
በእዚኽ ንዑስ ክፍል ፤ ሐገርን ሐገር የእሚያስብላት መዋቅር ይኽ ዓይነቱ ነው ብለው የእሚሞግቱትን ፖለቲካዊ ርዕዮቶች ፤ ቀደም ብለን እንደ አልነው በፅንፈኝነት እና በዴሞክራሲያዊነት ከፍለን በዝርዝር እናያቸዋለን ።
የፅንፈኝነቱን ጎራ ደግሞ እንደገና በእሚከተሉት አምስት ጎራዎች እንከፍለዋለን ፦
በተናጠል እና እንደ አንድ ሙሉ ፈርጅ ለብቻው እንመለከታለን ።
ምንም እንኳን ፤ በሚድያዎች እና አንዳንዴም በማሕበራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች ዘንድ ፤ የተለያየ ዓይነት ዴሞክራሲ እንደ አለ የእሚባል ቢሆንም ፤ በእኔ እምነት በሰብዓዊነት ላይ ያልተመሠረተው ሌላው ዴሞክራሲ ፤ የዴሞክራሲን የኃሳብ የበላይነት በመጠቀም ራስን ዴሞክራሲያዊ ለማስመሰል የእሚወጡ የዳቦ ስሞች እንጂ እውነተኛ የዴሞክራሲ ዓይነቶች አይደሉም ።
ስለ እዚኽ ምንም እንኳን ፤ ሶሻል ዴሞክራሲ ፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፣ ወዘተ ፤ በእሚል ስም የእሚጠሩ የተለያዩ ዓይነት ዴሞክራሲ ተብዬዎች ቢኖሩም ፤ እነ እዚኽ የተለያዩ ዓይነት ዴሞክራሲዎች ፤ የዜጎችን ተፈጥሮዋዊ ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ባለቤትነት በመቀበል ፤ የማንኛውም ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ አህድነታቸውን በማወቅ ፤ የዜጎችን ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ማክበር እና ማስከበር የስረዓታቸው ዋነኛ መገለጫ የእማያደርጉ ስለሆኑ ፤ ከፖለቲካዊ ጽንፈኝነት ጎራ የእሚመደቡ እንጂ ሌላ የዴሞክራሲ ዓይነቶች አይደሉም በእሚል ፤ የነጻነቱን ዴሞክራሲ (Liberal Democracy) እንደ ብቸኛ የዴሞክራሲ ዓይነት አቀርበዋለሁ ።