዚኽ መልኩ የጀመረውም የአመክንዮ እና የእምነት ፍልሚያ ኼዶ ኼዶ በኋላ ላይ ብዙዎችን ፤ እምነት እና አመክንዮ በቅንጅት እየሰሩ የሰውን ሕይወት የእሚያግዙ የነፍስ ስንቆች እንጂ በአላንጣዎች አይደሉም የእሚለው ፤ የብዙዎችን ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ ቢሆንም ፤ በወቅቱ የነበረው በአመክንዮ ሰም የተንጸባረቀው ጸረ መንፈሳዊነት ፤ መንፈሳዊነትን ያጠለሸበት ደረጃ ቀላል የእሚባል በአለመሆኑ ፤ ራሱን ከህሊና ወይንም ስነ ምግባራዊ ክልከላ ማላቀቅ ለእሚፈልገው ማርክሲዝም ፤ ራሱ ዶግማቲስት ሆኖ ሲያበቃ ከኃሳባዊያን (Idealists or Dualists) ጎራ የእሚመደቡትን ሕግ ፣ ህሊና እና መንፈሳዊነትን በባህላዊ ዝበት ወይንም በዶግማነት በመፈረጅ እነርሱን አስጠልቶ ራሱን ለማጽደቅ ፤ ምቹ ኹኔታን የፈጠረ ነበር።


ኃይማኖታዊ ጽንፈኝነት በአልነው ክፍል ላይ እንደ አየነው ግን ክህደተ-ዓምላክ (Atheism) እና ቁሳዊነት (Materialism) በመሠረታዊ በኃሪያቸው እንደ ኃይማኖት ኹሉ ሳይንስ ሳይኾኑ የልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ (Metaphysics) ስለ እዚኽም ፍልስፍና ናቸው ።  ይኽም ማለት ፦ በሳይንሳዊ መንገድ ተፈትሸው ይኽ ልክ ነው ፤ ይኽ ደግሞ ልክ አይደለም ሊባሉ የእማይችሉ ናቸው ። ነገር ግን ፤ ኃይማኖት አንድ ግዜ በልማዳዊነት እና በኋላቀርነት ስሙ ሲጠለሽ ፤ የእርሱ ተቃራኒ የኾኑት ነገር ግን ሳይንሳዊ ያልኾኑት ክህደተ ዓምላክ እና ቁሳዊነት ፤ ከሳይንሳዊነት ጋር በቀላሉ በመምታት ፤ መንፈሳዊነትን እንደ ጎጂ እና ኋላ ቀር ባሕላዊ አስተሳሰብ ፤ ቁሳዊነትን ደግሞ ከእዚያኽ በተቃራኒ ሳይንሳዊ አስመስለውታል ። 


ይኽ ዓይነቱ በሊኀቃን ዘንድ የእሚስተዋል ኃይማኖትን የተመለከተ ዝበታዊ እይታ ደግሞ በእዚኽ ዘመን እንኳን በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ የአለ ነው ። ለምሳሌ ፦ አንዳንድ ሊኀቃን በኃይማኖቱ ዓለም ኃሰተኛ ወይንም አታላይ የኃይማኖት አስተማሪዎች ግባቸው ፤ በኃይማኖት ስም ተከታይ ማፍራት እና ገንዘብ መሰብሰብ ነው የእሚለው ክስ ፤ በደስታ የእሚሰሙት ክስ ነው ። እነ እዚኹ ሰዎች ግን ፤ በሳይንስ ስምም ፤ ኢ-ሳይንሳዊ ኃሳብን ፥ ሳይንሳዊ በማስመሰል ፤ ደጋፊ ፣ ኃብት እና ስልጣን ፤ ለማጋበስ የእሚጠቀሙበት ሰዎች አሉ ሲባል ግን ግር እንደ እሚሰኙ በብዙ ይስተዋላል ። ይኽ ዓይነቱ አስተሳሰባዊ መፋለስ ደግሞ ፤ ተራማጅ ነን ይል በነበረው የእነ ማርክስ ዘመን አከባቢ ነዋሪ ከፍ ያለ ነበር ።


እውነታው ግን ፤ ልክ በኃይማኖት ስም የእሚነግዱ እንዳሉት ኹሉ በሳይንስ ስም የእሚነግዱ ከጥንት እስከ ዛሬ አሉ ። በኃይማኖት ስም የእሚደረግ ‘እኩይ’ ንግድን ተቃውመን ፤ በሳይንስ ስም የእሚደረግ ‘እኩይ’ ንግድ ለመቃወም አዙረን ማየት የእማንችል ከኾነ ፤ ሳይንስ ጣዖት ኾኖብናል ማለት ነው ። ዛሬም ፤ የአላገኙትን ግኝት አገኘሁ ብለው ፤ ሽልማት የእሚወስዱ ፣ የበጀት ድጎማ የእሚቀበሉ ፣ በትላልቅ ሳይንሳዊ መጽኼቶች ላይ ጽሁፋቸውን የእሚያሳትሙ ፣ ሳይንሳዊ የአልሆነ የተሰወረ ቦንብ ጠቋሚ ወይንም አነፍናፊ አንቴና አለኝ ብለው ከመንግሥታት ጋር ትልልቅ የንግድ ሽርክና የገቡ ፣ ወዘተ ፤ አጭበርባሪ ‘ሳይንቲስቶች’ እንደ አሉ ማወቅ አለብን ። አታላይ ሳይንቲስት የእሚለው ብኺል የእማይገጥም (Oxymoron ) ቢመስልም አለ ።


ይኽ መምታታት ፤ ከዳግም ስልጣኔ (Renaissance) ጀምሮ ፤ በማርክስ ዘመን እና አኹንም በአንዳንድ ምሁራን ዘንድ የእሚገኝ ስሜታዊ አመለካከት በመኾኑ ፤ ከስነምግባር ግዴታ የተላቀቀ ፖለቲካዊ ርዕዮት ለእሚፈልገው ማርክስ ፤ የስነምግባር አሳሳቢ የኾኑ ተቋማትን እንደ ኋላ ቀር እና ጎጂ ወግ አጥባቂያን መፈረጃ እና ከተከታዩ እሳቤ ውስጥ ማስወጫ አቅም ኾኖለታል ።


ከእዚኽም ተነስተን ፤ ማርክሲዝም የጸረ ስነምግባር አካኼዱን ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ፤ ፍልስናን ከሳይንስ ጋር በማምታት ፤ የፍልስፍና ዘውግ የሆነውን ቁሳዊነትን እንደ ሳይንሳዊ አድርጎ በማቅረብ እና በእዛኽ ዘመን እና እስከ ዛሬም በኃይማኖት ተቋማት ላይ የአለውን የሊህቃን ትችት እንደ እድል በመጠቀም ፤ የፍልስፍናውን ህሊናቢስነት ወይንም ጸረ ስነምግባራዊነት ፤ በአደባባይ ያለ እፍረት እንዲያራምድ አስችሎታል።

ደጋግመን እንደ አልነው ይኽን የእሚያደርገው ደግሞ ፤ የተፈጥሮ ሕግ ነው በእሚለው የመደብ ትግል መርህ መሠረት ፤ ማርክሲስቶች የመደብ ጠላታቸውን ያለ ምንም ሕሊናዊ ክልከላ የማጥፋቱን አብዮት እንዲያካኼዱ ነው።


ከእዚኽም የተነሳ ወይንም በአለው ጽነሰ ኃሳባዊ ጥራት ሰአይሆን ለማርክሲዝም ስኬት መሠረት የሆነ ህሊናቢስነት ወይንም ጸረ ስነምግባራዊ ማስፋፋት ስለ እሚፈልግ ስለሆነ የርዕዮቱ አንኳር የሆኑ ኃሳቦችን የእሚመርጠው ፤ የማርክሲዝም ፍልፍና እርስ በእርሳቸው የእሚቃረኑ ኃሳቦች የተሞላ ነው።


ለምሳሌ ፦ ማርክስ የስነ ዕውቀት ፍልስፍናውን ፤ ያለ ሳይንሳዊ መሠረት ፤ በቁሳዊነት ላይ እንዲ ደገፍ በማድረጉ ፤ ፍልስፍናዊ ምክንያቶች  ፤ የስነ እውቀት መላምቱን ፤ በእዚኽ የቁሳዊነት ምርጫው ላይ ሙሉ ለሙሉ እንዲያስደግፍ እና በታቃርኖ የተሞላ እንዲሆን ግድ ይለዋል ።


ፍልስፍናን እንደ አንድ ራሱን የቻለ የጥናት መስክ የተመለከትን እንደኾነ ፤ በውስጡ ሦሥት ዋና ዋና ንዑስ ክፍሎች ይዞ እናገኘዋለን ፦

    የልዕለ-ተፈጥሮ ትንታኔ (Metaphysics)

    የስነ-እውቀት ተመራምሮ (Epistemology)

    የስነ-ምግባር ተመራምሮ (Ethics)


እነ እዚኽ ሦሥት ንዑስ መስኮች በቅደም ተከተል ፤ አንደኛው፦ ይኽ የእምናየው ዓለም ፥ ሰውን ጨምሮ ከየት መጣ የእሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የእሚታትር ሲኾን ፣ ኹለተኛው፦ ደግሞ የሰው ልጅ እውቀት የማግኘት አቅሙን ከየት አገኘው እንዲኹም እውቀትስ እንዴት ነው የእሚያገኘው የእሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የእሚሞክር ሲኾን ፣ ሦሥተኛው ፦ ትክክል እና ትክክል ያልኾኑ የሰው ምግባሮች የእምንመዝንባቸው መመዘኛዎች ምንድናቸው የእሚለቱን ጥያቄዎች ለመመለስ የእሚሞክር ነው ። 


እነ እዚኽ ሦሥት መስኮች እርስ በእርሳቸው በጣም የተዛመዱ እና ለአንዱ የእሚሰጠው መልስ ለሌኛው የእሚሰጠውን መልስ የእሚወስን በመኾኑ ፤ ሙሉ በሙሉ እያንዳንዳቸውን በተናጠል (Exclusively) ማየት ያስቸግራል ። 


ከላይ በአስቀመጥነው አግባብ ፤ በልዕለ ተፈጥሮው ( Metaphysics ) መስክ ፤ በቁሳዊነት ላይ ብቻ ለመመርኮዝ የእማያስችሉ ብዙ ሳይንሳዊ ዕክሎች ቢኖሩም  ፥ ማርክስ ፤ የተጨባጫዊነትን ድክመት ለመሸፈን ከአለው ፖለቲካዊ ምክንያት የተነሳ ቁሳዊነትን እንደ መረጠው ፤  በስነ እውቀት መስኩም ፥ በይዘቱ አዲስ ያልኾነ (እርሱ ግን አዲስ አስመስሎ ያቀረበው) እና ሳይንሳዊ ባይኾን እንኳን  ፤ የሰዎች ግንዛቤ መሠረቱ የእሚኖሩበት ቁሳዊ ከባቢ ብቻ እና ብቻ ነው የእሚለውን ድምዳሜ ለማስቀመጥ አስገድዶታል ወይንም አስችሎታል ። 


ምክንያቱም ፦ በልዕለ ተፈጥሮው ትንታኔ ፤ ቁስ ብቻ ነው የአለው ፤ ሌላ ምንም ነገር የለም ያለ ሰው ፤ ከቁስ ውጭ ወይንም ቁሳዊ መሠረት የሌላቸው ኃሳቦች አሉ ሊል አይችልም ። ምንም እንኳን ሰው ፤ ለምሳሌ ፦ በአካል አይቶ የእማያውቃቸውን ክንፍ የአለው ፈረሰ (Pegasus) መሳል እንደ እሚችል ወይንም ቁሳዊ መሠረት የሌላቸው መልካም እና መጥፎ የእሚሉ ክፍፍሎች ወይንም የፍጽምና (Perfection) ኃሳብ ወይንም የቁጥሮች እሳቤ ሊኖረው እንደ እሚችል ቢገነዘብም።

 

በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት ፤ የቶማስ ሆብስ እና የጆን ሎክ ፤ ኃሳቦች የተመለከትን እንደኾን ፤ እውቀት ከከባቢ እንደ እሚመነጭ ቢስማሙም ፤ ከባቢ ብቻ የእውቀት ምንጭ እንደ አልኾነም አስቀምጠዋል ። በእዚኽም መሠረት ከከባቢያችን የተቀበልነውን መረጃ ፤ ድፍድፉን ፤ በማሰላሰል ፤ ወደ ተለያየ የግንዛቤ ደረጃ እንደ እምናደርስው አስቀምጠዋል ።


 እንደ እዛኽ ባይኾን ፤ በአንድ ዓይነት ከባቢያዊ ኹኔታ ውስጥ ያለ ሰው ኹሉ አንድ ዓይነት እውቀት ይኖረው ነበር ፤ እውነታው ግን ተመሳሳይ መንታዎች እንኳን ተመሳሳይ ግንዛቤ ወይንም እውቀት የላቸውም ። 


የካርል ማርክስ የሙግት ቁሳዊነትንም ፅንፈኛ ስሁትነትም ፤ ለፖለቲካዊ ግቡ ሲል የመረጠው ድርቅ ቁሳዊነት ፥ በፍልስፍናው መስክ በእሚያሳርፍበት አስገዳጅነት ፤ ይኽ በማሰላሰል የእሚገኘውን እውቀት በመካድ ፤ ተቀጥሮ የእሚሰራ ሰው ፤ እንደ እርሱው ተቀጥሮ ከእሚሰራው ሰው የተለየ ግንዛቤ ሊኖረው አይችልም ፤ ምክንያቱም ፦ ግንዛቤ ከቁሳዊ ኹኔታ ብቻ ነው የእሚመነጨው የእሚሉ ስኹት ድምዳሜዎችን የእሚያስከትለውን የሙግት ቁሳዊነት (Dialectical Materialism) እንዲ መርጥ ግድ ብሎታል ። 


ይኽ ደግሞ ግለሰባዊ ልዩነቶችን አጥፍቶ የሰውን ግንዛቤ በቁሳዊ መደብ የእሚወስን ይኾናል ። ያም ማለት ፤ ለምሳሌ ፦ በባለአባት መደብ ውስጥ ያለ ፤ እንደ ባለአባት ብቻ ነው የእሚያስበው ፤ በጭሰኛ መደብ ውስጥ ያለ እንደ ጭሰኛ ነው የእሚያስበው ማለት ነው ። 


ይኽ መላምት ግን ፤ ተግባራዊ እና ሳይንሳዊ መሠረት እንደ ሌለው ብዙ ርቀት ሳንኼድ ፤ ከላይ እንደ አልነው በአብዛኛው የማርክስን መርኽ ይዘው የከምኒዝም ን አብዮት ያቀጣጠሉና እና የመሩ ሰዎች ፤ በቁስ መደባቸው ቡርዥዋ ወይንም በአላባት የኾኑ ቤተሰብ ውስጥ ተወልደው ያደጉ የነበሩ ሲኾን ፤ አብዮቱን ያስነሱት በራሳቸው ‘መደብ’ አባላት ላይ  ፤ ከማርክስ አስተምኽሮ ፍፁም በተቃራኒ መኾኑ ነው ። 


ማርክሲዝም በእዚኽ መልኩ ፤ በፍልስፍናዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ፕሮፖጋንዳዊ ፋይዳው ምክንያት ፤ ሳይንስን ከፍልስፍና እየ አምታታ ፣ ኢሳይንሳዊ እና ጸረ ሳይንስ እየሆነ ፤ በጨፍን ሆን ብሎ የእሚጓዘው  ፤ ራሱን ከላይ በተቀመጠው አግባብ እንደ እማይሻር እና የእማይለወጥ የተፈጥሮ ሕግ አድርጎ በማቅረብ ፤ ከእርሱ አስተሳሰብ ውጭ የአለውን ፤ ፖለቲካዊ ፣ ኢከነሚያዊ ፣ ማሕበራዊ ፣ ወዘተ ፤ አስተሳሰብ እና መዋቅር ፤ ማጥፋት አብዮታዊ (ተፈጥሮዋዊ) ግዴታችን ነው በእሚል ፥  ያለምንም የህሊና እና የስነ ምግባር ክልከላ ፤ ከማርክሲዝም ውጭ ያሉ የፖለቲካ ርዕዮቶችን በሙሉ ለማጠፋት ነው። 


ይኽም የማርክሲዝም በኃሪ ፤ ከሳይንሳዊ መመዘኛ ውጭ ስነ ምግባርን እንደ መጥፎ የቆጠረ ፖለቲካዊ ርዕዮት በመሆን ፤ እስከ ዛሬ በዓለም ሕዝብ ታሪክ ከታየው አምባገነናዊ ስረዓት ኹሉ በላይ ፍፁም አምባገነን እና የፖለቲካ ፅንፈኝነት ጥግ ተምሳሌት የኾነ ፖለቲካዊ ርዕዮት እንዲሆን አድርጎታል ።


5.    ጠንሳሾቹን ጨምሮ ተግባሪዎቹ ፤ ለሳይንሳዊነቱ ሰአይሆን ለእሚያስገኘው ስልጣን ነው ቅድሚያ የእሚሰጡት


ይኽ በመኾኑም ወይንም ማርክሲዝም ከላይ የዘረዘርናቸውን ባሕሪያት በመላበሱ ፤  ለመጀመሪያ ግዜ በማርክሲዝም አስተሳሰብ መሪነት የፖለቲካ ስልጣን የያዘው ሌኒን ፤ ከማርክሲዝም ውጭ ሌላው ኹሉ የተሳሳተና መጥፋት የአለበት ነው ፤ ይኽንም ማድረግ የእሚቻለው ፍፁማዊ የኾነ የፖለቲካ ስልጣን በመያዝ ነው የእሚሉትን ፤ የማርክሲዝም አስተሳሰቦች መመሪያ በማድረግ ፤ ታሪክ የማርክስን ትንታኔ አልመስል ሲል ታሪክን በኃይል ከማርክስ ቲየሪ ጋር ለማስተካከል የተደረገ የመጀመሪያው እና ወሳኙ ክስተት ኾኗል  ።

