በአንጻራዊነት አማርኛ ለመጻፍ ቀላል የሆነ ፎነቲክ (Phonetic) አማርኛ መጽሐፊያ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለኹ። እንዴት እንደ እምትጠቀሙበት ዝርዝሩ ከታች አለ።
ሶፍትዌሩን በእዚኽ ያግኙ
የማትኪ (MatKey) የአማርኛ መጻፊያ ፤ የስልክ ላይ አጫጫን እና አጠቃቀም መመሪያ።
ኪቦርዱ በቀጥታ ሊባል በእሚችል ደረጃ QWERTY የእሚባለው እና ምስሉ ከእዚኽ በታች ያለው ኪቦርድ ግልባጭ ነው ፦
እንደ እዚኹም እንደ ተ ፣ ቸ ፣ ፕ ፣ ወዘተ ያሉት ፊደሎች ተደግመው ሲጫኑ ፤ ጠ ፣ ጨ እና ጰ የእሚሰጡ መሆናቸው ወይንም ድርብ መሆናቸው ነው።
በምስሉ ላይ እንደ እሚታየው አብዛኛዎቹ የአማርኛ ፊደሎች ኪቦርዱ ላይ ስለ እሚታዩ ፤ ለመጻፍ የፈለጉትን ፊደል መምረጥ ነው። ሆኖም ፦ ፊትለፊት የእማይታዩ ፊደሎችን ለማውጣት እና ቤታቸውን ለመቀየር ፤ ለምሳሌ ፦ ሀን ሁ የእሚደረግበት አግባብ እንደ እሚከተለው ነው ፦