ይኽ ዘመናዊ የእምንለው እና ባለፊት 5 መቶ ዓመታት ፤ ከ6 ሺ ዓመታት በእሚልጠው የሰው ልጅ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ፤ ታይቶ በእማይታወቅ ፍጥነት እና ጥራት ከፍተኛ ዘመናዊነት (Modernity) የታየበት እና ዓለማችንን አኹን ለእምትገኝበት ከፍተኛ ደረጃ ያበቃት ከ15ኛው ምዕተ ዓመት ወዲ የተከሰተው የአውሮፓውያን ሕዳሴ (European Renaissance) ነው።
ይኽ የአውሮፓውያን ሕዳሴ ወይንም ዳግም ማንሰራራት መሠረቱ ፤ የሰው ልጅ አዕምሮውን በመጠቀም ፦ ለማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቹ ሰዋዊ መፍትሔ ማምጣት ይችላል የእሚለው አስተሳሰብ ነው።
ይኽን አስተሳሰብ ከፍተኛ ቦታ የእሚያሰጠው ፤ ከእዚያን ግዜ በፊት ሰዎች ፤ በተለይ አውሮፓዊያን ፦ ንጉሥን እግዚያብሔር ነው እሚሾመው ስለ እዚኽ መጥፎ ንጉሥ ካለ እግዚአብሔር ነው እሚያነሳው ፣ ድህነት በእግዚአብሔር በረከት ነው እሚጠፋው ስለ እዚኽ እግዚአብሔር በረከት እንዲያመጣ መጠበቅ ነው ፣ በሽታ ከሰይጣን ስለ ሆነ እሚፈወሰው በጸሎት ነው ፣ ወዘተ ፤ በአጠቃላይ ለማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጸሎት እና የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው መፍትሔ ከእሚል እሳቤ ወጥተው ፤ አዕምሮን የፈጠረው እግዚአብሔር ስለ ሆነ ፤ አዕምሯችንን ተጠቅመን ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን ብንፈታ ፤ እግዚአብሔር ከእሚያዝንብን ይልቅ ፤ ያ በረከቱን የእሚገልጽበት መንገድ ነው ፤ በእሚል የመጣ በመሆኑ ነው።
ይኽም በሰዋዊ መንገድ ሰዋዊ ችግሮችን መፍታት ፤ ተፈጥሯዊ እና የተፈጥሮ ባለቤት የሆነው የእግዚአብሔር መንገድ ነው ማለት ፤ ካፈራው የማሕበረ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ ፤ አንዱ እና ዋነኛው የነጻነት ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ነው።
ይኽም የነጻነት ዴሞክራሲ (Liberal Democracy) አስተሳሰብ ፤ የዘመናዊነት (Modernity) መሠረት ነው።
በእዚኽ ገጽ ውስጥ ፤ ኢትዮጵያ ከነጻነት ዴሞክራሲ ውጭ የሆኑ ሌሎች ሐገር የማዘመኛ አስተሳሰቦች ተከትላ ከ52 ዓመታት ሙከራ በኋላ እንኳን ያላሳካችውን ዘመናዊነት እና ኢንደስትሪያላይዜሽን ፤ ከ30 ዓመታት በአነስ ግዜ ውስጥ ልታሳካ የእምትችለው በነጻነት ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ነው በእሚል ፤ የነጻነት ዴሞክራሲን አስተሳሰብ በተለያየ መልክ ፤ ለሐገራችን ሰዎች የእማቀርብበት ገጽ ነው።