ሌኒንዝም ፣ ስታሊንዝም በኋላም ማዖይዝም ማለት ፤ ሕዝብ በእሚኖሩበት በማንኛውም ማሕበረሰብ ውስጥ ፤ ማናቸውንም ዓይነት የቅራኔ ምንጮችን እየፈለጉ ፤ በእዚኽ ቅራኔ መሠረት ሰዎችን ፤ ለእርስ በእርስ ጦርነት ፣  ለሽብር ፣ ለመሰዋትነት ፣ ወዘተ ፤ በማነሳሳት ፤ መንግሥትን በኃይል ገልብጦ ፤ ፍፁማዊ የኾነ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ እና በማርክስ የታሪክ ቁሳዊነት መሠረት አምስተኛው ደረጃ ላይ የአለውን ሶሻሊዝም በጉልበት ማምጣት ይቻላል ማለት ነው ።


ስለ እዚኽ ፦ ሌኒንዝም ፣ ስታሊንዝም ፣ ማዖዚም ፤ በኃይል የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ እና ሌሎች ፖለቲካዊ ተቃዋሚዎችን ለመደምሰስ  ፦ የእርስ በእርስ ጦርነት ማስነሻ ፣ የሽብር ፣ የሽምቅ ውጊያ ማቀጣጠያ ፣ አማክሎ የመጠርነፊያ ፣  ወዘተ ፤ መመሪያ ናቸው ። 


በእዚኽ መልክ የፖለቲካ ስልጣን ከጨበጡ በኋላ ፤ የእየ ሐገራቱ ፖለቲካ ፣ ታሪክ እና ኢከነሚ ኢሳይንሳዊ የኾነው ማርክሲዝምን ቲየሪ እንዲ መስል ይሰራሉ ወይንም ማርክሲዝም መመሪያችን  ነው ይላሉ ።

አንዳንድ የማርክሲዝም አልሞት ባዮች ፤ እንደ እሚመስላቸው ወይንም እንደ እሚሉት ፤ የማርክስ ፍልስፍና በእነ ሌኒን እና ስታሊን መሰል ፤ በአብዮት ስም የፓርቲ ፖለቲካ በማካኼድ ስለ አበላሹት እንጂ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በመቶ ሚልየን ለእሚገመት ሕዝብ የእልቂት ምክንያት የኾነው ፤ በማርክስ መሠረት አብዮቱ በካፒታሊስት ስረዓት ውስጥ ብቻ በተበዘበዘው ሠራተኛ አመፅ ቢካኼድ ኖሮ ይኽ አይኾንም ነበር ፤ ወይንም ፥ የማርክስ ቲየሪ ልክ ነበር ፤ ቸኩለው በአልዳበረ ማሕበረሰብ ውስጥ ስለ አካኼዱት ነው የተበላሸው ሊሉ ይፈልጋሉ ።


እውነታው ግን ፤ እነርሱ ለማርክስ ቲየሪ ሳይንሳዊነት የእሚጨነቁትን ያኽል ማርክስ ራሱ ለራሱ ቲየሪ ሳይንሳዊነት አይጨነቅም ። በእርሱ ኢሳይንሳዊ ቲየሪ ይኹን በሌላ ፤ የከምኒስት ፓርቲ ስልጣን ከያዘ ማርክስ ዓላማውን እንደ አሳካ ነበር የእሚቆጥረው ወይንም ማርክስ ኹል ግዜ ግቡ የፖለቲካ ስልጣኑ ነበር ። 

የማርክስ ዓላማ ማሕበራዊ ለውጥ አልነበረም ፤ የፖለቲካ ርዕዮት ጓደኞቹን ስልጣን እንዲይዙ ማድረግ ነው ፤ ከእዚኽ ያነሰም ኾነ የበለጠ ዓላማ አልነበረውም ። 


ካርል ማርክስ ፤ ልክ እንደ ሌኒን እና ማዖ ፤ የከምኒስት ፓርቲ ፤ ቅራኔ እየፈለገ በአገኘው አጋጣሚ ግጭት ይፍጠር ፣ ሠራተኛ ያሳምፅ ፣ ወዘተ ፤ ሲል የነበረ እና ሰራተኞች ራሳቸው ጥያቄያችን ተመልሷል እና አመጽ አቁመናል ሲሉ በእነርሱ ላይ ይነሳ የነበረ ነው ፦


“ከምኒስቶች (ፓርቲው) ግዜያዊ ዓላማ ለማሳካት ፣ ወቅታዊ የኾነውን የሠራተኛውን ጥቅም ለማስጠበቅ መታገል አለባቸው ፤ በተጓዳኝም ግን የንቅናቄውን መፃኢ መንከባከብ አለባቸው ።  ... በፖላንድ ፤ እ.አ.አ. በ1846 ዓ.ም. የክራኮው አመፅን ያነሳሳውን እና የግብርና አብዮት ለብሔራዊ ነፃነት አስፈላጊ ነው የአለውን መደገፍ አለባቸው … በአጭሩ ፤ ከምኒስቶች በየትኛውም ስፍራ ፤ ነባራዊውን ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ ስረዓት ላይ የእሚያምፅ ማንኛውንም አብዮታዊ እንቅስቃሴ መደገፍ አለባቸው ።”

“The Communists (party) fight for the attainment of the immediate aims, for the enforcement of the momentary interests of the working class; but in the movement of the present, they also represent and take care of the future of the movement. ... In Poland, they support the party that insists on an agrarian revolution as the prime condition for national emancipation; that party which fomented the insurrection of Cracow in 1848. ... In short, the Communists everywhere support every revolutionary movement against the existing social and political order of things. [18]“


ይኽን መሰሉን ፤ በካርል ማርክስ በከምኒስት ማንፌስቶ ላይ የተቀመጠ ግልፅ የኾነ ፤ በተገኘው አጋጣሚ ኹሉ ቅራኔን እየፈለጉ ጠብ የማነሳሳት ውትወታ ወይንም ዝብዘባ ፤ የተመለከተ ሰው ፤ ማርክስ ሶሻሊስቱ ወይንም ከምኒስቱ አብዮተኛ ልክ በካፒታሊስቱ ስረዓት ውስጥ ይመጣል እንዳለው አብዮት ፤ ከካፒታሊስቱ በፊት ባለው የፊውዳሉ ስረዓት ውስጥ ገበሬውን አሳምፆ ከምኒስቱ/ሶሻሊስቱ ስልጣን ቢይዝ አሜን ብሎ የእሚቀበለው መኾኑን የእሚያሳይ ነው ። 


ይኽም ማለት ደግሞ ፤ ፍጹም የእማይሻር የተፈጥሮ ሕግ ነው የእሚለውን የታሪክ ቁሳዊነቱ ደረጃ ተጥሶ ፤ ከፊውዳሊዝም ቀጥታ ወደ ሶሻሊዝም ቢገባ ማርክስ ግድ አይለውም ነበር ማለት ነው ወይንም እርስ በእርሱ የእሚቃረን መላምት ያራምድ ነበር ማለት ነው ።


ጀርመን አይዲዮሎጂ በእሚለው መጽሐፍ ላይ እንዲያውም ፤ የሶሻሊስት አብዮት በዳበረ ካፒታሊስት ኢከነሚ በአላቸው ሐገራት ውስጥ ከጀመረ ፤ በዓለም ዓቀፋዊ ትስስር አማካኝነት የአልዳበረ ኢከነሚ በአላቸው ሐገራት ውስጥ እንደ እሚዛመት እና ይኽም ተገቢ እንደ ሆነ ሲሞግት ይገኛል ፦


“በአንድ ሐገር ውስጥ ተቃርኖው ወደ ለየለት ግጭት እንዲያመራ ተቃርኖው ወደ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ የለበትም። በዓለም ዓቀፋዊ ግንኙነት አማካኝነት ፤ በኢንደስትሪ ያልዳበሩ ሐገራት በኢንደስትሪ ከዳበሩት ሐገራት በእሚያደርጉት ፉክክር ፤ ተቃርኖውን ለማምጣት በቂ ነው።”

“Incidentally, to lead to collisions in a country, this contradiction need not necessarily have reached its extreme limit in that particular country. The competition with industrially more advanced countries, brought about by the expansion of international intercourse, is sufficient to produce a similar contradiction in countries with a less advanced industry. [15]”


ይኽም ቦልሼቪዝም ኾነ ማዖይዝም ፤ የማርክስን ምክር ከተለያየው ከእየ ሐገራቸው ኹኔታ ጋር ለማጣጣም በአደረጉት አካኼድ ይለያዩ ይኾናል እንጂ በይዘት ደረጃ ፤ የካርል ማርክስን ምክር ቃል በቃል እንደተገበሩት ግልፅ ያደርጋል ።


ስለ እዚኽ ቦልሼቭዝም እና ማዖይዝም በመቶ ሚልየን ሕዝብ ከጨፈጨፉ ፤ ማርክሲዝም አድርጉ ስለ አላቸው ነው ። ማርክሲዝም ከማዖዝም ወይንም ከቦልሼቭዚም ጋር ከተለያየ ፤ የተለያየው ፥ ማርክስዝም  ራሱ ኢሳይንሳዊ የኾነ (የሙግት ቁሳዊነት እና የታሪክ ቁሳዊነት) የእሚባል ትንታኔ እና በየትኛውም የማሕበራዊ እድገት ደረጃ ላይ በእሚገኝ ማሕበረሰብ ውስጥ ፤ ደም እንደ ጎርፍ አፍስሰህም ፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ አስነስተኽም ፣ ወዘተ ፤ ብቻ በቻልኸው መንገድ ስልጣን ያዝ የእሚል እርስ በእርሱ የእሚጣላ መርህ ስለ አለው ነው ። 


ማርክስም ፣ ሌኒንም ፣ ስታሊንም ፣ ማዖም የአንድ ወንዝ ፖለቲከኞች ናቸው ። በከምኒዝም  ፅንሰ ኃሳብ ኾነ በአተገባበሩ ላይ አንድ ዓይነት የጋራ ግንዛቤ ነው የአላቸው ።


ይኽም በመሆኑ ፤ የማርክሲዝም ርዕዮት መሠረታዊ የሆነ የስልጣን ጥመኝነት ላይ የተመሠረተ ፍልስፍና ፤ የማርክስ ሳይንሳዊ ትንታኔ በሙሉ ከማርክሲዝም ውጭ የአለውን ማንኛውንም ስረዓት በመቃረን የቆመ በመሆኑ ፤ ማርክሲዝም እንቶ ፈንቶ እንጂ ሳይንሳዊ መሠረት እንደ ሊለው ፤ ሌላው ማሳያ ነው። 


6.    ይኽን መሰሉ ማርክሲዝም ፤ በተግባር የዓለም ሕዝብ ሰቆቃ ምንጭ ሆኖ ነበር 


ከምኒስቶች ዓላማችን ሕዝባዊነት ነው ቢሉም እንኳን ፤ ይኽ የከምኒዝም ኢሳይንሳዊነት ፤ የተጨባጫዊነት ጭካኔ እና ሴራ ከለላ እንጂ እውነተኛ ሳይንሳዊ ለመኾን የተደረገ ስህተት እንደ አልኾነ ፤ በከምኒስቶች የተፈፀሙ ብዙ ታሪካዊ መንጀሎች እና በደሎች ምስክሮች ናቸው ።


ከምኒስቶች ፤ ማንኛውንም ማሕበርሰባዊ ሰቆቃ ወይንም አደጋ ፤ ጥቂት የፓርቲ አባላት ፤ ለስልጣን እንዲያበቃቸው ፤ ሕዝብን ለማሳመፅ ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስነሳት ፣ ራሳቸውን ለማጠናከር ፣ ወዘተ ፤ እንደ እሚጠቀሙበት የታወቀ ነው ። 


ሌኒን የሐገሩ ሕዝብ በርሐብ በእሚያልቅበት ወቅት ፤ ይኽን ርሐብ ሰበብ አድርገን ፤ ፓርቲያችንን በገንዘብ ለማጠናከር ገዳማትን መዝረፍ አለብን ሲል ነበር ፦


“…እነ እዚኽ ከመራባቸው የተነሳ እርስ በእርስ መበላላት በጀመሩ እና በሚልዮኖች እየሞቱ በመላ ሐገሪቱ በእየ መንገድ ዳሩ እየወደቁ ባሉ ሕዝብ ታግዘን ፤ ማሰባሰብ የእምንችለውን የጨከነ ኃይል ኹሉ ተጠቅመን የቤተክርስቲያንን ኃብት መውረስ የእምንችለው አኹን እና አኹን ብቻ ነው … ስለ እዚኽም ፦ በመቶ ሚልዮን ሩብልስ የእሚቆጠረውን ይኽን ኃብት ማጋበስ አለብን (አንዳንዶቹ እነ እዚኽ ገዳማት ምን ያኽል ኃብታም እንደ ኾኑ አስቡ!) ። በእዚኽ ደረጃ የናጠጠ ግምጃ ቤት (ገንዘብ ቤት) ሳይኖረን ፤ የትኛውም መንግሥታዊ ፕሮጀክት ፣  ኢከነሚያዊ ፕሮጀክት እናም አኹን የያዝነውን ቦታ ማጠናከር የእሚባል ነገር የእማይታሰብ ነው ። ምንም ዓይነት ዋጋ ቢያስከፍለንም ፤ እነ እዚኽን ሚልዮኖች (እንዲያውም ቢልዮኖች) ሩብልች በእጃችን ማስገባት አለብን ።”

“…with the help of all these starving people who are starting to eat each other, who are dying by the millions, and whose bodies liter the roadsides all over the country, it is now and only now that we can – and therefore must, confiscate all church property with the ruthless energy we can still muster….we must therefore amass a treasure of hundreds of millions of gold rubles (think how rich some of these monasteries are!). Without treasure on that scale, no state projects, no economic projects, and no shoring up of our present position is conceivable. No matter what the cost, we must have those hundreds of millions (or even billions) of rubles [23].”


በርኃብ በእየ መንገዱ የእሚወድቅን ሕዝብ አስተባብረን ፤ ለፓርቲያችን ሥራ ማጠናከሪያ ገንዘብ እንድ እናገኝ ገዳማትን እንዝረፍ የእሚሉ ናቸው እነ ሌኒን!   


የእነ ሌኒን ዘረፋ እና ማስገደድ ፤ የመደብ ጠላታችን በእሚሉዋቸው መነኮሳት እና ገዳማት ላይ ብቻም የተወሰነ አይደለም ። ታገልንልህ ፤ አብዮቱን ለአንተ አደረግነው የእሚሉትን ገበሬ ፤ በሶሻሊዝም መርኽ መሠረት ምርትኽን በሙሉ ለመንግሥት አስረክብ እና መንግሥት በራሽን ለመላው ሕዝብ (እውነታው ለፓርቲ አባሎቻቸው) ያከፋፍለዋል ሲሉት እንቢ ስለ አላቸው ፤ በወታደራዊ ኃይል በእየቤቱ እየገቡ ጎተራውን ማራገፍ ብቻ ሰአይኾን ፤ በላቤ የአመረትኹትን እኽል ለመንግሥት አላስረክብም ስለ አለ ፤ የአብዮቱ ጠላት ተብሎ ትዕዛዝ ወጥቶበታል ። 


ከእዚኽ በታች የአለው ፤ በገበሬ ማሕበር ታቅፌ ምርቴን ለቦልሼቭኩ አላስረክብም ባለው ገበሬ ላይ ሌኒን ያወጣው ትዕዛዝ ነው ፦


“የጥቃቅን እርሻ ባለቤቶች ፥ ከሠራተኛው ጎን ተሰልፈው ካፒታሊስቱን እና ትልልቅ እርሻ በአለቤቶችን ለማስወገድ በተደረገው ትግል ተሳትፈዋል ። አኹን ግን መንገዳችን ተለያይቷል ። እነ እዚኽ የጥቃቅን እርሻ በአለቤቶች ፤ መደራጀት እና በስርዓት ቁጥጥር ስር መኾንን ኹል ግዜ እንደፈሩ ነው ። ምንም ዓይነት ምህረት ሳናሳይ በእነርሱ ላይ ለመዝመት አኹን ግዜው ነው ።” 

 “The smallholders, the people who owned only a parcel of land, fought side by side with proletrait when the time come to overthrow the capitalists and the major land owners. BUT NOW our paths have diverged. Smallholders have always been afraid of discipline and organizatiom. The time has come for us to have no mercy, and to turn against them. [23]“


ይኽም ገበሬውን ፤ ጉልበትህ እና ምርትህን በመንግሥታዊ ወይንም ሶሻሊስታዊ አስተዳደር ስር አድርግ ብሎ የማስገደድ ኺደት ፤ በሌኒን ዘመን ባልጠነከረው ፓርቲያቸው ላይ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ አስነስቶ ለግዜው ከከሸፈ በኋላ ፤ በዘመነ ስታሊን ሲተገበር ፤ በራሺያ ብቻ ወደ 6 ሚልየን የእሚጠጉ ገበሬዎችን ሕይወት የቀጠፈ ነበር ፦


