ማትኪ (MatKey)


ፎነቲክ የአማርኛ መጻፍያ

marketing-image

በአንጻራዊነት አማርኛ ለመጻፍ ቀላል የሆነ ፎነቲክ (Phonetic) አማርኛ መጽሐፊያ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለኹ። እንዴት እንደ እምትጠቀሙበት ዝርዝሩ ከታች አለ።

ሶፍትዌሩን በእዚኽ ያግኙ

 

የማትኪ (MatKey) የአማርኛ መጻፊያ ፤ አጫጫን እና አጠቃቀም መመሪያ።

 

  1. የአጫጫን ማብራሪያ

 

 

image

 

 

 

image

 

  1. የአጠቃቀም ማብራሪያ

 

አንድ አንድ ግዜ ፤ መጽሐፉ እንደ እሚለው ፦

ታናሽ ከተማ ነበረች፥ ጥቂቶች ሰዎችም ነበሩባት፤ ታላቅ ንጉሥም መጣባት ከበባትም፥ ታላቅ ግንብም ሠራባት። ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፤ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም። (መጽሐፈ መክብብ 9፡14 - 16)

ድኃ እና ኋላ ቀር ስለ ሆንን ፤ የሰለጠነው ዓለም እኛ ጋር ስለ አሉ ነገሮች ትኩረት ስለ እማይሰጥ እንጂ ፤ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መጻፊያ ስረዓት ፤ በሞያው ሰዎች አቡጊዳ (Abugida) ተብሎ ቢጠራም እና ለምሳሌ ፦ እንግሊዝኛው ከእሚጠቀምበት ፎነቲክ (Phonetic) ከእሚባለው የአጻጻፍ ስልት ፤ መሠረታዊ ልዩነት ያለው ቢመስልም ፤ ጉዳዩን ለተመለከተው ሰው ፤ አቡጊዳ የእሚባለው የአማርኛ አጻጻፍ ፤ ምንም እንኳን ከእንግሊዝኛው የእሚለየው ነገር ቢኖረውም እንደ እንግሊዝኛው ፎነቲክ (Phonetic) ወይንም ድመጸት ላይ የተመሠረተ የአጻጻፍ ስልት ነው። 

ድምጸት ላይ የተመሠረተ የአጻጻፍ ስልት ትርጉም እሚሰጠው ፤ እንደ ቻይና ካሉት እና ሎጎግራፊክ (Logographic) ከእሚባሉት እና የጽሑፍ ስረዓታቸው ድምጸትን ከመወክል ይልቅ ቃላትን የመወከል ዝንባሌ ካለው የአጻጻፍ ስረዓት ጋር ሲነጻጸር ነው።

ለምሳሌ ፦ እንግሊዘኛን ፣ አማርኛን እና ቻይንኛን ወስደን ፤ ተራራ ብለው የእሚጽፉበትን መንገድ ብናይ ፤ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ፤ እንደ እየ ቋንቋቸው ፤ ተራራ የእሚለውን ቃል ለማውጣት የእምንጠቀምባቸውን ድምጾች የእሚወክሉ ፊደል ሲጠቀሙ ፤ ቻይንኛው በአንጻሩ ቃሉን እንደ አለ የእሚወክል ስዕል ወይንም ምልክት ይጠቀማል።

አጻጻፍ

አማርኛ

ተራራ

እንግሊዝኛ

Mountain

ቻይንኛ

 

ከእዚኽ የተነሳ ምንም እንኳን በአብዛኛው ለዕለት ተዕለት ተግባር የእሚጠቀሙባቸው ምልክቶች ከ3 ሺ ባይበልጡም ፤ ቻይንኛ ለመጻፍ ከ50 ሺ እስከ 100 ሺ ምልክቶች ይጠቀማል።

በአንጻሩ እንግሊዘኛ 26 ብቻ ሲጠቀም አማርኛ ቢያንስ 33*8 = 264 ምልክቶች ይጠቀማል።

የአማርኛው እንደ ቻይንኛው በሺ ባይቆጠርም ከእንግሊዝኛው አንጻር በጣም የበዛው ፤ አማርኛው ሲጽፍ እንደ እንግሊዝኛው አናባቢ (Consonant) እና ተናባቢ (Vowel) ስለ እማይጠቀም ነው።

ለምሳሌ ፦ ተራራ የእሚል ትርጉም ያለውን Mountain (ማውንቴን) የእሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል ብንወስደው ፤ ማውንቴን የእሚለውን ቃል ለመጻፍ ፤ 7 ፊደሎች ተጠ።ቅሟል።

