ዘመናዊ ፖለቲካን ከልማዳዊ ፖለቲካ የእሚለየው ነገር ቢኖር ፤ ፖለቲካን በግምት እና በመሰለኝ ወይንም አንዳንዴ ይሳካል አንዳንዴ ደግሞ አይሳካም በእሚል ሳይሆን ፤ ውጤቱ እርግጠኛ በሆነ ሳይንሳዊ መንገድ ማራመድ ይቻላል ብሎ በማለቱ ነው።
በሌላ አገላለጽ ፤ ፍጻሜያችን በሳይንስ በመመራት የእምንፈልገው ልናደርገው እንችላለን ብሎ በማመኑ ነው።
ይኽን ሳይንሳዊ ዕምነት ለእሚጋሩ ኢትዮጵያዊያን በእዚኽ ድሕረ ገጽ ፤ ፍጻሜያችን ላይ ሊያደርሰን የእሚችለው ሳይንሳዊ ፍኖተካርታ ፤ ሕገክራሲ የእሚለው መጽሐፍ የመጀመሪያ ዘጠኝ ክፍሎች አቅርቤያለሁ።
መጽሐፍት እና ጽሑፎች የእሚለውን ኩላብ በመጫን እና ጽሁፎቹን በማንበብ የኢትዮጵያን ፍጻሜ ከግምት ወደ ሳይንስ ለማዛወር የድርሻዎን ይወጡ።
መልካም ንባብ !