“… በገጠሩ ክፍል በግዳጅ ምርትን እና እርሻን በጋራ (በመንግሥት ወይንም ሶሻሊስት አስተዳደር ስር ማድረግ) ፤ በትንናንሽ እርሻ ባለቤት የገበሬዎች ሕዝብ ላይ በሶቭየቶች የተካኼደ ጦርነት ነበር ። እ.አ.አ. በ1930/31 ዓ.ም. ከኹለት ሚልዮን በላዮቻቸው ተፈናቅለው ነበር … ስድስት ሚልዮኖቹ በረኃብ ሞተዋል ፤ በመፈናቀላቸው ቀጥተኛ ምክንያትነት በመቶ ሺዎች የእሚቆጠሩ ሞተዋል ።”


 “…forced collectivization of countryside was in effect a war declared by the soviet state on a nation of SMALLHOLDERS. More than 2 million peasants were deported, 1930-31….6 million died of hunger, hundreds of thousands died as a direct result of deportation. [23]“


በአጠቃላይ ፤ ምንም እንኳን ከምኒዝም ፤ በመደብ ግጭት መርህ ማሕበርሰብ ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም ፤ ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም ይገባል ፤ በእዚኽም ኺደት ጥቂቶች የኾኑ በዝባዥዎች ከስልጣን ሲወገዱ ሰፊው ሕዝብ ፣ ሠራተኛው ወይንም ገበሬው የስልጣን ባለቤት ይኾናል ቢልም ፤ አንዱም የከምኒዝም አብዮት በእዚኽ አግባብ ያልተካኼደ እና ከአብዮቱም በኋላ ፤ ጥቂት የከምኒስት ባለስልጣናት ከየተኛውም አምባገነነን ስረዓት በላይ በሐገር ኃብት ላይ እንደ ግል ንብረታቸው የእሚያዙ እና በዜጎች ሕይወት ላይ እንደ አሰኛቸው የእሚወስኑ ልዩ ዓይነት አምባገነናዊ ስረዓት በመሆናቸው ፤ ሰፊው ሕዝብ ፤ ገበሬው ወይንም ሠራተኛው የፖለቲካ ስልጣን በአለቤት ሊኾን ይቅርና በአግባቡም እንደ ዜጋ አልኖረም ። 


ከምኒስቶች ፤ በሳይንስም ኾነ በተግባር ጥቂት ሰዎች የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ ከአላቸው ጉግት ውጭ ለሰፊው ሕዝብ ምንም ፋይዳ ባይኖራቸውም ፤ ለስልጣን በእሚንቀሳቀሱበት ግዜ ለጭካኔያቸው ወደር አልነበረውም ፦


 “አብዮት የእሚሳካው ወንዞች በሰው ደም ቀለማቸው ወደ ቀይነት ሲለወጥ ነው። የሰውን ዘር ፍፁም ለማድረግ የእሚፈለግ ከኾነ ደም መፍሰስ አለበት።”

“Revolutions succeed only when rivers run red with blood, and blood has to be spilled if what you are aiming for is the PERFECTABILITY of HUMAN RACE [23]“


የእሚሉ ናቸው ። ከምኒስቶች ፤ አንዳንድ ግዜ ፤ ይኽ ወደር የለሽ እና ከአንደኛው እና የኹለተኛው የዓለም ጦርነት በላይ በ100 ሚልየን የእሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ጭካኔያቸው ፤ የተሻለ ዓለም ለመፍጠር የተከፈለ ፤ አሳዛኝ ቢኾንም የግድ እና አስፈላጊ የኾነ ዋጋ እንደኾነ ሊሉ ይፈልጋሉ ፦


“… ብዝኃኑ የትላንቶቹ የደሞዝ ባሪያዎች በጥቂቶቹ በዝባዦች ላይ የእሚያደርጉት ጭቆና ፤ በተነፃፃሪነት የባሮች ፣ የጭሰኞች እና የምንደኞችን አመፅ ለማስቆም ከእሚደረገው ጭቆና ያነሰ ደም አፋሳሽ በመኾኑ ፤ የሰውን ልጅ የእሚያስከፍለው ዋጋ ትንሽ ነው ።”

“… for the suppression of the minority of exploiters by the majority of the wage slaves of yesterday is comparatively so easy, simple and natural a task that it will entail far less bloodshed than the suppression of the rising of slaves, serfs or wage-laborers, and it will cost mankind far less. [29]“


ይኽን መሰሉን ድፍረት እና ኢሰባዊነት የተሞላበት ድምዳሜያቸውን እንኳን እንደ አንቀበል ፤ ይኽን መሰሉ ደም አፋሳሽ ጭቆና ቁጥሩ ለእማይታወቅ አመት የሚቆይ ነው ይላሉ ፦


“በምን ዓይነት ፍጥነት እና በየትኛው ቅደም ተከተል እንደኾነ አናውቅም …”

“We do not know how quickly and in what succession, [29]“


ሌኒን ፤ ይኽን ፍጥነቱን እና ቅደም ተከተሉን አናውቀውም የእሚለው ጉዳይ ሌላ ሰአይኾን ፤ ወንዞችን በደም የእሚያጨቀየው የሠራተኛውን አምባገነን መንግሥት ወይንም ከላይ የአለውን ፤ ‘ብዙኃን’ ‘አናሳውን’ የእሚጨቁኑበት መንግሥት በስልጣን ላይ ቆይቶ ማሕበረሰብ ከሠራተኛው አምባገነንነት መንግሥት ወደ መንግሥት አልባ ፣ ሐገር አልባ ፣ መደብ አልባ ፣ ወዘተ ፤ ከምኒስታዊ ምድረገነት የእሚሸጋገርበትን አግባቡ ሲያስረዳ ነው ።


እንዲኽ እያሉ ነው እንግዲኽ ፤ ማርክሲስቶች ገደብ የለሽ ጭካኔያቸውን ፤ ያለ ህሊናዊ ክልከላ የእሚያካኺዱት ።

ስለ እዚኽ ፤ ማርክሲዝም የተምታታበት ፣ ኢሳይንሳዊ እና ጸረ ሳይንስ የሆነ ፤ ከእዛኽ ኹሉ በላይ ከጅማሮው አንስቶ እስከ ፍጻሜው በጭካኔው እና በጸረ ሕዝብነቱ የእሚታወቅ ነው ።


ማርክስ እድሜ ገድቦት ፤ የከምኒዝም አብዮት ተካኺዶ የፖለቲካ ስልጣን በያዘበት ወቅት ባይኖም ፤ ማርክሲስቶች ተግባራቸው ኹሉ ፤ እንደ ኃይማኖት መጽሐፍ ከእሚጠቅሱዋቸው የማርክስ ጋዜጣ ላይ የተጻፉ አምዶች ፣ ተበታኝ ወረቀቶች እና መጽኃፍት የተሰበሰቡ በመኾናቸው ፤ ማርክሲስቶች ፤ ማርክስን ራሱን ጨምሮ ፤ ኢሳይንሳዊ እና ጸረ ሳይንሳዊ ፍልስፍናቸውን ይዘው ይኽን ያኽል ትልቅ ፖለቲካዊ ተቋም ገንብተው ፤ ከላይ የጠቀስናቸውን ፖለቲካዊ እና ሰብዓዊ ወንጀሎች የእሚፈፅሙበት ታክቲክ የእሚከተለውን ይመስላል ።

መጀመሪያ ፤ ከላይ እንደ አልነው የማርክሲዝም ኹለት አዕማድ የኾኑት የሙግት ቁሳዊነት እና የታሪክ ቁሳዊነት ፤ መሠረታዊ የኾነ የሳይንሳዊነት ችግር ስለ አለባቸው ፤ በማርክሲዝም ሳይንሳዊ መላምቶች ላይ ትችት የእሚሰነዝሩ ምኹራንን በሙሉ ይሸሻሉ ። ይኽ ማርክስን ጨምሮ የኹሉም የከምኒስት ሊህቃን አካኼድ ነው ።

የኋለኛው ከውሚውንስት ኢንተርናሽናል መነሻ የኾነው የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ የሰራተኞች ማሕበር የእሚባለው ተቋም ውስጥ ካርል ማርክስ ፤ በወቅቱ የነበሩት ሙህራን በሙሉ ፤ ፍልስፍናው እንደ እማይሰራ ሲነግሩት ፤ እነርሱን ተከራክሮ በኃሳብ ማሸነፍ ስለ አቃተው ፤ የአደረገው ነገር ቢኖር ፤ ራሱን መሥራች አባል ከነበረበት ተቋም ገንጥሎ በማውጣት ፤ ኹለተኛው ዓለም ዓቀፍ የሰራተኞች ማሕበር የእሚባለውን ድርጅት ወደ ማቋቋም ነው የገባው ።

 

አብረውት የነበሩ ሙህራን ኹሉ ኃሳቡ ሳይንሳዊ አይደለም ብለው እየነገሩት ፤ እታገልላችኋላው የእሚላቸው ሰራተኞች ራሳቸው ጥያቄያችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ከተመለሰ የአመጽ መንገድ አንፈልግም እያሉት ፤ ኃሳቡን ብቻ መቀበል የእሚፈልጉትን የመሰብሰብ ዝንባሌው ፤ ምንም እንኳን ነባራዊው ሳይንስ እና ፍልስፍና ዓለምን ለመረዳት እንጂ ለመለወጥ አይጠቅምም የእሚል ማጣጣያ ቢያቀርብበትም ፤ የእማይጠይቅ ተከታይ ከማፍራት ፍላጎት ፤ እንደ እሚመነጭ ግልፅ ነው ።


ይኽን ከሙህራን የመሸሽ ኺደት ፤ ማርክሲስቶች እንደ እዚኽ ዘግበውታል ፦


“ማርክሲዝም የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ ከከስመ በኋላ በኹለተኛው ዓለም ዓቀፍ የሠራተኛውን መደብ ትግል ከቡርዣ ተፅኖ ተከላክሎ የበላይነቱን ጨበጠ ።”

“Marxism after the dissolution of the First and the formation of the Second International gained the hegemony in the struggle of the working class to bar bourgeois influences from its movement [30] “


ይኽ ጽሑፍ በተጠቀሰበት ፤ በእዚኹ ጽሁፋቸው ፤ ትችታቸው የመጀመሪያውን ዓለም ዓቀፍ ያከሸፈው እና ከምኒስቶች የቡርዣ ተፅኖ የእሚሉዋቸው ፤ በእዚኽም ምክንያት ማርክስ የሸሻቸው ሰዎች ፦ የዩኒቨርስቲ መምህራኖችን ፣ ፈላስፎችን ፣ ወዘተ ፤ እንጂ በዝባዥ የእሚባሉትን ባለ ኃብት አይደሉም ፦


“በትችት መሳሪያ ፤ የፍልስፍና ዳክተሮች ፣ የዩኒቨራቲ መምህራን ፣ ፕሮፌሰሮች ፣ የካፒታሊስቱን ፍላጎት የእሚወክሉ ማሕበራት እና ነጻ (በድርጅት ያልታቀፉ በግል የእሚሰሩ) ምሑራን ፤ እነዚኽ ኹሉ ትንሽ እና ትልቅ የቡርዣ ኃሳብ አፍላቂያን ፤ ማርክሲዝምን ለማጥፋት መጥተው ነበር ።”

“Through the weapon of criticism. An entire caste of Doctors of Philosophy, university lecturers, professors and syndics representing capitalist interests and independent scholars, an entire caste of large and small-scale producers of bourgeois ideology, was formed to “kill off” Marxism [30]“ 


እንግዲኽ ማርክስ የሸሻቸው ፤ ፀረ አብዮተኛ የአላቸው ፤ ከላይ እንደ አልነው ባለ ኃብቶችን ፣ ከምኒዝም  ላይ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ አድርጉልኝ ብሎ ካፒታሊስቱ የቀጠራቸው ‘ምሁራንን’ ወይንም ቦዘኔዎችን አይደለም ፤ ነገር ግን ፥ በራሳቸው ተነሳሽነት የመጡ ፦ የፍልስፍና ዳክተሮች ፣ የዩኒቨራቲ መምህራን ፣ ፕሮፌሰሮችን ፣ ወዘተ ፤ ነው ።

 

ይኽ ደግሞ ፤ እላይ የማርክሲዝም ጸረ ሳይንሳዊነት በእሚለው ርዕስ ስር ከአስቀመጥነው ፤ የማርክስ ፀረ ኃይማኖት ብቻ ሰአይኾን ፀረ ምሁር አካኼድ ጋር የእሚጣጣም ወይንም መዋቅራዊ እና ኹሉንም ዓይነት ምሁር የማግለል መርኃዊ አካኼድ እንጂ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም ።


ማርክሲዝም ሳይንሳዊነትን እንደ ለምድ ለማወናበጃነት የእሚለብሰው እንጂ ዋናው ግቡን ስልጣን እና ዘረፋ የአደረገ እንቅስቃሴ የኾነው ፤ በኋላ በእነ ሌኒን ዘመን ሰአይኾን  ፤ ከጠንሳሾቹ ከእነ ማርክስ ዘመን አንስቶ መኾኑ ፤ በራሱ በማርክስ ተግባር የተረጋገጠ ለመኾኑ ፤ ይኽ ከላይ የተጠቀሰው ክስተት ዓይነተኛ ማሳያ ነው ። 

ከእዚያኽን ግዜ አንስቶ ፤ ማርክስዚም በስልጣን ላይ በነበረባቸው ወቅት በሙሉ ምሁር የእማይወድ ስረዓት መኾኑ በርዕዮት እና በተግባር ደረጃ የተረጋገጠ ነው!


ማርክሲስታዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ፤ ከሐይማኖተኛ የባሰ ጭፍን ተከታይ የእሚያፈሩበት አግባብም ይኼው ነው ። ከእዚኽም የተነሳ እነዚኽ ምርጥ እማይጠይቁ ማርክሲስቶች ፤ ሚሎቨን ዲለስ እንደ እሚለው ፦


“ከምኒስቶች በራሳቸው እንደሚኮፈሱት የዘውድ ስረዓት አራማጆች እንኳን አይኮፈሱም ወይንም የዘውድ ስረዓት የከምኒዝም ን ያህል ፍፁማዊ ስረዓት አልነበረም”

“The monarchy did not think quite as highly of itself as thе Communists do of themselves, nor was it as absolute as they are. [11]“


ምክንያቱም ፦ ማርክሲዝም በመርህ ደረጃ ፤ ምንም ዓይነት ጥየቃ እና ምርምር ሳያደርጉ ፤ ማርክሲዝምን እንደ እንከን የለሽ የሰው ሰአይኾን የተፈጥሮ ሕግ የእሚወስዱትን በመሰብሰብ ስለ እሚመሠረት ነው ። 


ከእዚያኽም በኃላ ፤ እነዚኽ ጭፍን ተከታዮች ፤ ያለምንም ማመንታት በድፍረት እና በእቡይነት ፤ ማርክሲዝም የእማይሻር እና ኹሉም ሊቀበለው የእሚገባ የማሕበረሰብ ሕግ ነው ብለው ለመንቀሳቀስ ብዙም አይቸግራቸውም ፦


“ማሕበረሰብን የእሚገዛውን መርሕ እኛ ብቻ ነን የእምናውቀው ከእሚል ምክንያት ፤ ኢሳይንሳዊ እና ለግልፅነት በእሚል አጉል እንዲቀል የተደረገ መላምት አስቀምጠው  ፥ ማሕበረሰብን ለመለወጥ እና እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር ብቸኛ በአለመብት እና በአለስልጣን እኛ ብቻ ነን ፤ የእሚል ድምዳሜ ላይ አደረሳቸው ።”

“Beginning with the premise that they ALONE know the laws which govern society, Communists arrived at the oversimplified and unscientific conclusion that the alleged knowledge gives them the POWER AND EXCLUSIVE right to change society and to control its activities [11].”


በግዜ ኺደት ፤ የማርክስ ፥ የሙግት እና የታሪክ ቁሳዊነት የእሚለው አስተምህሮ ፤ ሊቀየር የእማይችል የተፈጥሮ ሕግ እንደኾነ በማስቀመጥ ፤ የከምኒስት አብዮተኞች ፤ የካርል ማርክስን ትምህርት የእማይቀበል ፤ የተለየ ኃሳብ የአለው ሰው ሰአይኾን  ፤ ፀረ አብዮተኛ እና ተፈጥሮዋዊ የታሪክ ኺደትን የእሚያደናቅፍ ወይንም የእማይቀበል ፥ ታሪካዊ ስህተት ወይንም ደንቃራ እንጂ ሰው እንደ አልኾነ ወደ እሚቆጥሩበት ደረጃ ይደርሳሉ ፦ 


“ግዜ በኼደ ቁጥር ፤ የማርክስ ተከታዮች ፤ የማርክስ አስተምህሮ ጥንቅቅ ያለ ፤ ኹሉን አካታች ዓለምን ገላጭ ኃሳብ አድርጎ የማቅረብ ዝንባሌ እና ይኽንንም ጥንቅቅ ያለ የማርክስን ሥራ ማስቀጠል የእነርሱ ኃላፊነት ነው ብሎ የማሰብ ዝንባሌ አመጡ ። ቀስ እያለም ፤ ሳይንስ ለፕሮፕጋንዳ ቦታ እየለቀቀ መጣ ፤ በስተመጨረሻም ፕሮፖጋንዳው ሳይንስ ኾኖ ወደ መቅረብ መጣ ።”

“As the time passed, Marx's successors revealed а tendency to present his teachings as а finite and all-inclusive concept of the world, and to regard themselves as responsiЬle for thе continuation of all of Marx's work, which they considered as beiпg virtualy complete. Science gradually yielded to propaganda, and as а result, propagaпda tended more апd more to represent itself as science [11].”