በአንጻሩ Mountain  የእሚለው ቃል በአቡጊዳ ቢጻፍ 5 ፊደሎች ብቻ ነው የእሚጠቀመው ፦ ማ ው ን ቴ ን።

ምክንያቱ ደግሞ ፤ እንጊልዘኛ ተናባቢ ላይ አናባቢ በመጨመር ድምጸት የእሚያወጣ በመሆኑ ነው። 

ለምሳሌ ፦ Mountain ፤ ማ (Mo) ው(u) ን (n) ቴ(tai) ን (n)። 

በምሳሌው እንደ እሚታየው ፤ በእንግሊዝኛውም አናባቢዎች (Vowels) እና ሳድሶች በአንድ ፊደል ነው የእሚወከሉት - ው(u) ን (n) ን (n)።      

ማ እና ቴ ግን በኹለት እና ሶስት ፊደሎች ነው የተወከሉት ፣ ተናባቢ ከአናባቢ ጋር በመያያዝ - ማ (Mo) እና ቴ(tai)።

ስለ እዚኽ ፦ የአማርኛው መጻፊያ ፤ አቡጊዳ ፤ በቋንቋው ውስጥ ላሉት ልዩ ድምጸቶች ኹሉ ፊደል ስለ እሚሰጥ ፤ ምንም እንኳን ድምጸታዊ (Phonetic) ቢሆንም ፤ በፊደል ደረጃ ከእንግሊዘኛው የእሚበልጥ ፊደላት አሉት ፤ በአብዛኛውም ቃላትን ከእንግሊዝኛው ባነሰ ፊደላት ይጽፋል።

ይኽን ወደ ኪቦርድ () ስናመጣው ፤ በብዙ ጥናት የተፈጠረው እና አኹን አብዛኛዎቻችን የእምንጠቀምበት ፤ ክወርቲ (QWERTY) የእሚባለው ኪቦርድ () ፤ በዋናነት 26 የእንግሊዘኛ ፊደላት እና ሌሎች አጋዥ ምልክቶች እና ቁጥሮች ብቻ እንዲይዝ ተብሎ ስለ ተሠራ ፤ ከ264 በላይ የተናጠል ፊደላት ያሉትን አማርኛ የእሚጠቀምበትን አቡጊዳ () የእሚለውን የመጻፊያ ሲስተም ፤ 26 ፊደላት ብቻ በእሚጠቀመው በክወርቲ ኪቦርድ ላይ መጻፍ እሚከብድ ይመስላል።

በተለይ ደግሞ አማርኛ አንድ ዓይነት ድምጽ ያላቸው ፦ ሀ ፣ ሐ እና ኀ ዓይነት ሶስት ፊደላት ወይንም የኢንግሊዝኛው ቋንቋ የእማያውቃቸው እንደ ጸ እንደ ጨ እና እንደ ጰ ያሉ ፊደላቶች ፤ ያሉበት መሆኑ ፤ ለእንግሊዝኛ ተብሎ የተሠራውን ኪቦርድ ከአማርኛው ጋር ማዛመዱን ከባድር ያደርጉታል።

ይኽን የማዛመድ ችግር መፍቻው መንገድ ፦

 

 ስለ እዚኽ ፦ በማትኪ (MatKey) የኪቦርድ አቀማመጥ ፦ የመጀመሪያው ፊደል ከተገኘ በኋላ 

በኪቦርድ ላይ ሲታይ ምን እንደ እሚመስል ፤ ከእዚኽ በታች ተቀምጧል።

> MatKey Layout Guide

MatKey (ማትኪ) የቁልፍ ሰሌዳ መመሪያ

~~
11
22
33
44
55
66
77
88
99
00
--
==
Backspace
Tab
q
w
eሳድስ
r
tተ/ጠ
y
uክልተ
iሠልስተ
oሳብዕ
pፐ/ጰ
[[
]]
\\
Caps Lock
aአ/ዐ/ኧ
sሰ/ሠ/ሸ
d
f
g
hሀ/ሐ/ኀ
j
kከ/ኸ
l
;
''
Enter
Shift
zዘ/ዠ
xጸ/ፀ
cቸ/ጨ
v
b
nነ/ኘ
m
,አምስ/፣
.ራብዕ/።/ስምንት
//
Shift
Ctrl
Emoji
Alt
Space
AltGr
Win
Menu
Ctrl