እነ ትሮትስኪ ዓይነት የሥራዓቱ መሪዎች ራሳቸው ፤ የከምኒስት ፓርቲ ሰው ሰራሽ ሰአይኾን ተፈጥሮዋዊ ነው በማለት ፤ ፓርቲው ሊሳሳት አይችልም እስከ ማለት አደረሳቸው ፦


“ፓርቲው ሊሳሳት አይችልም ፤ ምክንያቱም የታሪካዊ አስፈላጊነት የወለደው (አካል ያለበሰው) በመኾኑ ።”

“The party is infalible, for it is the incarnation of a historical necessity [11]“


ከእላይ እንደ አልነው የፓርቲው ወይንም የእንቅስቃሴው መሪዎች ፤ ከሙህራን እየሸሹ ፤ ይኽን መሰሉን ፖለቲካዊ ሳይንስን እና ኃይማኖታዊ መሰል ጭፍን ታዛዥነትን የእማይለይ ጭፍን ታዛዥ እየፈለጉ ፤ ጆሮዋቸውን እንኳን ቢቆርጡዋቸው ሌላ ነገር መረዳት የእማይችሉ ሰዎችን ኾን ብለው የእሚሰበስቡት ፤ ጨካኝ መቺ ኃይል ለመፍጠር ከአላቸው እቅድ ነው ። 


ለዛም ነው ፤ ሳይንሳዊ ነኝ የእሚለው ከምኒዝም በውስጡ ወይንም እውነተኛ መልኩ የተጨባጫዊያን ፤ ትክክል እና ስነ ምግባር የተላበሰ ለመኾን አትጨነቅ ፤ ጠላቶችህን አዘናግተህ በኃይል ጨርሳቸው እና የፖለቲካ ስልጣን ያዝ የእሚለው ፤ የኃይል አካኼድ ራሱን በሳይንስ ስም የሰወረበት የእሚመስለው ፦


“በቋሚነት … ኃይል ራሱን እንደ እማይታይ ፣ እንደ እማይወራ እና ስውር ተፈጥሮዋዊ እና ዋና ግብ ራሱን ደብቋል።”

“Throughout...power has concealed itself as the hidden, invisible, unspoken, natural and principal end. [30]“ 


ይኽም በመኾኑ ፤ መጀመሪያ ላይ ከምኒዝም ራሱን ፤ ከሙህራን እና ከሳይንሳዊ ግምገማ ያሸሻል ። ይኽ ሽሽት ግን ፤ ጭፍን ታማኝ እና ታዝዥ ተከታይ እስኪገኝ የእሚደረግ ግዜያዊ ሽሽት ነው ። የታዘዘውን ማንኛውም ወራዳ እና ጨካኝ ተግባር በፓርቲ ፍቅር ስም ለመፈፀም ምንም ዓይነት የህሊና ክልከላ የሌለበት ታማኝ ከተገኘ በኋላ ፤ በእዚኽ በወታደራዊ ዓይነት ታዛዥነት በተቃኘ እና በተደራጀ ጥቂት ኃይል ፤ ራሳቸውን ብቸኛ የፖለቲካ ኃይል እስኪ ያደርጉ ድረስ ፤ ኹሉንም ዓይነት ተቀናቃኝ ያለ ርኽራኼ ያጠፋሉ ።


ለእዚኽም ፤ ይኽን የሰበሰቡትን ጭፍን ታዛዥ ፤ ወለም ዘለም በእማይል መዓከላዊ ታዛዥነት ያደራጁታል ፦


“የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲኽ በጋመበት በአኹኑ ሰዓት ፤ የከምኒስት ፓርቲ ሚናውን መጫወት የእሚችለው ፤ በፍፁም ማዕከላዊነት ተዋቅሮ ፣ የወታደር ዓይነት እንደ ብረት የጠነከረ ስረዓት ይዞ ፣ ይኽም ማዕከላዊ አወቃቀር የሚያጥረገርግ ኃይል ተላብሶ ፣ ተቀናቃኝ የሌለው ስልጣን ተላብሶ ፣ የአባላቶቹን ሙሉ ድጋፍ ሲያገኝ ነው ።”

“At the present moment of hard fought civil war, the communist party will be able to fulfil its role only if its organized in a totally centralized fashion, if its iron discipline is as rigorous as any army, and if its central organization has sweeping powers, is allowed to extend uncontested authority, and enjoys the unanimous confidence of its members. [23]“ 


በግዜ ኺደት ይኽን ጭፍን ከሰበሰቡ እና ከአደራጁ በኋላ ፤ ሊያጠፉት በእሚፈልጉት ተቋም ወይንም መንግሥት ውስጥ ያሰርጉት ይጀምራሉ ፦


“…ከተግባሮቻችን ዋናው ፤ ሕጋዊ እውቅና ከአላቸው ድርጅቶች በተጓዳኝ ፤ በወሳኙ ሰዓት (ነውጥ በእሚነሳበት ሰዓት) ወሳኝ ኩነቶችን መፈፀም የእሚችሉ (የእርስ በእርስ ጦርነት ማስነሳት የእሚችሉ) ህቡዕ ድርጅቶችን ማቋቋም ይኾናል።” 

“It is the duty to set up everywhere, in parallel to the legal organization, an UNDERGROUND MOVEMENT capable of decisive action (meaning starting civil war) in service of the revolution at the moment of truth (i.e., at the time of the insurrection) [23]“


ይኽ ተሰውሮ ግዜ የእሚጠብቅ መቺ ኃይል ፤ እነርሱ ግዜው ደረሰ በእሚሉበት ግዜ ፤ ያለ ምንም ክልከላ የጭካኔ ተግባሩን ይፈፅማል ፦


“የሠራተኛው አብዮት የብረት እጆች ጠላቶቹን የእሚመታበት ግዜ ሲመጣ ምንም ዓይነት ክልከላ የለም ።”

“There were no restrictions when the time came for the iron fist of THE DICTATORSHIP of the proletariat to smite its foe. [23]“


ይኽ ግዜ ደርሶ አብዮቱ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት በእሚሸጋገርበት ግዜ ፤ የከምኒስት ፓርቲ መሪዎች ወደ ስልጣን የእምናደርገውን ጉዞ ያደናቅፋል ያሉትን ፤ የፓርቲያቸውን አባላት ጨምሮ ፣ ሙህራንን ፣ ነጋዴዎችን ፣ የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ፣ ወዘተ ፤ በአጠቃላይ ወታደር ያልኾነውን የማሕበረሰብ ክፍል በወታደራዊ አካኼድ ያለ ርህራኼ ያጠፋሉ ።


ይኽ የከምኒስቶች አካኼድ ፤ በወታደራዊ ውጊያ ተቃራኒ የእሚባሉ ኃይላት የእሚያካኺዱት እንጂ ሰላማዊ የፖለቲካ ኃይላት የእሚያካኺዱት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል አይደለም ።  


 ለዋነኞቹ የከምኒስት መሪዎች ስልጣን አስጊ የኾኑትን የፓርቲውን አባላት ፤ አብዮት ልጆቿን ትበላለች ብለው ፤ ያስወግዱዋቸዋል ፦


“የከምኒስት አብዮቶች ‘ልጆቻቸውን ሊበሉ ይችላሉ’ ኹሉንም ግን አይደለም”

“Communist revolutions may “eat their own children” but not all of them. [11]“


 የውስጥ ተቀናቃኞቻቸውን ከአስወገዱ በኋላ ፤ የከምኒዝም እኩይነት ሳይገባቸው ከምኒዝም ስለ ራሱ እንደ እሚለው ፤ ለድኾች የቆመ የፍትሕ አቀንቃኝ የእሚመስላቸው ከከምኒስት ፓርቲው ውጭ የእሚገኙ ሕዝባዊ እና ተራማጅ ኃይላት ላይ ፤ አብዮቱን ተገዳደሩ በእሚል በራሺያ እንደ ቼካ በእኛ ሐገር አብዮት ጥበቃ የእሚባሉትን ገዳይ ቡድኖች ይልኩባቸዋል ፦


“ሰራተኞቹ ፤ በሜንሼቪክ ፣ በሶሻሊስት አብዮተኞች እናም በሌሎች ዲቃላ ፀረ አብዮተኞች ተፅዕኖ ፤ አድማ በመምታት ፤ የተለያዩ ፓርቲዎችን ያካተተ መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል ። በከተማው ኹሉም ሰው ሊያየው በእሚችለው ቦታ እንዲኽ የእሚል ትልቅ ማስታወቂያ ለጥፍ ፦ ቼካ በሶቭየቱ (ደርጉ ወይንም ከሚቲው) ላይ የእሚያሴሩ ሽፍታዎችን ፣ ሌቦችን ፣ ነጋዴዎችን ወይንም ማንኛውንም ፀረ አብዮተኛ በተገኙበት ይገድላል ። የየአከባቢውን ቼካ እንዴት ነው የእማቋቁመው ካልኽ ፤ የሰዎችን አፍ ለመዝጋት ጭንቅላታቸውን በጥይት ከመምታት ያለፈ የተሻለ መንገድ እንደሌለ የገባቸውን ሰዎች በማፈስ መኾኑን እወቅ ።”  

“The workers, under the influence of the Menesheviks, the Socialist Revolutionaries, and other counterrevolutinary bastards, have all gone on strike, and demonstrated in favor of a government made up of all the different socialist parties. Put big posters up all over the town saying that the Cheka will execute on the spot any bandit, theif, speculator, or counter revolutionary found to be conspiring against the Soviet....you ask how to form the local Cheka; just round up all the most resolute people you can, who understand that there is nothing more effective than a bullet in the head to shut people up. [23]“


በእዚኽ ግልፅ አዋጅ እንደ እሚታየው ፤ እነ እዚኽን ሰላማዊ ጥያቄ የጠየቁ የሐገሬው ሕዝብን ወንጀለኛ ያስባላቸው እና ክርክርን ለማሸነፍ ጭንቅላትን በጥይት ከመምታት የተሻለ መንገድ የለም ብሎ የእሚለው ቼካ (አብዮት ጠባቂው) ያስላከባቸው ፤ ከምኒዝም ቆምኹለት የእሚለው ዓይነት ሕዝባዊ እና ሠራተኛውን ያሳተፈ መንግሥት ይቋቋም ስለ አሉ ነው ።


በእዚኽ መልክ ፤ የድርጅታዊ ቅርፅ የአላቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ከአጠፉ በኋላ ፤ የፍትሕ ከሚሳር በእሚሉዋቸው ሰዎች አማካኝነት ደግሞ ወደ ሕዝቡ ውስጥ ሰርፀው ፤ ያልተደራጁ ነገር ግን ንቃት የአላቸው እና ለ’አብዮቱ’ ስጋት ሊኾኑ ይችላሉ የእሚሉዋቸውን ሰዎች ያጠፋሉ ፦


“ስቴንበርግ ሌኒንን ይጠይቀዋል ‘የሕዝብ ከሚሳር ለፍትኽ ብሎ መሰየም ምን ጥቅም አለው ?’ የሕዝብ ከሚሳር የማሕበረሰብ ክፍሎችን ለማጥፋት ተብሎ ቢሰየም የበለጠ ተዓማኒ እና ሕዝቡም በቀላሉ የእሚረዳው ይኾን ነበር ። ሌኒንም ሲመልስ ፤ ‘ግሩም ኃሳብ’ የእኔም እይታ እንደ እዛው ነው ፤ የእሚያሳዝነው ግን እንደ እዛኽ ብሎ መሰየሙ ብዙ ርቀት አያስኼድም።”

“What is the point of a ‘people’s Commissariat for Justice?” Steinberg asked Lenin. “It would be more honest to have a People’s Commissariat for Social Extermination. People would understand more clearly.”

“Excellent idea,” Lenin countered.” That is exactly how I see it. Unfortunately, it wouldn’t do to call it that! [23]“


በእዚኽ የስቴንበርግ እና የሌኒን ውይይት ላይ እንደ እሚታየው ፤ የፍትሕ ከሚሳር የእሚለው ቃል ፤ ሕዝቡን ትንሽ ግራ አጋብቶታል ለምን አጥፊ ቡድን ብለን በግልፅ አንሰይመውም በእሚለው ጉዳይ ላይ ነው የእሚወያዩት ።


በውይይቱም ስቴንበርግ ፤ የፍትሕ ከሚሳር ብለን ሕዝቡን ግራ ከእምናጋባው ፤ ግልፁን ገዳይ ቡድን ብለን ነግረነው የአብዮቱን ጠላቶች ግደል ብንለው ይቀላል ብሎ ላነሳው ኃሳብ ፤ የበግ ለምድ የለበሰው ቀበሮው ሌኒን ፤ እኔም እንደ እዛኽ ነው የእማስበው ነገር ግን ፤ በግልፅ እንደ እዛኽ ብሎ መናገሩ ብዙ ርቀት አይወስደንም እና በእዚኹ ስሙ ይቀጥል እያለ ነው ። 


ሌኒን ስለ ነጋዴዎች እንደ እዚኽ ይላል ፦


“ነጋዴዎችን በእሚገባቸው መንገድ እስከ አለ አስተናገድናቸው ፤ እርሱም ጥይት ጭንቅላታቸው ውስጥ በማኖር ፤ የትም ልንደርስ አንችልም ።”

“Lenin…” For as long as we fail to treat the speculators the way they deserve – with a bullet in their head – we will not get anywhere at all. [23]“


በትምሕርታቸው የተሻሉ ሰዎችም የከምኒስቶች የጥፋት ዒላማ ናቸው ፦


“በፖላንድ…የሚታሰሩ ሰዎች ዝርዝር አዘጋጁ…በእዚኽ ዝርዝር ላይ በቀዳሚነት የእሚገኙት ፤ ‘ጠላት የመኾን እምቅ አቅም የአላቸው’ ያሉዋቸውን በትምህርታችው ጥሩ የነበሩ ተማሪዎችን ነው።”

“… in Poland…they drew up lists of people to be arrested…at the top of these lists were the names of able pupils, whom they judged to be “potentially hostile. [23]“


በእዚኽ መልኩ ፤ ምህዳሩን ከኹሉም ዓይነት ተቀናቃኝ ከአፀዱ በኋላ ፤ ከገበሬ ማሕበር አንስቶ እስከ ቲያትር ክበብ ኹሉንም ማሕበራዊ አድረጃጀቶች በሙሉ በፓርቲው ቁጥጥር ውስጥ ያስገባሉ ፦


“አዲሱ መደብ ፤ ከጠቅላይነቱ እና ከብቸኛ-ገዢ አባዜው የተነሳ ፤ የእማይቆጣጠረውን ወይንም በእጁ ያለ አስገባውን ነገር ፤ ሊያስቀረው (ይኽን አባዜውን) በእማይችል መልኩ ለማጥፋት ወይንም ለመቆጣጠር ይሰራል። በራሺያ  የገበሬ ማሕበር ምሥረታ አስፈሪ እና አውዳሚ ጦርነት ነበር ፤ እንዲኽም ኾኖ የአዲሱን መደብ ስልጣን ለማስቀጠል ስለ እሚያስፈልግ  የግድ መደረግ ነበረበት እና ተደርጓል ።”

“Because of its totalitarianism and monopolism, the new class finds itself unavoidably at war with everything which it does not administer or handle, and must deliberately aspire to destroy or conquer it. … Collectivization was а frightful and devastating war which resembled an insane undertaking-except for the fact that it was profitable for the new class by assuring its authority [11].”


የኪነ ጥበብ ሞያተኞች ፤ በማሕበራዊ ተጨባጭነት ወይንም ፤ ከላይ የገለፅናቸው እንደ የታሪክ ቁሳዊነት ባሉ መርኾች ተቃኝተው ፤ ያንን ለሕዝቡ በማስተማር ተግባር ላይ ብቻ እንዲ ወሰኑ ይፈልጋል ፦


“‘ማሕበራዊ ተጫባጫዊነት’ የእሚለው ምን ማለት እንደኾነ በአግባቡ የተቀመጠ ትርጉም በአይኖርለትም ፤ በተግባር ግን የከምኒስት ፓርቲ በኹሉም መስክ የኃሳብ ብቸኛ አከፋፋይ የመኾኑ ማሳያ ነው ። ጥረቱም ፤ ጠባብ እና ኋላ ቀር የኾኑት የከምኒስት መሪዎች ኃሳብ በኪነጥበብ በአለሞያዎች እየተንቆለጳጰሰ እና ተሽሞንሞኑ እንዲቀርብ ማድረግ ነው ። ይኽም ፤ መንግሥት ቢሮክራሲያዊ በኾነ መንገድ ፤ ኪነጥበብንም ሳይቀር ኃሳብን በሙሉ እንዲቆጣጠር የተገበዘ ምክንያት ይሰጠዋል ።” 

“Not having been evolved into а complete theory, “Socialist Realism” actually means ideological monopolism by communist party.  It calls for efforts to clothe the narrow, backward ideas of the leaders in art forms and for their works to be depicted romantically and panegyrically. This has led to а Pharisaic justification of the regime’s control over ideas and to bureaucratic censorship of the needs of art itself [11].”


በእዚኽ መልኩ ፤ ሳይንሳዊ ስለ መኾኑ እና የእማይሻረው የተፈጥሮ ሕግ ነፀብራቅ ነው የተባለው ከምኒዝም ፤ በሳይንሳዊነት ብዙ ቅስቀሳ ከተደረገበት በኋላ ፤ ጢሱ ሲበን እና አቧራው ሲረግብ ፤ በተፅኖ ክልሉ ውስጥ ያሉትን ማንኛውም ሰዋዊ እንቅስቃሴዎች ያለምንም ተቀናቃኝ በፍፁማዊ አምባገነናዊ ስልጣን የእሚገዛ አዲስ መደብ ይፈጠራል ።


ሚሎቨን አዲሱ መደብ የእሚላቸው ፤ በሶሻሊስት አብዮት የፖለቲካ ስልጣን ከያዙ በኋላ ራሳቸውን ወደ ገዢ መደብነት የቀየሩ የከምኒስት ፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችን ነው ። ከእላይ የጠቀስኩት የሚሎቨን መጽሐፍም ርዕሱ ፤ አዲሱ መደብ (The New Class) የእሚል እና የእነዚኽን ሰዎች ፖለቲካዊ ታሪክ የእሚዘረዝር ነው ።

ከእዚኽ የተነሳ ፤ የማርክሲስት አብዮት ፤ ለሕዝብ ጥቅም የበላይነተ የተደረገ ነው ማለት ፤ ባዶ ማባበያ ነው የኾነው ፦


“የሠራተኛው አምባገነንነት የእሚለው ብኺል ፤ ባዶ መፈክር ኾነ።…እንደ ከምኒዝም  ባሉ ጠቅላይ ገዢዎች ፥ የሠራተኛው አምባገነንነት ከምኒዝምን ሳይንሳዊ ለማስመሰል የእሚቀርቡ መላምቶች ወይንም ጥቂት አምባገነኖች ስልጣን ባለቤት እነርሱ እንደኾኑ እንደ አይታወቁ የእሚጠቀሙበት ጭምብል ነው ።”

“The claim that it the dictatorship of the proletariat becomes an empty slogan. …In totalitarian government of this type, the dictatorship of the proletariat is a theoretical justification, or the ideological mask at its best, for the authority of some oligarch [11].”


በእዚኽ አግባብ ስልጣንን ከያዙ እና ከአደራጁ በኋላ ፤ እንደ ስታሊን ያለ አንድ ሰው ፤ እንደ ፍፁማዊ ንጉሥ የፈለገውን ውሳኔ ያለተቀናቃኝ የእሚያካኺድበት ኹኔታ ወይንም ከእዚኽ ቀደም ከነበሩት አምባገነን ስረዓቶች ኹሉ የላቀ ፤ ማሕበርሰባዊ ምድረበዳ ላይ የእሚገዛ ፍፁም አምባገነን ይኾናል   ፦


   “ሰውየው (ስታሊን) ፤ ክርሱቾፍ ራሱ በዘመኔ ያየኹት ‘ምርጥ ማርክሲስት’ ብሎ የመሰከረለት ፤ በማርክሲዝም ፍልስፍና ውስጥ ትልቅ ቦታ የአለውን ዳስ ካፒታል የእሚባለውን መጽሐፍ አላነበበም ። በእርግጥ ስታሊን የእማይናቅ ፤ የፖለቲካ ታሪክ እውቀት በተለይ በራሻ ላይ የአለው ሲኾን ፤ ከእዚኽም ጋር አስገራሚ የማስታወስ ችሎታ አለው ። ስታሊን ሚናውን ለመጫወት ከእዚኽ በላይ እውቀት አላስፈለገውም ። ከእርሱ ፍላጎት እና እይታ ጋር የእማይገጣጠመውን ነገር ፤ ‘ጥላቻ የተሞላ’ እያለ ያግደዋል ።”

“This man (Stalin), whom khurschev himself today acknowledge to have been the “best Marxist” of his time, had not even read Marx’s das Kapital, the most important work on Marxism. Stalin had considerable knowledge of political history only, especially Russian, and he had an uncommonly good memory. Stalin really did not need any more than this for his role. Anything that did not coincide with his needs and his views he simply proclaims it as “hostile” and forbade it [11].”


ከእዚኽም የተነሳ ፤ ከምኒዝም ፤ በፕሮፖጋንዳ ሳይንሳዊ ነኝ እያለ ፤ በአብዮት የያዘውን የመንግሥት ስልጣን የእሚያስቀጥለው ፥ በሕዝብ ላይ መንግሥታዊ ማሸበር እና ወንጀል በመፈፀም ነው ። ይኽንንም የከምኒስት ጥቁሩ መጽሐፍ እንዲኽ አስቀምጦታል ፦


“…የከምኒስት መንግሥታት ወንጀልን በአጋጣሚ አይደለም የእሚፈፅሙት (የአጋጣሚ ወንጀል መንግሥታት ኹሉ ይፈፅማሉ) ፤ ከምኒስቶች ‘ተፈጥሮዋቸው’ ራሱ የወንጀል ተቋም ነው ፡ በመርህ ደረጃ በእሚባል ዓይነት በሕገ-ወጥነት ነው ሐገር የእሚመሩት ፤ ለሰው ሕይወት ምንም ዓይነት ክብር ሳይኖራቸው ፤ በአመፅ ጉልበት ይገዛሉ።”

 “…the Communist regimes did not just commit criminal acts (all states do so on occasions), they were criminal enterprises in their essence: on principle, so to speak, they all ruled lawlessly, by violence, without regard for human life. [23]“


“ለከምኒስት መንግሥት ሐገር መግዛት ወይንም ማስተዳደር ማለት ፤ በእየ እለቱ አፋኝ እና ጨቋኝ እርምጃዎችን ያለ ማቋረጥ ማስቀጠል ማለት ነው ።”

 “A routine of administering repressive measures on a daily basis, --- that was the core of communist governance [23]“


ምን ዓይነት መንግሥት ፥ የትኛውስ አብዮት ነው ሰው በኮታ የእሚገድል? ከምኒዝም  በስትራቴጂ ደረጃ ፤ ማሕበረሰብ እንደገና ማዋቀር በእሚል ብኺል ፤ የሰዎችን ግላዊ ማንነት ፣ ምንነት ፣ ወዘተ ፤ ሳያውቅ በመደባዊ አስተሳሰብ ብቻ ከእዚኽ አከባቢ ይኽን ያኽል ሰው ገድላችሁ ሪፖርት አድርጉ ብሎ የእሚያዝ አስገራሚ ፅንፈኛ ነው ፦


“… ኮታ የእሚባል አሰራር በማስተዋወቅ ፤ እያንዳንዱ ክልል እና ወረዳ ፤ ጠላት ተብለው ከእሚሰየሙት የማሕበረሰብ መደብ ውስጥ የእሚገኙ ሰዎች ይኽን ያህል ፐርሰንት (እጅ) ይታሰር ፣ ይፈናቀል ወይንም ይገደል ይላል ። ይኽ ኮታ ደግሞ በፓርቲው ቁጥጥር ከአንድ መዓከል የእሚወሰን ነው ።”

“…introduced a quota method, each region and district, had to arrest, deport or shot a certain percentage of people who were members of several “enemy” social class. The quotas were centrally defined under the supervision of the party [23].”


ይኽን መሰሉ የከምኒስት ፓርቲ ጭካኔም የራሺያን መንግሥት ወደ ወንጀል ውስጥ አስገብቶት እንደ ነበር ፤ ከስታሊን በኋላ በኹለተኝነት የሶቭየት ሕብረት ፕሬዘዳንት ኾኖ የነበረው ኒኪታ ክርስቼቭ በአደባባይ ያመነው ነው ፦


“ክሩስቼቭ እ.አ.አ. በ1956 ዓ.ም. ፓርቲው ወደ ወንጀል እንደገባ ተናዟል ።”

 “Khrushchev in 1956 confessed, the party has deviated to be a criminal [23]“


በእርግጥ ፥ ከምኒዝም  ስለ ራሱ እንደ እሚለው ፤  ለሕዝብ ፍትሕ የታገለ ፓርቲ መስሏቸው ፤ ሕይወታቸውን ፣ ጉልበታችውን እና የአላቸውን ነገር በሙሉ ፤ ለእዚኽ ዓላማ የሰው ሰዎች አሉ ። ነገር ግን ፤ ከምኒዝምን በአግባቡ የተረዱት ሰዎች ፤ የከምኒዝም  ሳይንሳዊነት ፤ እንዴትም አድርገህ የፖለቲካ ስልጣን ከያዝኽ በኋላ ፤ በሽብር ፣ በወንጀል እና በአፈና ፤ የመላ ሕዝቡን ጉልበት እና ኃብት በቁጥጥርህ ስር አድርግ የእሚለው ፤ የተጨባጫዊያን የስልጣን ብሎም የፖለቲካ ፍልስፍናን በሳይንሳዊ ስም አቅርበህ ተጠቀምበት የእሚሉት ናቸው ፤ ከእዚኽም የተነሳ ፥ በስረዓቱ አድናቂያን እና በስረዓቱ ተጠቃሚዎች መካከል ፤ መሠረታዊ የአረዳድ ልዩነት አለ ፦


“የከውምኒስቶች ቋንቋ ከሕዝባቸው ጋር አንድ ከእሚኾንበት ይልቅ የእሚለያይበት ይበልጣል ። ኹለቱም አንድ ዓይነት ቃል ይጠቀማሉ ፤ ቃላቶቹ የእሚገልፁት ኃሳብ ውስጣዊ ትርጉሙ ግን ከምኒስቶች ብቻ ነው የእሚገባቸው ።”

“The languages which the communists speak are hardly the same with their own people. The words are the same, the expressions, the meaning, the inner sense, all of these are their very own. [11]“


ይኽን መሰሉም ፤ መደናገር ፥ የፖለቲካ እና ማሕበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎችን ሳይቀር ፤ ከምኒዝም  እንደ ተራ በአመፅ ስልጣን የመያዣ እና የማስቀጠያ ስረዓት ሰአይኾን  ፤ እንደ ሳይንሳዊ የማሕበረሰብ ፍልስፍና ተመልክተውት ፤ ራሳቸውን አደናግረዋል ። ይኽን ኹኔታ የከምኒዝም  ጥቁሩ መጽሐፍ ጸኃፍት እንደ እዚኽ ገልፀውታል ፦


“ይኽ ድኽነት (የግንዛቤ) ደግሞ ከምኒዝምን እንደ ‘ተፈጥሮዋዊ’ ማሕበራዊ ኺደት ውጤት ፤ ከአጉል ንክኪ እና መድሎ በፀዳ ኹኔታ መረዳት ይቻላል ብሎ ከማሰብ የመነጨ ነው ። ይኽንም ተከትሎ ፤ ተመራማሪዎች ፤ የጥቅምቱ አብዮት የሰራተኞች አብዮት እንጂ በአንድ ፓርቲ የተደረገ መንግሥት ግልበጣ አይደለም ብለው አስረግጠው ያስቀምጣሉ ፤ እውነታው ግን ፤ የፓርቲው መንግሥት ግልበጣ በሰራተኞች አብዮት ታዝሎ ነበር ።”

“This poverty flows from the premise that communism can be understood, it is an aseptic and value free mode, as the pure product of social process. Accordingly, researchers have persistently insisted that the October revolution was a worker’s revolution not a party coup d’état while the latter was piggyback riding on the former [23].”


ድምዳሚያችንን ሚዛናዊ ለማድረግ ፤ አንዳንድ ግዜ ነገሮችን በአንድ አቅጣጫ ብቻ ማየት የለብንም ። አንድ የፖለቲካ ስረዓት ፤ ፍፁማዊ ነው ፣ አምባገነን ነው ፣ የጥቂቶችን ተጠቃሚነት የእሚያረጋግጥ ነው ስንል ፤ በአልተገባ ኹኔታ ብዘዎችን ለእንግልት ይዳርጋል ፣ ኑሮን በአልተገባ ኹኔታ ፈታኝ ያደርጋል ፣ የሚልየኖችን ህይወት የአላግባብ ይነጥቃል ፣ ወዘተ ፤ ማለት ነው እንጂ ፤ እንደው ሰው የእሚባል ለምን አይቼ የእሚል ፤ ወረርሽኝ ዓይነት ነው ማለት አይደለም ። 


አንድ ስረዓት ፍፁማዊ ፅንፈኛ ነው ሲባል በጥቂቶች (በሚልዮን የእሚቆጠሩ) ላይ በሕይወት የመኖርን መብት ሲገፍ ፤ አብዛኛውን ሰው ደግሞ ነፃነቱን እና ንብረቱን ሊቀማ ፣ ሊያግድ ፣ ሊያንገላታ ፣ ወዘተ ፤ ይችላል ማለት ነው እንጂ ሐገሬውን በሙሉ በተርታ ይረሽነዋል ማለት አይደለም ። 


አውሬ ነው የእምንለው ከምኒዝም  ፤ የራሻን ሕዝብ 10 በመቶ መግደል አለብን ብሎ ሲያቅድ ፤ እንደ ሰው ያስደነግጠናል ፤ ያ ማለት ግን 90 በመቶውን አልተወም ማለት አይደለም ። እነ እዚኽ የተማሩ ፣ ባለኃብት የኾኑ ፣ የኃይማኖት መሪዎች ፣ ሥራ ፈጣሪዎች ፣ ወዘተ ፤ ለስረአቱ ስጋት ስለ ኾኑበት እነርሱን አድኖ ያጠፋል ፤ የቀረውን የስረዓቱን ጭምብል የእማያስወልቀው እና ጉዳት የእማያመጣውን ይተወዋል ፤ ይተወዋል ብቻ ሰአይኾን  ፤ ከእዛኽ ከቀረው ውስጥ የተወሰነውን ተጠቃሚ ያደርገዋል ፤ ምክንያቱም ፦ ማወቅ የአለብን አንድ ስረዓት ያለሰው ሊቀጥል የእማይችል መኾኑን ነው ።


ጥገኛው ተውሳክ አስጠጊውን በማጥፋት ሰአይኾን እሱ ላይ ተለጥፎ እርሱን መኖሪያው በማድረግ ነው የእሚኖረው ።


ምን ለማለት ነው ፤ ነፍሰ በላ ስረዓት ነው ከምኒዝም  ሲባል ፤ እንደው ኹሉን የእሚቀረጣጥፍ ነው ማለት አይደለም ። ነፍሰ በላ ስረዓትም ለመኾን ስረዓቱን የእሚያስቀጥል ማሕበረሳባዊ መሠረት እና አስፈፃሚ ይፈልጋል ። ዋናው መረዳት የአለብን ፤ የከምኒዝም  ስረዓት ህልውናው ከማንኛውም የማሕበረሰብ ክፍል ህልውና በላይ መኾኑ እናም ይኽንን ለማረጋገጥ ከፍተኛ አቅም የነበረው መኾኑ ነው ። ይኽም ባሕሪው ነው ፤ ከዘመናዊ ፖለቲካዊ ፅንፈኞች ጎራ በቀዳሚነት የእሚያስመድበው ።


ለስረዓቱ አደጋ ናቸው ከአለ ፤ 100 ሚልየን ሕዝብ ከመግደል ወደ ኋላ አይልም ፤ ያ ማለት ግን የሰውን ዘር በሙሉ ያጠፋል ማለት አይደለም ፤ እውቀታቸው ፣ ተወዳጅነታቸው ፣ ችሎታቸው ፣ ወዘተ ፤ ታዋቂ የእሚያደርጋቸው ከኾኑ ወንጀለኛ ይኾናሉ ፤ የቀረው ሕዝብ በአይጠፋም የመከራ ኑሮ እንዲገፋ ይገደዳል ፤ በእዚኽ ውስጥ የተወሰነ ተጠቃሚ የሕብረተሰብ ክፍል የእሚኖር መሆኑ ግን አያጠያይቅም ። 


ከምኒዝም በእዚኽ አካኼዱ ምክንያት ፦ ታዋቂ ኾነው እንኳን ለስረዓቱ ታማኝ ቢኾኑም አይተዋቸውም ። ከምኒዝም  አዋቂነትን ፣ ችሎታን በአጠቃላይ መልካም እሴትን ወንጀል የእሚያደርግ ስረዓት መኾኑ ነው ትልቁ ክፋቱ ። 


ከምኒስቶች ለምሳሌ ፤ በሞያቸው የተመሰከረላቸውን ሙህራን ከትምህርት ቤት ሲያባርሩ ፤ በችሎታው ምክንያት የስረዓት ስጋት ተብሎ የእሚባረረው ብቁ ባለሞያ እና የእርሱ ብቃት ተጠቃሚ ሊሆን የእሚችለው ሰፊው የተማሪው ማሕበረሰብ ሲጎዳ ያለ ሞያው ፥ ያለ ብቃቱ አስተማሪነቱን ቦታ የእሚይዘው ሰው አይጠቀምም ማለት ግን አይደለም ። 


ምናልባትም ፤ ይኽንን ቦታ እንዲይዝ የተመረጠው ሰው ፤ በችሎታቸው ምክንያት ስለተባረሩ ሰዎች ጉዳይ ምንም የእሚያውቀው ነገር ላይኖር ይችላል ። 


ዋናው ፤ ከምኒዝም  ብሎም ናዚ እና ፋሺዝምን እንደ ስረዓት ፤ ፅንፈኞች እና ጨፍጫፊ ናቸው ስእንል ፤ ማሕበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢከነሚያዊ አቅም የአላቸውን ወይንም ሊኖራቸው ይችላል ብለው የእሚያስቡዋቸውን ሰዎች ፤ የፓርቲውን አባሎች ሳይቀር ያጠፏቸዋል ፤ እነርሱን ከአጠፉ በኋላ ግን ፤ እነዚያኽ የጠፉ ሰዎች የእሚፈጥሩትን ክፍት ቦታ በመረጡዋቸው እና ንቃታቸው ደካማ ናቸው በአሉዋቸው ሰዎች መሙላታቸው አይቀርም ፤ እንደ ስረዓት መቀጠል ከአለባቸው። እነዚኽ ተተኪዎች አልተጠቀሙም ማለት አይቻልም ።

 

እንደገናም ከምኒዝም  ወይንም እንደ ከምኒዝም  ያለ ፍፁማዊ አስተዳደር ኢከነሚያዊ እድገት አያስመዘግብም ማለትም አይደለም ። ለምሳሌ ፦ ፍፁም የፖለቲካ ስልጣን ከአለው ፤ በሚልየን የእሚቆጠሩ ሰዎችን አስሮ ፤ እነ እዚኽን ስዎች እስኪ ሞቱ ድረስ በማሰራት ፤ መንገድ ፣ ድልድይ ፣ ወዘተ ፤ በርካሽ ወይንም በነፃ ጉልበት ሊያሰራ ይችላል ፤ ይኽንንም የአደረገባቸው ብዙ ሐገራትም አሉ ። ደሞዝን አጥፍቶ ፣ መብትን አጥፍቶ ፣ ወዘተ ፤ ሰራተኞችን ባሪያ አድርጎ እያሰራ እድገት አስመዘገብሁ ማለት ይችላል ፤ ደግሞም ብሏል ። 


ስለ እዚኽ ፦ ጉዳዩ ያልገባው ከምኒዝም  እኮ እድገት አምጥቷል ሊል ይችላል ። ለእድገት ለእድገትማ የባሪያ ስረዓትም እድገት/ኃብት ይፈጥራል ፤ ዋናው በሰዎች መቃብር እና ስቃይ የእሚፈጠር ኃብት ወንጀል ነው ብቻ ሰአይኾን ፤ መሰል ኢከነሚያዊ እድገት ትክክለኛ ማሕበራዊ መሠረት ስለ እማይኖረው መጨረሻው በሐገር ደረጃ ኢከነሚያዊ እና ፖለቲካዊ ውድቀት የእሚያስከትል መሆኑ ነው ።


እስከ አኹን ፤ ማርክሲዝምን በተመለከተ እያጣቀስን ፣ እያብራራን እና እየተቸን ሰፋ ያለ ዳሰሳ አድርገናል ፤ እስከ አኹን ስንጥል ስናነሳ የነበሩትን ኃሳቦች ጭብጥ ፤ ከእላይ በቀረቡት ሰፊ ዝርዝር ሳይደናገር የማርክሲዝምን ኃሳብ ማጠቃለያ ብቻ ለእሚፈልገው አንባቢ ቀለል በአለ መልኩ ለማስቀመጥ እና እስከ አኹን የተባለውን ያለ ማጣቀሻ መንዛዛት በድጋሚ ለማቅረብ ፤ በእዚኽ ክፍል ስለ ማርክሲዝም የአነሳናቸውን ነጥቦች ጠቅለል አድርገን በኃተታ መልክ ከእዚኽ በታች ለማስቀመጥ ልሞክር።


ማርክሲዝም ፥ የሳይንሳዊነት ጭምብሉ ሲወልቅ ፤ የፖለቲካን ስልጣንን ለመጨበጥ በየትኛውም መርህ እና የህሊና ሕግ ሳይገደቡ ፤ በሰላማዊም ሆነ በአመጽ መንገድ መጠቀም ተገቢ ነው የእሚለው ፤ ተጨባጫዊነት ነው። 


ማርክሲዝም በእዚኽ መልኩ ሳይንሳዊ ለምድ የለበሰ ተጨባጫዊነት ቢሆንም ለአብዛኛዎቹ ተከታዮቹ ሳይቀር ፤ ለብዙ ሰዎች ራሱን የቻለ አዲስ የፖለቲካ ርዕዮት መስሎ የታየው ፤ በጣም የተተነተነ ሰፋ ያለ የጽንሰ ኃሳብ መዋቅር ስለ አለው ነው።


ይኽ የማርክሲዝምን እውነተኛ ገጽታ የሸፈነው ፤ የጽንሰ ኃሳብ መዋቅር ፤ በዋናነት በጥንታዊው የቁሳዊነት (Materialism) ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ነው። 


የእዚኽም የቁሳዊነት ፤ ዋና ጭብጥ ፦ ቁስ ማንም ሳይፈጥረው ከጥንትም የነበረ እና የእሚኖር ነው የእሚል እና ይኽን ቁሳዊውን ዓለም የእሚገዛው ብቸኛው መርህ ፤ ይኽ ቁሱ ዓለም በተለያየ ግዜ የተለያየ ቅርጽ ወይንም መልክ እንዲይዝ በእሚያደርገው በተቃራኒ ዓካላት/ቁሳት መካከል በቋሚነት የእሚደረገው የግጭት ሕግ ነው የእሚሉት ፤ በዋናነት በጥንታዊ የግሪክ ፈላስፎች ዴሞክሪተስ እና ሔራክሊተስ የተቀነቀኑ ኹለት ኃሳቦች ናችው።


እነ እዚኽ የዴሞክሪተስ እና የሔራክሊተስ ኃሳቦች ፤ ለዘመናዊ የቁሳዊነት ፍልስፍና መሠረት በእሚሆኑ መልኩ ፤ በጥንታዊ የግሪክ ፈላስፎች ፤ ዴሞክሪተስ እና ሔራክሊተስ የተቀመጡበት አግባብ ቢሆንም ፤ እነ እዚኽ ኃሳቦች ግን ፤ በኃይማኖት እምነት መልክ ፤ ከግሪኮቹ ቀደም ብለው በግብጻዊያን በኋላም በሕንዶች የቡዲዝም እምነት ውስጥ ሲንጸባረቁ የነበሩ በመሆኑ እና የግሪክ ስልጣኔ የእነ እዚኽ ቀደምት ስልጣኔዎች ወራሽ በመሆኑ ፤ የቁሳዊነት ህፀፅ ፤ ከዴሞክሪተስ እና ከሔራክሊስተስም ቀደም ብሎ በግብጽ እና በህንድ የነበረ በመሆኑ ፤ ግሪኮችም ቢሆኑ የኃሳቡ አዳባሪዎች እንጂ ጀማሪዎች የእሚባሉ አይደሉም።


ማርክስዚምም ፤ ይኽንን በሺ የእሚቆጠሩ ዓመታት እድሜ የአለውን ፤ እንደ አንድ የልዕለ ተፈጠሮ (Metaphysics) ዘውግ ፤ ከኃሳባዊያኑ በተቃራኒ ፤ ቁሳዊነቱን የፍልስፍናው መሠረት ማድረጉ ፤ ከማርክስ ጽሁፎች ብቻ የእሚታይ ሰአይሆን ፤ በማርክሲዝም ፍልስፍና የጠለቀ የጽንሰ ኃሳብ እውቀት እና የተግባር ልምድ በአላቸው እንደ ሚለቫን ዲለስ ፣ ጆሴፍ ስታሊን እና ሌኒን ባሉ የስረዓት ቀንደኛ አቀንቃኞች የተመሰከረ ጉዳይም ነው።


ማርክሲስም ፤ በእዚኽ ጥንታዊ ፍልስፍና ፤ ነገር ግን ሳይንሳዊ ያልሆነው ቁሳዊነት ላይ ከተመረኮዘ በኋላ ፤ የሙግት ቁሳዊነት(Dialectical Materialism) የእሚባል የስነ እውቀት ፍልስፍና እና የታሪክ ቁሳዊነት(Historical Materialism) የእሚባል የሰውን ልጅ ፖለቲካዊ ታሪክ ፤ ጥንት ከነበረበት ከጋርዮሽ ስረዓት ጀምሮ የመጨረሻ ደረጃ እስኪ ደርስ የእሚኖረውን መልክ እተነትናለሁ የእሚሉ መላምቶች አስተዋወቀ።


የሙግት ቁሳዊነት ዋናው ጭብጡ ፤ የሰው ልጆች የፖለቲካ ግንዛቤያቸውን ከየት ነው የእሚያገኙት የእሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የእሚፈልግ ሆኖ ፤ በእዚኽም አካኼዱ ፤ በተመረኮዘበት ጥንታዊ ቁሳዊነት ላይ ሆኖ ፤ መንፈስ ፣ ነፍስ ፣ ወዘተ ፤ የእሚባሉ ነገሮች የሌሉ እና በተጨባጭነት የአለው ቁስ ብቻ በመሆኑ ፤ የሰው ግንዛቤ የቁሱ ዓለም ነጸብራቅ ነው የእሚል ነው። 


በእዚኽም ላይ ተመርኩዞ ፤ የሰው ግንዛቤ የቁሱ ዓለም ነጸብራቅ በመሆኑ እና የቁሱ ዓለም ደግሞ የእሚመራበት መርህ ፤ ቋሚ የሆነ በተቃራኒ አካላት መካከል በእሚኖር ግጭት የእሚፈጠሩ አዳዲስ እርጎች (States) በመሆኑ ፤ የሰው ልጅ የእሚኖረው ብቸኛው እና ትክክለኛው ግንዛቤ ፤ እርሱ ከእሚኖርበት የኢከነሚ መደብ ውጭ ከእሚኖሩ ሰዎች ጋር የእሚጋጭ ፤ የመደብ ትግል አስተውሎ ወይንም ግንዛቤ ብቻ ነው ፤ የእሚኖረው የእሚል ነው።


በሌላ አገላለጽ የሙግት ቁሳዊነት ፤ የሰው ልጅ ፖለቲካዊ ግንዛቤ ከእሚኖርበት ፤ ኢከነሚያዊ ደረጃ የእሚመነጭ እና እርሱም ፤ ከእርሱ የተለየ ወይንም የተሻለ ኢከነሚያዊ መደብ ውስጥ የእሚኖሩትን ሌሎችን በመደብ ትግል ለማጥፋት የእሚያነሳሳው ነው የእሚል ነው።


ከእዛኽ በመቀጠል ፤ የታሪክ ቁሳዊነት የእሚለው መላምቱ ደግሞ ፤ የሰው ልጆች በሙግት ቁሳዊነት ምክንያት በእሚኖራቸው የመደብ ትግል አስተሳሰብ ፣ አስተውሎ ወይንም ግንዛቤ እየተመሩ ፤ በጥንታዊነት ፍራፍሬ በመልቀም እና በአደን ይኖሩ ከነበረበት ፤ የጥንታዊ ጋርዮሽ ስረዓት ወደ ባሪያ አሳዳሪ ስረዓት ፥ ከባሪያ አሳዳሪ ስረዓት ወደ ፊውዳል ስረዓት ፥ ከፊውዳል ስረዓት ወደ ካፒታሊዝም ስረዓት ፥ ከካፒታሊዝም ስረዓት ወደ ሶሻሊዝም ስረዓት ፥ በስተመጨረሻም ከሶሻሊዝም ስረዓት ወደ ከምኒዝም  ስረዓት ይሸጋገራሉ የእሚል ነው።

ይኽንንም ተከትሎ ፤ አኹን በአለንበት የታሪክ ደረጃ ፤ የሰው ልጅ ታሪክም ፤ በእዚኽ የመደብ ግጭት እየተመራ ፤ ወሳኝ በእሚባሉት ሐገራት ውስጥ ካፒታሊዝም የእሚባለው የታሪክ ደረጃ ላይ ደርሷል ። ይኽም በመሆኑ ፤ በሙግት ቁሳዊነት ምክንያት ፤ ካፒታሊዝም ስረዓት ውስጥ ያሉት ፤ ባለ ኃብቶች እና የእነርሱ ሰራተኞች ፤ ተቃራኒ መደቦች በመኾናቸው ተጋጭተው ፤ ግጭቱም በብዙኃኑ በሠራተኛው ድል አድራጊነት ተደምድሞ ፤ ብዙኃኑ ሠራተኛው የፖለቲካ ስልጣን በመያዝ ሶሻሊዝም ስረዓትን ማቋቋማቸው የተፈጥሮ ግዴታ ነው ።

ይኽን መሰል ፤ የተብራራ እና ውስብስብ ትንታኔ የእሚያስቀምጠው ማርክሲዝም ግን ፤ ከሳይንሳዊነት አንጻር

አንድ ኹለት ብለን የእምንቆጥራቸው ፤ ወደ ስድስት የእሚጠጉ መሠረታዊ ግድፈቶች አሉበት ።


በእዚኽም ረገድ የመጀመሪያው ፤ ማርክሲዝም ፍልስፍናን እና ሳይንስን ያምታታ መሆኑ ነው። ፍልስፍናን እና ሳይንስ ምንም እንኳን ኹለቱም ሰፊ የኃሳብ መዋቅር እና ትንታኔ የአላቸው መሆናቸው ቢያመሳስላቸውም ፤ ፍልስፍና ከሳይንስ በተለየ መልኩ በአንድ ጥያቄ ወይንም ጉዳይ ላይ የተለያዩ እና አንዳንዴም የእሚቃረኑ መላምቶችን ሊያስቀምጥ የእሚችል ሲሆን ሳይንስ ከእዚኽ በተቃራኒ ለጥያቄዎች የእሚያቀምጣቸው መልሶች ወይንም ትንታኔዎች ብዛት ሊኖራቸው ቢችልም እንኳን የእሚቀመጡት መልሶች ዓለም ዓቀፋዊ ተቀባይነት የአላቸው ናቸው። 


በሳይንሱ ዓለም ፤ የአንድ ሦሥት ማዕዘን ስፋት የእሚለካበት ፤ በኹሉም የዓለም ጫፍ ተቀባይነት የአለው ቀመር አለ። በፍልስፍናው መስክ ግን እንደ እዚኽ ዓይነት ወጥ ተቀባይነት የእማይቻል ነው። በልዕለ ተፈጥሮ ትንታኔ ፤ ቁሱ ሳይፈጠር ያለ እና የነበረ ነው እንደ እሚሉት ቁሳዊያኑ ፤ ከእነርሱ በተቃራኒ ኃሳባዊያኑ ፤ ቁሱን የፈጠረው ከቁሱ ውጭ የሆነ የእማይፈጠር እና ቁስ ያልሆነ ፈጣሪ አለ ብለው የእሚያምኑ አሉ። 


እነ እዚኽ ተቃራኒ የልዕለ ተፈጥሮ መላምቶች ደግሞ ልዩነታቸው በሳይንሳዊ መንገድ ሊፈታ የእማይችል እና ከተጀመሩበት ከዛሬ 4 እና 5 ሺ ዓመታት አንስቶ የእየራሳቸው ተከታይ ይዘው የእሚኖሩ መስኮች ናቸው።

ስለ እዚኽ ፦ ሳይንሳዊ ነኝ የእሚለው ማርክሲዝም ፤ ራሱን ሳይንሳዊ በአልሆነ ፍልስፍና ላይ መስርቶ እና ከእዚኽ ሳይንሳዊ ከአልሆነ ፍልስፍናዊ አስተሳሰብ ከተፋታ የአስተሳሰብ መዋቅሩ በሙሉ የእሚንኮታኮት በመሆኑ ሳይንሳዊ መሆን የእማይችል እንዲኹም ሳይንስን እና ፍልስፍናን ያምታታ ነው።


የማርክሲዝም ሳይንስ እና ፍልስፍናን በእዚኽ መልኩ የማምታታቱን ችግር ብናልፈውም እንኳን ፤ ማርክሲዝም ኢሳይንሳዊ ነው ፤ ማለትም ፦ መላምቱ የአመክንዮ ተፋልሶ የአለው እና በሰው ልጅ ኢከነሚያዊ እና ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ ውስጥ በታሪክ ከተመሰከሩ ኃቆች ጋር የእሚጋጭ በመሆን የመረጃ (Data) መጣረስ የአለው ነው። 


የማርክሲዝምን አመክንዮ ተፋልሶ ከእሚያሳዩ ጉዳዮች መካከል አንዱ ፤ ማርክሲዝም ከዘመናዊ የኢከነሚክስ ሳይንስ ተግባራዊ እውነታ ጋር በመጋጨት ፤ የሸቀጦች ዋጋ የእሚወሰነው ገበያ ውስጥ ባለ የሸቀጦች ፍላጎት እና አቅርቦት መስተጋብር ሰአይሆን ፤ ሸቀጦቹን ለማምረት በዋለው የሠራተኛው ጉልበት ነው የእሚልበት ነው። 

ማርክሲዝም ግን እነ እዚኽን መሰል የአመክንዮ ተፈልሶዎች ብቻም ሰአይሆን የአለበት ፤ አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ፖለቲካዊ ታሪክ በማርክሲዝም ከተቀመጠው ትንታኔ ፍጹም ተቃራኒ የሆነ በመሆኑ ፤ የማርክሲዝም ትንታኔ ከታሪካዊ ኃቁ ጋርም የእሚጣረስ ነው። 


ለምሳሌ ፦ በማርክሲዝም አስተምኽሮ ፤ የሠራተኛው አብዮት ፤ ልክ እንደ ተፈጥሮ ሕግ ፤ በማሕበረሰባዊ የታሪክ ኺደት ውስጥ በራሱ ግዜ የእሚመጣ ፤ ተፈጥሮዋዊ የማሕበረሰብ ታሪካዊ ደረጃ እንደኾነ ቢያስቀምጡም ፤ ይኽ የተባለው አብዮት ፤ የሕሊና ሕግ ሳይገድባቸው ያለ ምንም ርሕራሔ በሺ እና በሚልየን የእሚቆጠሩ ሰዎችን የመግደል አባዜ የአለባቸው ሌኒን እና ስታሊንን የመሰሉ ሰዎችን ፤ ስረአቱ ሲያጣ ፤ በተተገበረበት ቦታ ኹሉ ሲፈራርስ እንደ ነበር የአብዛኛው ከምኒስታዊ ስረዓቶች ታሪክ ምስክር ነው ። 


ይኽም ብቻ አይደለም ፤ ማርክሲዝም የሠራተኛው አብዮት በኹሉም ማሕበረሰብ ውስጥ ፤ ተፈጥሮዋዊ የማሕበረሰብ ሕግ አካል ስለ ኾነ አይቀሬ ነው ቢልም ፤ ለምሳሌ ፦ ምንም እንኳን ፤ በራሺያ ፣ ጣሊያን እና በፈረንሳይ ተቀራራቢ ቁሳዊ/ኢከነሚያዊ ኹኔታ በወቅቱ ቢኖርም  ማርክሲዝም ፈረንሳይ እና ጣሊያን ውስጥ ፤ ራሻ ውስጥ ያገኘውን ስኬት ሊያገኝ አልቻለም። 


ለእዚኽ ልዩነት ምክንያቱ በፈረንሳይ እና በጣልያን ፤ የዴሞክራሲያዊ ስረዓት ከራሺያ በላይ ስለ ዳበረ ወይንም የተሻለ ማሕበረሰባዊ መሠረት ስለ ነበረው እና የከምኒስት ሰርጎ ገባዊ አብዮታዊ ቅስቀሳ በተመሳሳይ የካፒታሊስቶች ጣልቃ ገብነት ስለ ተመከተ ፤ በተለመደው የማርክሲስታዊ አብዮት ስልት ፤ በአመፅ እና በሴራ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ፤ በእነዚኽ ሐገራት መሳካት በአለመቻሉ እንደ ሆነ የብዙዎች እምነት ነው ።


እነ እዚኽ ክስተቶች ፤ የማርክሲዝም ሳይንሳዊ መላምት እና ነባራዊው ኹኔታ ያልተጣጣሙ እንደ ሆኑ ያሳያሉ።

ማርክሲዝም ግን ኢሳይንሳዊም ብቻ ሰአይሆን ፤ ጸረ ሳይንስም ነው። ማርክሲም ፤ የከምኒስት ማንፌስቶው ላይ በግልጽ እንደ ተጠቀሰው ፤ ጸረ ሳይንስ መሆኑን በአደባባይ የአወጀ ነው። በማርክሲዝም ፍልስፍና መሠረት ፤ አኹን በዓለም ላይ ያሉት የማሕበራዊ ሳይንስ እውቀቶች በሙሉ ፤ በንብረት ባለቤትነት መብት ላይ የተመሠረተው የመደብ ልዩነት ውጤት በመሆናቸው ፤ ከቤተሰብ ፣ ከኃይማኖት ፣ ከግል ንብረት ፣ ከሞያ ፣ ከሐገር ጋር አብረው መጥፋት ያለባቸው ናቸው ይላል።


ይኽም በመሆኑ ፤ ማርክሲዝም ከእርሱ ውጭ ያሉ የትኛውንም የዘመናዊ ማሕበራዊ ሳይንስ አይቀበለም። 

የሰው ግንዛቤው ከእሚኖርበት ቁሳዊ ኹኔታ ወይንም ኢከነሚያዊ መደብ ብቻ እና ብቻ ነው የእሚመነጨው የእሚለው ማርክስ ፤ የንብረት ባለቤትነት በእሚፈቅድ ማሕበረ ኢከነሚ ውስጥ እየኖረ ፤ እርሱ ከየት የንብረት ባለቤትነት መብት መጥፋት አለበት የእሚለውን ግንዛቤ እና ይኽ ማሕበረ ኢከነሚ የፈጠራቸውን ሳይንሳዊ እውቀቶች መጥፋት አለባቸው የእሚለውን ግንዛቤ እንደ አመጣው ሳይመልስ ወይንም ከራሱ መላምት ጋር ቀጥታ በእሚጋጭ አግባብ ፤ ነባራዊው እውቀት እና የመሐበረሰብ አደረጃጀቶች በሙሉ መፍረስ አለባቸው በማለት ተፋልሶ ይፈጽማል።


እንደገናም በካርል ማርክስ ፥ የታሪክ ቁሳዊነት ፤ ተፃራሪ መደቦች እንጂ ፤ የተበደለው መደብ ተወካይ ነኝ የእሚሉ ሰዎች (ፓርቲ) ፤ የመደብ ትግሉን በውክልና ያካኺዳሉ አይልም ።

 

ይኽ እንዲኾን ደግሞ ፤ ኹለት የዳበሩ እና በፍፁም አብረው ሊኖሩ የእማይችሉ ፤ በተፈጥሮዋዊ ተቃርኖ ውስጥ ያሉ መደቦች መኖር አለባቸው ። እነ እዚኽ መደቦች በእዚኽ ኹኔታ ለጠብ የእሚያበቃ አቅም ሳይዳብሩ ፤ ተቃርኖዋቸው ወደ አተረማማሽ ግጭት ሊለወጥ አይችልም ።


 የከምኒዝም  አብዮት በተካኼደባቸው ሐገራት በሙሉ ግን ፤ እነ እዚኽ መደባዊ ልዩነቶች ዳብረው እና ተፈጥረው ወደ ግጭት አልገቡም ፤ የኾነው ነገር ይኽን ትንታኔ እንደ ምክንያት አቅርቦ ፥ ያለ ከልካይ ስልጣን ለመያዝ አቅም የአላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች የመደምሰስ አካኼድ ነው የተስተዋለው ። 


የከምኒዝም አብዮት እና ስረዓት በመዓከልነት ስትመራ በነበረችው ራሺያ ፤ ሕብረተሰቡ ከምኒስታዊ መዋቅራዊ ለውጡን ሊፈልገው ቀርቶ መኖሩንም ሳይውቅ ነው የራሻው ከምኒስታዊ አብዮት የተካኼደው ።

ገበሬው በከምኒስቶች ተቀስቅሶ አብዮቱን ሲያጅብ የመሬት ባለቤት ትኾናለኽ ፣ ሠራተኛው ደሞዝ ይጨመርልኃል ፣ የሥራ ሰዓት ይቀነስልኃል ፣ ወዘተ ፤ በአጠቃላይ ‘ዳቦ ፣ ሰላም እና መሬት’ ታገኛለኽ ፤ ተብሎ ነው ። አንድ ግዜ ከምኒዝም  በስልጣን ከተደላደለ በኋላ ግን ፤ እነ እዚኽን ‘የዳቦ ፣ የሰላም እና የመሬት’ ጥያቄዎች ማንሳት ፀረ አብዮተኛ አስብሎ በግዳጅ ሥራ ፣ በእሥራት አንዳንዴም በሞት የእሚያስቀጣ ነው የኾነው ። 


በራሺያ ከምኒስቶች ከገበሬው እስከ ባለኃብቱ ቤት የአለውን ፤ በጎተራ ከተቀመጠ እህል አንስተው ማንኛውንም ኃብት ወደ መንግሥት ግምጃ ማስገባት በእሚል ዘርፈዋል ።  ኮምኒስቶቹ ለምን ይኽን አደረጋችኹ ተብለው ቢጠየቁ ፤ ይኽን ብር የዘረፍነው ልማት ለመሥራት እና ይኽን ልማት ለማካኼድ የእሚያስፈልገንን ስልጣን ለማስጠበቅ ነው እንጂ ፤ እንደ ተራ ወመኔ በስካር እና በመጠጥ ልናባክነው አይደለም የእሚል ይኾናል ፤ ቁም ነገሩ ፥ ተራ ቦዘኔ ሌባስ ቢያዝ ከእዚኽ የተለየ ምን ይላል?


ሌኒን ፤ ሐብቱን ዘርፈን ፤ በርኃብ በእየመንገዱ እየወደቀ ለእሚሞተው ድኃ እናከፋፍለው ወይንም ገበሬውን እናጠናክርበት አይደለም የአለው ፤ በግልፅ ቋንቋ የመንግሥት ፕሮጀክት እናካኺድበት ፥ ስልጣናችንን እናስጠብቅበት ነው የአለው ። የአፈ ታሪኩ ሮቢን ኹድ ዓይነት የፍትኽ ግንዛቤ እንኳን አላሳዩም ።

ሶሻሊዝሙን ፤ ወይንም ምርትን ኹሉ በጋራ አምርቶ ፥ እንደሥራ ተዋፆ መጠን መካፈልን ፤ ዘላቂ መፍትኼ አድርገን ስለ እምናይ ነው ፤ ከገዳማት የተዘረፈውን ለገበሬው ያላከፋፈልነው ሊሉ ይችላሉ ። ዘረፋቸው ግን ፤ በገዳማት ወይንም በትልቅ በአለኃብት የተወሰነ አልነበረም ፤ ተራ ከእጅ ወደ አፍ የእሚያርሰውንም ገበሬ ፤ ጎተራኽን አራግፈኽ እኽሉን ወደ መንግሥት ካዝና አስገባ እርሻህንም በማሕበር እንጂ በግልህ አትረስ ነው ያሉት ። ድህነት ያጎሰቆለው ገበሬ ፤ ይኽን ክፉ ግፊያ እምቢ በማለቱ ፤ ታሪካዊውን ሶሻሊዝም ገበሬው እምቢ አለ ተብሎ በአብዮት ጠላትነት ተፈርጆ እስከ ሞት የእሚያደርሱ ብዙ እንግልቶች ደርሶበታል ።


ይኽን መሰሉ ግድፈት የሞላበት ማርክሲዝም ፤ ከጽንሰቱ ጀምሮ እና ከቆርቋሪዎቹ ጨምሮ ፤ ከራሱ መላምት ጋር በእሚጻረር መልኩ ፤ የመደብ ትግልን በጭካኔ እና ያለምንም ህሊና ሕግ ለማድረግ ሲጥር የነበረ ነው። ይኽንን ሳይንሳዊ እና ሊሻር የእማይችል የተፈጥሮ ሕግ ነው የእምንከተለው እያሉ ፤ ኹሉም ማርክሲስቶች ፦ ማርክስ ፣ ሌኒን ፣ ስታሊን ፣ ማዖ ፣ ወዘተ ፤ ከማርክሲስዝም መርህ ውጭ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ እና በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲንቀሳቀሱ ነበር።


ይኽም በመሆኑ ፤ ማርክሲስቶች የፍልስፍናቸውን መላምት ፊት ለፊት አስቀምጠው ፤ ፖለቲካዊ ግባቸውን ለማሳካት ፤ ከመላምቱ ጋር ፍጹሙ የእሚጋጩ አካኼዶችን በመከተላቸው ፤ በዘመናችን ከታዩ አምባገነናዊ ስረዓቶች በተለየ እና በገነነ መልኩ ፤ ማርክሲስቶች በስልጣን ለቆየባቸው ዓመታት ኹሉ ፤ ለሰው ልጆች የሰቆቃ እና የእልቂት ምክንያት ሆነው ነበር። 


ከማርክስ ጀምሮ ያሉት ኹሉም ማርክሲስቶች ፤ ማርክሲዝም መመሪያችን ነው እያሉ ለብዙ አስርት አመታት በአደባባይ እየለፈፉ ፤ ነገር ግን በተመሳሳይ በእዚኹ በአደባባይ ፤ ከጅማሪያቸው አንስተው እስከ ፍጻሜያቸው ድረስ ፤ ከማርክሲዝም መርህ በተቃራኒ እየተንቀሳቀሱ ፤ የዓለምን ሕዝብ አይቶ በእማያውቀው የመከራ ባሕር ውስጥ የጨመሩት ፤ በመጀመሪያ የማርክሲዝምን ኢሳይንሳዊነት ከእሚያጋልጡ ሰዎች በመሸሽ ነው።


ይኽንን አካኼድ ማርክስ በመጀመሪያው እና በኹለተኛው የሠራተኛው ዓለም ዓቀፋዊ ማሕበር ውስጥ የተከተለው ነው።


ማርክስ በመጀመሪያው የዓለም ዓቀፍ የሰራተኞች ማሕበር ውስጥ ከሙህራን ትችት በመሸሽ ነው የወጣው እና ኹለተኛ የዓለም ዓቀፍ የሰራተኞች ማሕበር የእሚባለውን የተቀላቀለው። 


ስለ እዚኽ ፦ ማርክሲስቶች ለኢሳይንሳዊው መላምታቸው ተከታይ ሲያፈሩበት የነበረበት መንገድ ፤ ያለ ምንም ጥያቄ በማርክስ ዲያሌክቲክስ ብቻ አምነው የእሚከተላቸውን የእማይጠይቅ እና ለመታዘዝ የቆረጠ ኃይል መሰብሰብ ፤ ከእዚያኽም በእዚኽ ፥ የእማይጠይቅ ፣ ታዛዥ እና የደረጀ ኃይል በኃሳብ የእሚቃወማቸውን ኹሉ በጉልበት ከአጠፉ በኋላ ፤ በእዚኽ ጥቂት የተደራጀ ኃይል ፤ ነባራዊ ማሕበራዊ መዋቅሮችን በሙሉ በማፈራረስ ፤ የራሳቸውን አዲስ መዋቅር ገንብተው ፤ በአንድ ሐገር ብቻ ሰአይኾን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የአለውን ፤ ፖለቲካዊ ስልጣን እና ኃብት በቁጥጥራቸው ስር ማስገባት ነው ። 


ስለ እዚኽ ፦ ከምኒዝም  በነገሠባቸው ሐገራት ፤ የፖለቲካ ስልጣኑን የያዘው ፤ በማርክስ ቲየሪ መሠረት ፥ በተቃራኒ መደቦች መካከል የመደብ ትግል ተደርጎ ሰአይኾን ፤ የከምኒዝም  አብዮት በተሳካባቸው ሐገራት የነበረው ሙህር (የሕብረተሰብ ሰላማዊ መሪዎች) ፤ በዴሞክራሲያዊ ውይይት ተግባብተን እንሰራለን ብሎ ከምኒስቶቹንም የጨመረ ውይይት ሲያካኺድ ፤ ይኽን በሰው መርህ የእሚመራ አዋቂ ፤ በአውሬ መርህ የእሚመሩት ራሳቸውን “እውነተኛ” ከምኒስት የእሚሉት ፤ እንደ ደራሽ ጎርፍ መጥተው ጨፍጭፈው በማውደም ራሳቸውን ብቸኛ ገዳይ እና አምባገነናዊ የፖለቲካ ኃይል በማድረጋቸው ነው ። 


ማርክሲስቶች በእዚኽ መልክ ፤ እውር ተከታይ እና ደጋፊዎች ከሰበሰቡ በኋላ ፤ በእነ እዚኽ እውር ደጋፊዎቻቸው አማካይነት ፤ ከራሳቸው ፓርቲ ጀምረው እስከ ሰፊው ማሕበረሰብ ውስጥ ያሉ ፤ የስልጣን ተቀናቃኝ ሊሆኑኝ ይችላሉ የእሚሉዋቸውን ሰዎች በሙሉ ያለምንም ርህራሔ ያጠፉዋቸዋል።

ከራሳቸው ፓርቲ ፣ ከተቀናቃኝ ፓርቲ እና በሕበረተሰብ ውስጥ ያሉ ፤ ትልልቅ ነጋዴዎችን ፣ የተማሩ ሰዎችን ፣ የመሪነት ብቃት የአላቸውን ሰዎች በሙሉ በጸረ አብዮተኛነት ፈርጀው ያጠፋሉ።


እንዲኽ አድርገው ፤ ሲለው በኢሳይንሳዊ ቲየሪ ሰአይኾን  በአመፅ ፤ የጭቁኑ ወገን ሞግዚት ነን ብለው የፖለቲካ ስልጣን የያዙት ከምኒስቶች ፤ ስልጣን ከያዙ በኋላ ፤ ራሳቸው አዲስ ገዢ መደብ ኾነው ፤ የራሳችውን የስልጣን እና የኃብት ጥቅም ለማስከበር ረዥም ርቀት የእሚኼዱ ፤ ፍፁማዊ እና በዝባዥ አዲስ ገዢ መደብ ነው የኾኑት ።

ሚሎቨን እንደ እሚነግረን ፤ የከምኒዝም  ፓርቲ አመራሮች ፤ ለድኃው በእሚደረግ ትግል ስልጣን ከያዙ በኋላ ፤ ራሳቸውን ወደ አዲስ የገዢ መደብ ነው የእሚለወጡት ። 


ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ፤ የሰፊው ሕዝብ ፍላጎት ፤ በስልጣን ላይ ባሉ በጣት በእሚቆጠሩ ሰዎች ፍላጎት ይዋጣል ፤ ከእዚኽም የተነሳ ፤ በከምኒዝም  ስም ትግል የአደረገ ጭፍራ እና አዲሱ የገዢ መደብ የኾነው ቋንቋቸው የተደበላለቀ ይኾናል ። ለምሳሌ ፦ ኹለቱም አብዮቱ ይላሉ ፤ ለአዲሱ የገዢ መደብ አብዮቱ የስልጣናቸው መጨበጫ ይኾናል ፤ ለተሳታፊው ግን ጭቆናን ለማስወገድ ፣ ፍትሕን ለማስፈን ፣ ወዘተ ፤ የተካኼድ የሞት ሽረት ትግል ይኾናል ፤ ምንም እንኳን ነፃነት እና ፍትሕ መሰል አስተሳሰቦች ለከምኒዝም ትርጉም አልባ ቢኾኑም ። 


የከምኒስት ፓርቲ አንቀሳቃሾች ፤ ምሁሩን እና የነቃውን የማሕበረሰብ ክፍል ፤ ለአብዮት ማቀጣጠያነት ከተጠቀሙበት እና አብዮቱ ፈንድቶ ስልጣን በያዙ ማግስት ፤ ይኽን ምሁር እና የነቃ ማሕበረሰብ ፤ የስልጣን ስጋት ስለ እሚኾንባቸው ፤ በሰበብ አስባቡ የፀረ አብዮት እንቅስቃሴያቸው ሰለባ ያደርጉታል   ።

የተማሩ የእሚሉዋቸውን ሰዎች ማጥፋት የታወቀ አሰራራቸው ነው ።


ከምኒዝም  የድኃ ፖለቲካ አይደለም ፤ የደኃ ተቆርቋሪ መምሰልን ለፖለቲካ ማታለያነት ይጠቀምበታል እንጂ ። 

በድኃው ወይንም በጭቁኑ ስም ስልጣን ከያዘ በኋላ ፤ ድኃው ወይንም ጭቁኑ ፤ ከባሪያ ያነሰ ፖለቲካዊም ኾነ ኢከነሚያዊ አቅም እንደ አይኖረው ለማድረግ ቆርጦ ይሰራል ። ድኃው የሐገሩ ባለቤት እንዲኾን ሰአይኾን ፤ ጥቂት የፓርቲ አባላት እና ሹመኞች ፤ የሐገሩ ባለቤት እና ብቸኛ ባለስልጣናት እንዲኾኑ ይሰራል ። ከምኒዝም  ስልጣን ላይ ከተደላደለ በኋላ ፤ ገበሬው ፣ ሠራተኛው ፣ ሞያተኛው በሙሉ የስረዓቱ ገባሪ እና ተገዢ ነው የእሚኾነው ። 


ይኽ አካኼድ እና አሰራር ፤ ማርክስም ፣ ሌኒንም ፣ ስታሊንም የእሚያምኑበት አካኼድ ነው ፤ በእርግጥ ሌኒንዝም ወይንም ስታሊንዝም ማለትም ጭብጡ ይኽ ነው ። ስለ እዚኽ አንድ ሰው ፤ እኔ ከምኒስት ነኝ ሲል ፦ ወይ የፖለቲካ ስልጣን በኃይል በታገዘ ሴራ ለመያዝ ማንኛውንም ዓይነት ወንጀል እፈፅማለኹ እያለ ነው ወይንም ደግሞ የተታተለ ተከታይ ነው ማለት ነው ።


ይኽ በኃሳብ ገበያው ሲሸነፉ ፤ እየተገነጠሉ ፤ ወደ ግራ ወደ ቀኝ የእማይሉ ተከታዮችን አፍርቶ ፤ ይኽን ጭፍን ተከታይ ወደ ተደራጀ ኃይልነት ቀይሮ ፤ ሊወያይ በመጣ ኃይል ላይ መልቀቅ (ሌኒንዝም ፣ ስታሊንዝም ፣ ቦልሼቪዝም) እና የኃሳብ ተቀናቃኞችን ከምድረገፅ በድንገት ማጥፋት ፤ ከሚንተርን በራሺያ የተከተለው ብቻ ሰአይኾን  ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምኒዝም  በገባባቸው ሐገራት ኹሉ የእሚደገም ስልት እንደ ኾነ እና ይኽም አካኼድ በማርክሲስታዊ ፖለቲካዊ ፍልስፍና እና በፓርቲ የትግል ስልት ሰነዶች ላይ ፤ በግልፅ የተብራራ በመኾኑ ፤ ጉዳዩ የተወሰኑ አፈንጋጭ ክስተቶች ጉዳይ ሰአይኾን ፤ ወጥነት የአለው ማርክሲስታዊ አካኼድ ስለመኾኑ ግልፅ ማሳያ ነው ። 


 እነዚኽን መሰል የጭከና ሥራዎች ለመሥራት የቆረጠ በመኾኑ እና ለእዚኽም ኢሰባዊ ተግባሩ ፤ የፅንሰኃሳብ ማገዣ ከማርክሲዝም የእሚያገኝ በመኾኑ ፤ እንደ ዘመናዊው ከምኒዝም  ያለ ፖለቲካዊ ፅንፈኛ ስረዓት በዓለም ሕዝብ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም ።


እንግዲኽ ከላይ ያየናቸው መሬት ላይ ያሉት ኃቆች ፤ ከምኒዝም  እንደ እሚለው ፥ ማሕበረሰብ ፤ በሙግት ቁሳዊነት መዘውር ታሪክ እየተመራ ከአንድ መዋቅር ወደ ሌላ ዓይነት መኃበራዊ መዋቅር ይሸጋገራል ፤ ይኽም ማንም ሊጋፋው የእማይችል ‘ተፈጥሮዋዊ’ ሕግ ነው የእሚለው እንደ እማይሠራ በታሪክ ስለ ታየ ፤ የራሳቸው

የከምኒስቶች ታሪክ ለማርክሲዝም ቲየሪ እርባና ቢስነት ዓይነተኛ ማሳያ ነው ። 


ማርክሲዝም በእዚኽ መልኩ ፦ ሳይንስና ፍልስፍናን በማምታት ፣ ጸረ ሳይንስ በመሆን ፣ ኢሳይንሳዊ በመሆን ፤ ተጨባጫዊነትን ዋነኛ የፖለቲካ ስልቱ አድርጎ መራመድ የቻለው ፤ ማርክሲዝም በግልጽ ፤ የአለ በቂ ሳይንሳዊ ምክንያት ስነምግባር ወይንም ህሊና የእማያስፈልጉ ነገሮች ናቸው ብሎ በማውገዝ ፤ ተከታዮቹን ከስነ ምግባር ወይንም ከህሊና ፍርድ እንዲላቀቁ ማድረግ በማቻሉ ነው። ይኽም ማለት ማርክስዚም ጸረ ስነምግባር ነው።

ሌላው ልዩ የኾነው የማርክሲዝም መለያ ፤ ከመፀነሱ ጀምሮ ፤ ይኽ በሳይንስ ፣ በድኃ እና በጭቁን ሕዝብ ስም ፤ ለመዝረፍ ወደ ስልጣን የመጣ ቡድን ፤ ዘራፊ ኾኖ በአንድ ሐገር መቆየት እንደ እማይችል አስቀድሞ ስለ ተረዳ ፤ የዘረፋ መዋቅሩን ፤ በከምኒስት ኢንተርናሽናል ፣ በራሺያው የስለላ ድርጅት እና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፤ በራሺያው ከምኒስት ፓርቲ ዋና መሪነት ፤ በአብዮት ስም ፤ የዳበረ ዴሞክራሲያዊ ስረዓት በሌላቸው እና ድኀነት እና መኃይምነት መንግሥታዊ መዋቅራቸውን በአደከሙባቸው ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሐገራት የእሚያስፋፋ መኾኑ ነው ። በእዚኽም ዓለም ዓቀፋዊ የመንግሥታዊ ዘረፋ እና አምባገነንነት መረብ በመኾን ፤ አዲስ ዘመናዊ ፖለቲካዊ ክስተት ኾኗል ።


 ይኽ እንግዲኽ የዘመናዊ ፖለቲካዊ ፅንፈኝነት ኹሉ የበላይ የኾነው የማርክሲዝም ፖለቲካዊ ገፅታ ነው ።

ከላይ እንደ አልነው ፤ ሕዝባዊ ሕገመንግሥት አልባ የዘውድ ስረዓቶች ፣ በደም ተወራራሽ የፖለቲካ ስረዓቶች ፣ እንደ ፋሺዝም እና ልማታዊ መንግሥት ያሉ ዘመናዊ የተደራጁ የፖለቲካ ስረዓቶች ፤ የፖለቲካ ስረዓት ፅንፈኝነት ፈርጅ ውስጥ ልናስገባቸው የእምንችል ቢኾንም ፤ የማርክሲዝም ልዩ ባሕሪ እነ እዚኽን ኹሉ ስረዓቶች ስለ ዋጣቸው እና ፋይዳ ቢስ ስላ አደረጋቸው ፤ ትኩረታችንን በማርክሲም ላይ አድርገናል ።


እንደ አልነው ፤ ፋሺዝም በእዚኽ ዘመን ፤ እንደ ፖለቲካዊ ርዕዮት በግልፅ እና በስፋት የእማይስተዋል ቢኾንም ወይንም በዋናነት የከሰመ ፅንፈኛ ፖለቲካ ቢኾንም ፤ አንድ አንድ የፋሺዝም አስተሳሰብ ሐረጎች እንደ ማድመቂያ ብልጭታ እዚኽም እዛም ስል እሚስተዋሉ ፤ የፖለቲካዊ ፅንፈኝነት ዳሰሳችንን ሙሉ ለማድረግ የፋሺዝምን ቅሬታ አስተሳሰብ ተመልክተን እና ፋሺዝም በሐገር ጉዳይ ከማርክሲዝም የእሚለይበትን ነጥብ አስቀምጠን ይኽን ንዑስ ክፍል እንደምድም ።


ፋሺዝም ወይንም ፋሺስት የእሚለው ቃል ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃም ኾነ በእኛ ሐገር ፤ ሲጠራ ሰው አዕምሮ ውስጥ የእሚመጣው ግንዛቤ ጨፍጫፊ የእሚለው ነው ። ምናልባት ፤ በተለይ በእኛ ሐገር ቃሉ ፋስ (መጥረቢያ) ከእሚለው ቃል ጋር የአለው ቁርኝትም ይኽን ‘የተሳሳተ’ ግንዛቤ ሳያግዝ አልቀረም ። በእርግጥ ፋስ እና ፋሺዝም መመሳሰላቸው አጋጣሚ ኾኖ ሰአይኾን ፤ የፋሺስት ፓርቲ ልዩ ምልክቱ ይኽኑን ፋስ (መጥረቢያ)


ከማድረጉ የመጣ ነው ። ፋስ የአማርኛው መዝገበ ቃል ውስጥ የገባው ከጣሊያንኛ ይኾን ይኾናል ።

 የፋሺዝም ስረዓት መሥራች የኾነው ፤ ቤኒቶ ሞሶሎኒ (Benito Mussolini) ፤ የፋሺዝም ቀኖና (The Doctrine of Fascism) በእሚለው ጽኹፉ ላይ ፤ ፋሺዝም በቀጫጭን በትር እስሮች እጀታ ላይ የተቀመጠን ፋስ ምልክታቸው የአደረገበትን ምክንያት እንዲኽ አስቀምጦታል ፦


“ይኽንን ዓላማ ለማሳካት ስነ ምግባርንን እያስከበረ እና ስልጣንን እየተጠቀመ ፤ ወደ ሰዎች ነፍስ ውስጥ ገብቶ ያለተቀናቃኝ ይገዛል ። ስለ እዚኽም ፤ የጋሻ ጃግሬውን ፋስ ፤ የአንድነት ፣ የጥንካሬ እና የፍትሕ ምልክት እንዲኾነው መርጧል ።”

“To achieve this propose it enforces discipline and uses authority, entering into the soul and ruling with undisputed sway. Therefore, it has chosen as its emblem the Lictor’s rods, the symbol of unity, strength, and justice. [31]“



 

ምስል 1 ፡ የሞሶሎኒው ፋሺስት ፓርቲ ምልክት አድርጎ የመረጠው የጋሻ ጃግሬው ፋስ።

በእዚኽ ክፍል ላይ እንደ እሚታየው ፤ የፋሺስት ፓርቲ ይኽንን ፋስ (መጥረቢያ) ልዩ ምልክቱ ሲያደርግ ግን ጨፍጫፊ ነኝ በእሚል ሰአይኾን ፤ ፋስ ፥ የጥንታዊ ጣሊያን ወታደሮች ወይንም የባላባቱ ጋሻ ጃግሬዎች የእሚይዙት መሳሪያ ፤ ስለ እዚኽም የመንግሥት ወይንም የፍትሕ ምልክት በመኾኑ እና ጥንታዊያኖቹ የእሚይዙት የእዚኽ ፋስ እጀታ የቀጫጭን በትሮች እስር በመኾኑ ፤ ይኽ ከትብብር የእሚመጣ ጥንካሬን እና የማሕበራዊ ፍትኽ አስተሳሰብን እንዲያመለክት ነው ። 


በአጭሩ ፋሱ የማሕበራዊ ፍትሕ ፤ ምሳሌያዊ ምልክት እንዲሆን ነው የታሰበው ፤ ልክ በዴሞክራሲያዊያኑ ሐገራት ወይዘሪት ፊትሕ አይኗን በጥቁር ጨርቅ ታሥራ ፤ ሚዛንን በግራ እጇ እና ሰይፍ በቀኝ እጇ ይዛ መታየቷ የፍትሕ ምልክት እንደ ሆነው ማለት ነው።


ፋሺዝም ከጭፍጨፋ ጋር በልማድ የተያያዘው ፤ ለፍትኽ ተነሳኹ በማለቱ ሰአይሆን ፤ ይልቁንም ሐገር መጀመሪያ ሰው በኋላ በእሚል ‘ብሔርተኝነት’ የሰውን ወይንም የዜጎችን ነፃነት እና ሕይወት ለመግፈፍ ወደ ኋላ የእማይል ስረዓት በመኾኑ ወይንም የዜጎች ደኀንነት ከሐገር ደኀንነት በኋላ ይመጣል በማለቱ ነው ። 

ይኽን ኃሳብ ሞሶሎኒ እንዲኽ አስቀምጦታል ፦


“ ፀረ - ግላዊ የኾነው ፋሺስታዊው የሕይወት ውጥን ፤ የመንግሥትን (ሐገርን ፥ ብሔራዊ መንግሥቱን) ጠቀሜታ አበክሮ ግለሰቡን የእሚቀበለው ፤ የግለሰቡ ፍላጎት ከመንግሥት ፍላጎት ጋር እስከ ሰመረ ድረስ ብቻ ነው ፤ ይኽ መንግሥትም የሰው ዘር እንደ ታሪካዊ ፍጥረት ዓለም ዓቀፋዊ እና ሆንታዊ ፈቃድ መገለጫ ነው ።“

“Anti-individualistic, the Fascist conception of life stresses the importance of the State and accepts the individual only in so far as his interests coincide with those of the State, which stands for the conscience and the universal, will of man as a historic entity. [31]“ 


በሌላ አገላለፅ ፤ ሐገር የሰው ሳትኾን ሰውን የሐገር ንብረት በማደረጉ ነው ። ይኽ ዓይነቱ ፖለቲካዊ አካኼድ ወይንም ፋሺዝም ደግሞ ፤ መጨረሻው በሐገር ሕልውና ስም ወይንም በብሔራዊ ደኀንነት ስም ፤ የሐገር መሠረት የኾኑ ዜጎችን ፤ ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከሕግ አግባብ ውጪ የእሚገፉ አምባገነን የፖለቲካ ጁንታዎች በመፍጠር ፖለቲካዊ ፅንፈኛ እንደ እሚኾን የታወቀ ታሪካዊ ኃቅ ነው ።


ሐገርን ከግለሰብ ማስቀደም ወይንም የግለሰብ ደኀንነት ከማሕበረሰቡ ደኀንነት አይበልጥም የእሚሉት ፋሺስታዊ አባባሎች ሲያዩዋቸው እውነት ይመስላሉ ። እውነታው ግን የግለሰብ ደኀንነትን ማረጋገጥ የእማይችል መንግሥት ማሕበራዊ ወይንም ሐገራዊ ደኅንነትን ሊያረጋግጥ አይችልም ።

ነገሩ ወይንም አካኼዱ ፤ የማሕበረሰብ ደኅንነት ስናረጋግጥ አይደለም ሐገር የእምትረጋው ፤ ይልቁንም የግለሰብ ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሕጋዊ ጠበቃ ሲያገኙ ነው ሐገር የእምትረጋው ። ፋሺስቶች ግን ከእዚኽ ፍፁም ተቃራኒ ስለ እሚያስቡ ወይንም ይኽንን የሐገር ደህንነት ምክንያት የፍፁማዊ ስልጣናቸው መሸፈኛ ማድረግ ስለ እሚፈልጉ የተለመደው አምባገነናዊ ጥገኝነት ይወርሳቸዋል ።


ከእዚያኽ በመለስ ግን ፤ ፋሺስቶች እና የእነርሱ ተቀራራቢ የኾኑት ከማርክሲስት ውጭ የአሉት ፍፁማዊ አምባገነኖች ፤ ብሔራዊ ፍቅርን ከልክ በማሳለፍ ይከሰሱ ይኾናል እንጂ የሐገርን ፅንሰ ኃሳብ በመክዳት ወይንም በማጣጣል አይታወቁም ።


ከእዚኽ የተነሳ ፤ ፋሺስቶችን እና ሌሎቹን የፖለቲካ ፅንፈኛ ኃይሎች ከማርክሲስቶች ጋር ፤ የከበረ ለእሚሉት ፖለቲካዊ ኃሳብ ሰውን ወይንም ዜጎችን ለመሰዋት ፈቃደኛ መኾናቸው ሲያመሳስላቸው ፤ ከማርክስ ውጭ የአሉት ፖለቲካዊ ፅንፈኞች ሐገርን በፅንሰ ኃሳብ ደረጃ መቀበላቸው ከማርክሲዝም ይለያቸዋል ።


ለማርክሲዝም በተቃራኒው ሐገር ማለት የቡርዥዋ ማሕበረ ኢከነሚ የእሚፈጥረው የካፒታሊዝም ስሪት በመኾኗ ፤ ልክ እንደ ግል ንብረት ባለቤትነት መብት መጥፋት የአለባት ነች ። 

ይኽም በመኾኑ ማርክሲዝም ፤ በግዜያዊ ታክቲክነት ሐገርን ሊታገስ ቢችልም ፤ በርዕዮት ደረጃ ሐገር እና መንግሥት መጥፋት የአለባቸው መኾኑን በግልፅ ያስቀመጠ ነው ፤ ‘ሠራተኛ ሐገር የለውም’ ብሎ ።